92 የአእምሮ ጤንነትን ለመጠበቅ፤ በጉበት ላይ አላስፈላጊ የስብ ክምችት እንዳይፈጠር ለማድረግ፤ በፅንስ ወቅት የሕፃናት አእምሮ እድገት የተሻለ እንዲሆን እና በተለያዩ በሽታዎች አማካኝት የሚከሠቱ የማቃጠል ስሜቶች እንዳይፈጠሩ በማድረግ በኩል እገዛ ያደርጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የም ግብ ዘይቱ ሳይበላሽ ለረዥም ጊዜ (long shelf life) የመቆየት እና የመርጋት ችግር የሌለው መሆኑ ለጤንነት የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው፡ 10.3. የምግብ አዘጋጃጀት እና የተሰባጠረ አመጋገብ ሁኔታ (ሪሲፒ) በሀገራችን እስካሁን ባለው ሁኔታ ኅብረተሰቡ ካሚሊናን በስሱ በማመስ ወቅጦ እንደተልባ እሽት (ብጥብጥ) ለምግብ ማባያነት ይጠቀሙበታል፡፡ ጠቆር አድርጎ በመቁላት ወቅጦ ዱቄቱን ማንኛውም ወጥ አንደሚዘጋጅ ሠርቶ የመጠቀም ልማድ አለ፡፡ የእንጀራ ልስላሴ ለመጨመር በእንጀራ ዱቄት ዝግጅት ወቅት 0.5 ኪግ ለአንድ ኩንታል በመጨመር የሚጠቀሙበት ሲሆን ይህም የእንጀራውን የንጥረ ምግብ ይዘት ለማበልጸግ እና ጣዕም እንዲኖረው ይረዳል፡፡ የሽሮን ጣዕም የተሻለ ለማድረግ እና የንጥረ ነገር ይዘቱን ለማሻሻል ለ20 ኪግ የሽሮ እህል ላይ 120 ግራም የታመሰ ካሚሊና ደባልቆ ማስፈጨት ይቻላል /ስንጠረዥ 4/፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
93 10.3.1. የካሚሊና እሽት ቅንብር ጥሬ እቃ መጠን • ካሚሊና የቡና ትልቁ ስኒ (40 ግራም) • ውሃ ከ1-2 መካከለኛ ኩባያ • ጨው 1የሻይ ማንኪያ • ቃሪያ /ሚጥሚጣ/ 2 መካከለኛ/1የሻይ ማንኪያ • ነጭ ሽንኩርት 3 ፍሬ • ቀይ ሽንኩርትየተከተፈ 1 የሻይ ማንኪያ አዘገጃጀት • ካሚሊናውን ማጽዳት እና በነጩ ማመስ • በተዘጋጀ ንጹህ መውቀጫ መውቀጥና መንፋት • ቃሪያውን አጥቦ ፍሬውን ማውጣትና በደቃቁ መክተፍ • ነጭ ሽንኩርቱን ልጦ በማጠብ አድቅቆ መክተፍ • በታጠበ ሳህን ላይ የተዘጋጀውን የካሚሊና ዱቄት በማድረግ ውሃ ጠብ እያደረጉ በማንኪያ ወይም በታጠበ እጅ መምታት • በመጨረሻም ከላይ የተዘረዘሩትን ግብዓቶች በመቀላለቀል ከእንጀራ ወይም ከዳቦ ጋር ለምግብነት ማቅረብ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
94 ማሳሰቢያ:- በቃሪያ ቦታ ሚጥሚጣ ወይም በርበሬ መጠቀም ይቻላል:: ለሕፃናት ከሆነ የሚያቃጥል ነገር መጨመር አያስፈልግም፡፡ 10.3.2. ካሚሊና የተቀላቀለበት እንጀራ እና ሽሮ አዘገጃጀት 50 ኪግ ጤፍ ላይ በነጩ የታመሰ 0.25 ኪግ ካሚሊና በመቀላቀል ማስፈጨትና መጠቀም የእንጀራውን ልስላሴ ይጨምራል፤ ሽሮ ዱቄት በሚዘጋጅበት ወቅት ካሚሊናን ሌሎች ቅመሞች እንደሚገባው ሁሉ በ20 ኪግ የሽሮ እህል ላይ 120 ግራም በነጩ የታመሰ ቀላቅሎ አብሮ በመስፈጨት መጠቀም የምግብ ጣዕሙንና የምግብ ይዘቱን ያሻሽላል፡፡ 10.3. የካሚሊና ዱቄት ለማሰሻነት በአነስተኛ መጠን የቅባትነቱን መጠን ሳይቀንስ ብዙ እንጀራ መጋገር ያስችላል ይህም ለማሰሻ የሚወጣ ወጪን በመቀነስ ደረጃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው 10.4. የምግብ ማቆያና የኢ-ንጥረ ምግብ መቀነሻ ዘዴዎች የካሚሊና ዘይት እንደሌሎቹ ከእጽዋት የሚገኙ የምግብ ዘይቶች ሳይረጋ ለረዥም ጊዜ መቆየት የሚችል ሲሆን ዘሩ በድህረ ምርት ተባይም ሆነ በሽታ ተጋላጭ ባለመሆኑ ምርቱ ለረዥም ጊዜ መቆየት ይቻላል፡፡ የእፅዋት ተዋፅኦ የምግብ አይነቶች በተፈጥሮ እንደ ፌኖል፣ ታኒንና ፋቴት የተባሉ ኢ-ንጥረ ነገር ይዘት የያዙ በመሆኑ እኒህ ውሁዶች ደግሞ የተለያዩ ወሳን የመዕድን የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
95 አይቶችን የሰውነት አጠቃቀም በከፍተኛ መጠን ይቀንሳሉ፡፡ በመሆኑም የተለያዩ በህለዊ የምግብ አዘጋጃቶች በተለይም እንደ ውሃ ውስጥ መዘፈዘፍን፣ በስሱ በእሳት ማመስን፣ በማጎንቆል፣ መፈተግና መሰል የምግብ አዘጋጃት ሂደቶችን በመጠቀም የምርቶቹን ኢ-ንጥረ ነገር ይዘት መቀነስ ይቻላል፡ 10.5. በዝግጅት ሂደት ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች ንፅሕናን መጠበቅ፡- በምግብ አዘገጃጀት ወቅት ተገቢውን የግል፤ የመሥሪያ ቁሳቁስ እና የአካባቢ ንጽህናዎችን መጠበቅ የካሚሊናን ምግብ ለማዘጋጀት ጥሬ እቃውን ከአቧራ እና ባዕድ ከሆኑ ነገሮች የጸዳ ማድረግ፤የሚያዘጋጀው ሰውና የሚዘጋጅበት እንዲሁም የሚከማችበት እቃ ንጽህና መጠበቅ ንፅህናውና ደህንነቱ የተጠበቀ ውሃና የምግብ ግብዓትን መጠቀም፡-- ለም ግብነት የሚውለውን የካሚሊና የእህል ጥራትና ደህንነት ም ንጭ መለየትና ማወቅ፤ ለሚፈለገው አገልግሎት መዋል መቻሉን ማረጋገጥ፤ ምግብን በአግባቡ ማብሰል፡- ካሚሊናን በጥሬው ከመመገብ ይልቅ በተሻለ ሁኔታ የም ግብ ጣዕሙና ይዘቱ የተሻለ እንዲሆን በመካከለኛ ሙቀት ማመመስ እና መውቀጥ እና የዘይት ምጠናውን በመጠበቅ መጠቀም፤ ምግብን በጤናማ የሙቀት መጠን ውስጥ ማቆየት፡- የተዘጋጀውን ም ግብ ለረዠም ጊዜ አለማቆየትና የምግብ ደህንነት ስጋቶችን መከላከል፤ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
III ክፍል ሶስት የምግብ ሲናር የአመራረትና የአጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
97 1. መግቢያ ሲናር ከብርዕ ሰብሎች የሚመደብ ሲሆን ከገብስና ከስንዴ ጋር የተዛመደና በኢትዮጵያ አገር በቀል ሰብል ሲሆን ወፍ-ዘራሽ ሲናር (Avena abyssinica) እና አረም ሲናር ወይንም እንክርዳድ (Avena fatua) የሚጠቀሱ ሲናር ዓይነቶች ናቸው፡፡ እነዚህ አገር በቀል የሲናር ዓይነቶች ከስንዴና ከገብስ ጋር የሚበቅሉ ሲሆን እነዚህ ዝርያዎች በአርሶ አደሩ ዘንድ በአረምነት ይታወቃሉ፡፡ በሀገራችን በአርሶ አደሮች እጅ የሚገኙት የሲናር ዓይነቶች ለመኖነት ከውጭ ሀገር የገቡ ወይም አገር በቀል ዓይነቴዎች ናቸው፡፡ ከወጭ የገቡት የመኖ ዝርያዎች ለአህል ምርትነት ጥቅም ላይ እየዋሉ ቢሆንም ምርቃቸው እሾሃማ በመሆኑ በአጨዳና በውቂያ ወቅት የሰውን ቆዳ ስለሚወጉ በአምራቾች ዘንድ አይወደዱም፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ ሀገራችን የገቡ የምግብ ሲናር ዓይነቶች እሾሃማ ምርቅ የሌላቸው፤ ምርታማ የሆኑ፤ በንጥረ ነገር ይዘታቸው የበለጸጉና ለአገሮ እንዱስትሪዎች ግብዓት የሚሆኑ ዝርያዎች ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር እንስትቲዩት የተለቀቁት የምግብ ሲናር ዝርያዎች ቢኖሩም ወደ ምርት ስርዓቱ ከማስገባት አንጻር ውስንነት በመኖሩ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ አልተቻለም፡፡ ሲናር የም ግብ እና የመኖ ሲናር ተብሎ የሚከፈል ሲሆን የም ግብ ሲናር ዘሩ ለም ግብነት ገለባው ደግሞ ለእንስሳት መኖ ያገለግላል። የምግብ ሲናር በአሁኑ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ለጤና ከሚሰጠው ጥቅም በመነሳት የሰብሉ ተፈላጊነት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል። በሀገራችንም በደጋማው አካባቢ ሲናርን ለምግብነት በስፋት የሚጠቀሙ አርሶ አደሮች ቁጥር ቀላል ባይሆንም በተሻሻለ የአመራት ስርዓት ለመደገፍ ፓኬጅና የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
98 ማንዋል ባለመዘጋጀቱ በሰብሉ መስፋፋትና ምርታማነት ላይ ውስንነት እንደነበረው ይታወቃል፡፡ የምግብ ሲናር የምግብና ስነ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጠቀሜታ ካላቸው ሰብሎች መካከል አንዱ ሲሆን በንጥረ ነገር ይዘቱም የበለጸገ እንዲሁም የተለያዩ ጠቀሜታዎችን የሚያበረክት ሰብል ነው፡፡ ሰብሉን በዘመናዊ የአመራረት ስርዓት ውስጥ ለማስገባትና በየደረጃው የሚገኘው የኤክስቴንሽን ባለሙያ ግንዛቤ ይዞ በትክክለኛው የአመራረት ፓኬጅ በመጠቀም መስራት እንዲችሉ ይህን ማኑዋል ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የምግብ ሲናር ጠቀሜታ፡- ለምግብነት የምግብ ሲናር ለምግብና ስነ ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ያለው ጠቀሜታ የጎላ ነው:: ሰብሉ ከሌሎች የብርዕ ሰብሎች ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ የፕሮቲን፣ የማዕድንና የአሰር ይዘት ስላለዉ ለእናቶችና ለህጻናት አሰፈላጊውን የፕሮቲን ፍላጎት በሟሟላት በኩል ድርሻው ከፍተኛ ነው፡፡ ሲናር በአገር ዉሰጥ በእንጀራ፣ በቂጣ፣ በገንፎ፣ በአጥሚት፣ በሾርባ እና ለተለያዩ ባህላዊ መጠጥ ዓይነቶች በማዘጋጀት ለምግብነት ያገለግላል፡፡ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በትላልቅ ሆቴሎችና በሆስፒታሎች የምግብ ዝግጅት ላይ ጠቀሜታው እየጨመረ በመምጣቱ በምግብ እንዱስትሪዎች በመቀነባበር ላይ ስለሆነ ሰብሉ ለአግሮ እንዱስትሪዎች ጥሬ እቃ በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
99 ለመኖነት የምግብ ሲናር ገለባ ለእንስሳት መኖነት ተመራጭና ለስጋና ወተት ምርታማነት እንዲጨም ር የሚያደርግ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ የም ግብ ሲናር ተረፈ ም ርት በንጥረ ነገር ይዘቱና ለእንስሳቱ አመጋገብ ተስማሚ ሲሆን በመጠን ደረጃ ከሌሎች ብርዕ ሰብሎች የተሻለ ነው፡፡ እንደ አማራጭ ሰብል የምግብ ሲናር አረምን በመቋቋም ምርት ከሚሰጡ ሰብሎች መካከል አንዱ ሲሆን በዚህ ባህርይው የአረምን ዕድገት በመጫን የሚታወቅ ሰብል ነው፡፡ ሲናር ከሌሎች የብርዕ ሰብሎች በተሻለ ሁኔታ የአሲዳማነት ባህርይ ያለባቸውን የአፈር ዓይነቶች በመቋቋም የተሻለ ም ርት የሚሰጥ ሰብል ነው፡፡ አርሶ አደሮች በዚህ ባህርይው ም ክንያት በተራቆተ መሬት ላይ ውጤታማ ሰብል ነው በማለት ይገልጹታል፡፡ በመሆኑም ይህ ሰብል በአሲዳማ አፈር በተጠቁ አካባቢዎች አማራጭ ሰብል ነው፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
100 2. የማኑዋሉ ዓላማና ግብ 2.1. ዓላማ • በአሲዳማነት በሚጠቁ አካባቢዎች የምግብ ሲናርን በዘመናዊ የአመራረት ስርዓት ውስጥ በማስገባት የምርትና ምርታማነት ማነቆዎችን በመፍታት የምግብና ስነ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፤ • የምግብ ሲናርን ለማምረትና ለመጠቀም አርሶ አደሮች አዳዲስ ቴክሎጂዎችን እና አሰራሮችን በመጠቀም እንዲያመርቱ ምክረ ሀሳቦችን ተደራሽ ለማድረግ፤ • በየደረጃው ያሉ የግብርና ልማት ባለሙያዎች፣ የልማት ጣቢያ ሠራተኞችን ከም ግብ ሲናር ሰብሎች አመራረት ዘዴዎችና ቴክኖሎጂዎች ጋር በማስተዋወቅ ለአርሶ አደሩ ያልተቋረጠ ክትትልና የሙያ ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ አቅም ለመገንባት፤ 2.2. የማኑዋሉ ግቦች • በደጋማና በአሲዳማ አፈር በተጠቁ አካባቢዎች ተስማሚ የሆኑ የምግብ ሲናር ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮች ለአርሶ አደሮች ተደራሽ ሆነዋል፤ • በተሻሻሉ የአመራረት ዘዴዎችና ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ከፍተኛ የምግብ ሲናር ምርት ተመርቷል፤ • ለአግሮ ፐሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ በግብዓትነት የሚውሉ የምግብ ሲናር ሰብሎችን በዓይነት በመጠንና በጥራት ቀርቧል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
101 • በደጋማና በአሲዳማ አፈር በተጠቁ አካባቢዎች ከምግብ ሲናር ሰብሎች አመራረት ጋር ተያይዘው ያሉ ወሳኝ የምርትና ምርታማነት ማነቆዎች ተፈተዋል፤ 2.3. የማኑዋሉ አስፈላጊነት • የምግብ ሲናር ምርት ለምግብና ስነ ምግብ ዋስትና የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ፤ • የምግብ ሲናር የተሻሻሉ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ስለሚያደርግ፡፡ • የተሻሻሉ አሰራርና ቴክኖሎጂዎችን ምክረ ሀሳብ በአርሶ/ከፊል እንዲሰርፅ ተከታታይ የሆነ ምክርና ክትትል ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፡ • በዘርፉ ከሚንቀሳቀሱ የምርምርና የተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመስራት በምግብ ሲናር ሰብል ልማት የሚስተዋሉ የክህሎት ክፍተቶችን መሙላት፤ • የም ግብና ስነ ም ግብ ዋስትና በማረጋገጥ ጤናማ አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር፤ • በደጋማና በአሲዳማ አፈር በተጠቁ አካባቢዎች ያለውን የሰብል አመራረት ስርዓትን በማሻሻል የአፈር ለምነት ለማዳበር፣ የተባይ ዑደትን ለማቋረጥ፣ ዘላቂ የሆነ የሰብል ልማት እንዲኖር ከፍተኛ ሚና የሚጫወት በመሆኑ፤ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
102 3 . ሰብሉን የሚመረትበት ስነ-ምህዳሮች 3.1. ከባህር ጠለል በላይ ከፍታ የምግብ ሲናር የደጋ ሰብል ቢሆንም ከእርጥብ ቆላ እስከ ውርጭ ስነምህዳር ባላቸው አካባቢዎች መልማት የሚችልና ምርት መስጠት የሚችል እህል ነው፡፡ ሲናር ከባህር ጠለል ከ1500-3800 ሜትር ከፍታ ላይ በጥሩ ሁኔታ መመረት ይችላል፡፡ ሰብሉ በደጋ አካባቢዎች በስፋት የሚመረት ቢሆንም በቂ ዝናብ በሚያገኙ ቆላማ እና ውርጭማ ስነምህዳሮች ውጤታማ መሆኑን በማላመድ ተግባር በተሰሩ ምርምሮች ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ 3.2. የአየር ሙቀት የምግብ ሲናር ዝቅተኛና መካከለኛ የአየርና የአፈር ሙቀት ባለባቸው አካባቢዎች መመረት የሚችል ሰብል ነው፡፡ ሰብሉን ለማምረት የአካባቢ ሙቀት ዝቅተኛና ከፍተኛ መጠን ከ10-25 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሲሆን ለሰብሉ የተሻለ ምርት ተስማሚ የሆነው የሙቀት መጠን ግን በአማካይ 15-22 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነው፡፡ 3.3. የዝናብ መጠን የምግብ ሲናር ስንዴና ገብስ በሚመረትባቸው እርጥብ ቆላ እና ውርጭማ አካባቢዎች የሚመረት ሲሆን ዓመታዊ የዝናብ መጠናቸዉ በአማካኝ 700-1500 ሚ.ሜ ዝናብ በሚያገኙ ስፍራዎች መልማት ይችላል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
103 3.4. የአፈር ዓይነት የምግብ ሲናር በተለያዩ የአፈር አይነቶች ላይ ሲለማ ከአሲዳማ እስከ ኮትቻ (መረሬ) እንዲሁም ለምነቱ በተሟጠጠ የአፈሮች ዓይነቶች ምርት ይሰጣል፡፡ ነገር ግን ዉሃ የሚቋጥር ኮትቻ አፈር ላይ በሚመረትበት ወቅት ትርፍ ዉሃን በቢቢኤም በማጠንፈፍ መዝራት ተገቢ ነው፡፡ ለምግብ ሲናር ተስማሚ የሆነውና ከፍተኛ ምርት የሚሰጠው ለምና ውሃ የማይተኛበት አፈር ተስማሚ ነው፡፡ ሠ ንጠረዥ 1፡-በኢትዮጵያ የምግብ ሲናር የሚመረትባቸው አካባቢዎች ተ.ቁ ክልል ዞኖች ወረዳዎች 1 ኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ፣ፊንፊኔ ደገም፣ግራር ጃርሶ፣ ያያ ጉለሌ፣ ዙሪያ ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ውጫሌ ጅዳ፣ ሱሉልታ፣ በርሄ ምስራቅ ወለጋ አለልቱ ቅምብቢት፣ አብቹ፣ 2 አማራ ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ ወልመራ፣ ጀልዱ፣ ጊንጪ፣ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም አንጎለላ፣ ባሶና አንኮበር፣ ስናን፣ ደባይ ጥላትግን፣ማቻከል፣ ደጋ ሰሜንጎንደር፣ ሰሜን ዳሞት፣ ሰካላ፣ ቋሪት፣ ዳባትና ወሎ፣ ደቡብ ጎንደር ደባርቅ፣ ጋሽና፣ ገረገራ፣ መቂት፣ 3 ትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ‹ ፋርጣ ደጋ ተምቤን፣ እንደርታ፣ ደቡብ ምስ/ዞን 4 ደቡብ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ ሀውዜን፣ ማይጨው ምሁር አክሊል፣ ጉመር፣ ምዕራብ አዘርነት እና ሊሙ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
104 4 . የተሸሻሉ አመራረት ዘዴዎች 4.1. ማሳ መረጣ ለዘር (ለፍሬ) ተኮር ሰብል የሚሆን ማሳ በምንመርጥበት ጊዜ ታሳቢ የምናደርጋቸው ጉዳዮች፡- የአፈሩ ዓይነት ከገንቦሬ እስከ መረሬ/ዋልካ ሊሆን ይችላል፣ የመሬቱ ተዳፋትነት መጠነኛ ቢሆን ውሃ ለማጠንፈፍ ያግዛል፡፡ የማሳው ቀደም ታሪክ መመርመርና በቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ (ሲናር እና ሌሎች መሰል የብርዕ ሰብሎች) ያልተመረቱበት ቢሆን ይመረጣል፡፡ ይኸውም ከተመሳሳይ ዝርያዎች የሚተላለፉ በሽታዎችንና እንደ እንክርዳድ የመሳሰሉ አረሞችን ወረራ ለመከላከል ነው፡፡ ከሰብል ፈረቃ አንጻር እንደየአካባቢዉ ተስማሚነት የጥራጥሬ ሰብሎች (ቦለቄ፣ አተር፣ ባቄላ፣ የእርግብ አተር፣ የላም አተር) ወይንም ጎመንዘር የመሳሰሉት ቢቀድሙ ይመረጣል:: በማሳ መረጣ ወቅት የሚደረገው ጥንቃቄ ምርታማነትን ከመጨምር በተጨማሪ ጥራት ያለው ሰብልን ለማምረት ያስችላል። በተለይም ከማሳው የሚገኘውን ምርት ለሚቀጥለው የሰብል ዘመን ለምርትነት የምንጠቀም ከሆነ በምንም ሁኔታ የምግብ ሲናር በቀዳሚው አመት የተዘራበት ማሳ መዘራት የለበትም። 4.2. የማሣ ዝግጅት ለምግብ ሲናር አዝመራ የሚውል ማሳ ዝግጅት በመሰረቱ በአፈሩ ዓይነት ይወሰናል፡፡ ሲናር በፍሬ ግዝፈቱ እና በአስተዳደጉ እንደ ስንዴ እና ገብስ ተመሳሳይ ስለሆነ የማሳ ዝግጅቱም ተመሳሳይ ነው፡፡ መረሬ አፈር የዝናብ ወቅት ሲጀም ር ዉሃ በብዛት ከማቆሩ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
105 በፊት ማሳውን መላልሶ ማረስና ማለስለስ፣ ከአረም ማጽዳት ያስፈልጋል፡፡ በአንጻሩ ገምቦሬ መሬት በቀላሉ የሚልም ስለሆነ መላልሶ ማረስ ላያስፈልግ ይችላል፡፡ ድንግል መሬት ከሆነ ለሁለቱም የአፈር ዓይነት መላልሶ ማረስና ከተገዳዳሪ አረምና ቁጥቋጦና ጉቶ ማጽዳት ያስፈልጋል፡፡ ረባዳ መሬት ከሆነ የውሃ ማቆርን ለመከላከል ማሳውን አግድም አቋርጦ የሚቀድ ቦይ በማረሻ ጠለቅ አርጎ በመትለም ተፋሰሱን ማመቻቸት ያስፈልጋል፡፡ ማሳው ውሀ የሚተኛበት ከሆነ የውሃ የማንጣፈፊያ ዘዴዎችን ለምሳሌ ሹሩቤ እና ቢቢፍ መጠቀም ያስፈልጋል። የውሀ ማንጣፈፍ ቴክኖሎጅዎችን መጠቀም የሰብሉን እድገት በማገዝ ምርታማነቱ እንዲጨምር የሚረዳ ስለሆነ የምግብ ሲናር አምራቾች ቴክኖሎጅውን እንዲጠቀሙ ይመከራል። ምስል1. የሀገር በቀል የማንጣፈፊያ ምስል2. በማንጣፈፍ ቴክኖሎጅ የተዘራ ማሳ ቦይ ማውጫ (Localy made BBF machine), ሰብሉ ከማሳ ከተነሳ በኋላ (BBF field after har ve s t) የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
106 4.3. ዘር መረጣ የዘር ጥራቱና የዘር ብቅለቱ የተመሰከረለት የምግብ ሲናር ዓይነት ከታማኝ ምንጭ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ በሀገራችን ለም ግብ የሚሆን የሲናር ዓይነት በም ርም ር የመምረጥ ሂደት በጅማሮ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ለጊዜዉ በቅርቡ የተለቀቁ ዝርያዎችን መጠቀም ይቻላል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የተሻሻሉ ዝርያዎችን መጠቀም የሲናር ምርትን እስከ 50% ይጨምራል። በአሁኑ ወቅት የሲናር አምራች ገበሬዎች የሚጠቀሙት ዝርያ ለመኖነት የተለቀቀ በመሆኑ የዘር ምርታማነቱ አነስተኛ ነው። ነገር ግን ለምግብ ሲናርነት በምርምር ማዕከላት የተለቀቁ ዝርያዎች ምርታቸው ከፍተኛ ከመሆናቸው በተጨማሪ የምግብ ንጥረ ነገር ይዘታቸውም ከፍተኛ ነው። ከዘር ምርታቸው በተጨማሪም የገለባ ም ርታማነታቸው ጥሩሩ በመሆኑ አርሶ አደር ቢጠቀማቸው ከፍተኛ ጠቀሜታ ያገኛል። በምርምር ስርአቱ የተለቀቁ እና የተመዘገቡ የምግብ ሲናር ዝርያዎችን በሰንጠረዥ 1 መመልከት ይቻላል። የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
ሠንጠረዥ 2፡-በኢትዮጵያ የዝርያ ምዝገባ ስርዓት የተለቀቁ ተ.ቁ የዝርያዉ ስም ተስማሚ ከፍታ የዝናብ መጠን (ሚ.ሜ) ለመድረስ የሚያስፈልገዉ የዝርያው ፋይዳ የዘር ቀለም ለአገር ውስጥ ፍጆታና ለገበያ የተለ 1 ከፍተኛ ምርት፣ ነጣ ያለ ነጭ ሱራታፍ 150 አሲዳማነትን የሚቋቋም፣ ቡናማ (SORATAF) በሽታን የሚከላከል 2 ጤና (Tena 2266- 750- ከፍተኛ ምርት፣ ነጣ ያለ ነጭ -Souris: 2865 1500 150 አሲዳማነትን የሚቋቋም፣ ቡናማ ነጭ 3 NDሁ9ለ6ገ1ብ161) 2266- 750- በሽታን የሚከላከል ነጣ ያለ (Hulegeb 2865 1500 ቡናማ -Goslin) ከፍተኛ ምርት፣ 150 አሲዳማነትን የሚቋቋም፣ በሽታን የሚከላከል
107 የምግብ ሲናር ዝርያዎች ምርታማነት (ኩንታል በሄከታር) በምርምር በገበሬ ማሳ ማሳ ለቀቁ ዝርያዎች የአበባ ቀለም የተለቀቀበት ዓ.ም. መስራች ዘር ተስማሚ ማብራሪያ ጭ 24-41 ሆለታ በኦሮምያ እና እማራ ክልል 20-40 2009 ሰሜን ሸዋ ዞን - ደብረ ብርሃን ግ.ም.ማዕከል 26.15- 21.96- አዴት በአሲድማነት የሚያጠቃቸው ጭ 2011 የአፈር ይዘት ያላቸው የባንጃ 44.03 41.8 ግ.ም.ማዕከል ፣ ሰከላ፣ ስናን ፋጅ፣ ፋርጣ 26.55- 20.93- አዴት በአሲድማነት የሚያጠቃቸው ጭ 2011 የአፈር ይዘት ያላቸው የባንጃ 50.75 42.40 ግ.ም.ማዕከል ፣ ሰከላ፣ ስናን ፋጅ፣ ፋርጣ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
108 4.4. ዘርን ማከም ሲናር ለፍሬ ሲመረት የእድገት ጊዜው ከብቅለት አስከ ፍሬ ብስለት ረዥም ስለሆነ በዚህ ወቅት በተለያዩ የሻጋት እና የዋግ በሽታዎች ሊጠቃ ይችላል፡፡ ስለዚህ ከበሽታ የጸዳ ዘር ከመጠቀም በተጨማሪ ዘሩን በፀረ-ሻጋት ኬሚካል ማከም የበሽታውን ክስተት ይቀንሳል፡፡ በተለይም በዘር የሚተላለፉ በሽታዎችን እንደ አረማሞ ያሉ በሽታዎችን ለመቆጣጠር ዋነኛ መንገድ ነው። የአረማሞ በሽታን ለመከላከል ፕሮሲድ ፕላስ እና ዳይናሚክን መጠቀም ይቻላል። አጠቃቀሙ 2.5 ኩንታል ዘርን በ200 ግ.ም ኬሚካል በማሸት መጠቀም በዘር የሚተላለፉ በሽታዎችን መከላከል ያስቻላል። 4.5. የዘር ወቅት እንደማንኛውም በዝናብ የሚለማ ሰብል ሁሉ የምግብ ሲናርም የሚዘራው የክረምቱ ዝናብ በአስተማማኝ ሁኔታ መግባቱ ሲረጋገጥ ነው፡፡ ቢሆንም አርሶ አደሩ ካለው ልምድ የረጅም ጊዜ የዝናብ፤ የአየር ሙቀት እና የውርጭ መለዋወጥ አንጻር አመች የዘር ወቅቶችን ለመወሰን የአርሶ አደሩንም ልምድ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በወቅቱ የተዘራ ሲናር የምርት ይዘት (grain yield፣ የፍሬ ክብደት (grain density) እና ምሉዕነት (plumpness) ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ሆኖም የተለያዩ ዓላማዎችን ለማሳካት ከተለመደው የዘር ወቅት ሊቀድም ወይንም ሊዘገይ ይችላል። ተሻሽለው የመጡ ዝርያዎችን ስንጠቀም ዝርያዎችን የሚደርሱበትን ቀን ባገናዘበ ሁኔታ መዘራት ይኖርባቸዋል። የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
109 ሰንጠረዥ 3፡ በዋና ዋና የሲናር አምራች አካባቢዎች የዘር ወቅት አምራች አካባቢዎች የዝናብ ወቅት የዘር ወቅት መካከለኛው ኢትዮጵያ ሚያዚያ ጨረሻ ከግንቦት መጀመሪያ እስከ ሰኔ መጨረሻ ስሜን ምዕራብ ግንቦት መጀመሪያ ከግንቦት መጀመሪያ እስከ ሰኔ መጨረሻ ኢትዮጵያ ሰሜን ኢትዮጵያ ከሰኔ አጋማሽ ጀምሮ ከሰኔ አጋማሽ ጀምሮ 4.6. የዘር መጠን እና አዘራር ዘዴ የዘር መጠን የምግብ ሲናር በብተና ለመዝራት የሚያስፈልገው የዘር መጠን 175 - 200 ኪ.ግ ለአንድ ሄክታር ሲሆን በመስመር ከሆነ እስክ 150 ኪ.ግ በሄክታር ይሆናል። ሆኖም ማሳው ለም ከሆነ፣ የአፈር እርጥበቱ የተስተካከለ ከሆነ፣ የአረም ብዛት ለመቀነስ ከታቀደ ወይንም ዘግይቶ መዝራት ካስፈለገ የዘር መጠኑን በጥቂቱ ከፍ ማድረግ ይቻላል:: በአንድ ሄክታር አስፈላጊውን የዘር መጠን መጠቀማችንን ለማረጋገጥ ከ 20 እስከ 30 ተክሎች በ1 ጫማ ካሬ መብቀላቸውን ናሙና በመውሰድ ማረጋገጥ ተገቢ ነው:: በምርምር ከሚመከረው የዘር መጠን በታችም ሆነ በላይ መጠቀም በምግብ ሲናር ምርታማነት እና ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽኖ ይኖረዋል፡፡ ስለዚህ ጥራት ያለው ዘርና የተሻለ የሲናርን ምርት ለማግኘት ተገቢውን የዘር መጠን መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
110 የዘር ጥልቀት ለዘር በቂ የአፈር እርጥበት ካለ ዘሩ 3-4 ሳ.ሜ ጥልቀት ላይ ይዘራል፡፡ ከዚህ በላይ ዘሩ በአፈር ከተቀበረ የመብቀል አቅሙን ስለሚቀንሰው የሰብሉን አጠቃላይ አቋም ያልተስተካከለ ሲያደርገው ከተጠቀሰው በታች በበቂ ሁኔታ አፈር ካልለበሰ ደግሞ የመወለድ አቅሙን ከመቀነሱም በላይ በደካማ የሆነ የስር እድገት ምክንያት በቀላሉ ሊወድቅ ይችላል፡፡ 4.7 የአዘራር ዘዴ እስከአሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የምግብ ሲናር የሚዘራው በብተና ሲሆን በተቻለ መጠን በብተና ሲዘራ ለሚዘራው ማሳ ተመጥኖ የመጣው ዘር በአግባቡ በተመጣጣኝ መልኩ እኩል መዳረስ ይኖርበታል። በእኩል ተበትኖ የተዘራ ሰብል አላስፈላጊ የእጽዋት ሽሚያን በማስቀረት ጥሩ ምርት እንዲገኝ ይረዳል። ስለሆነም በምርምር የሚመከረውን የዘር መጠን እና አዘራር መከተል ይገባል። የምግብ ሲናር በመስመር በዘር መዝሪያ ማሽን ሲዘራ በእጽዋት መካከል 0.10 ሳ.ሜ እና በመስመር መካከል 20 ሳ.ሜ መሆን ይኖርበታል። ነገርግን በሀገራችን ገበሬ ሁኔታ የተገለጸውን በመስመር መካከል የሚያስፈልገውን የርቀት መጠን መጠበቅ ስለሚያስቸግር ገበሬው በመስመር በሚዘራበት ወቅት በሚከተለው መልኩ መሆን ይኖርበታል። በመስመር በምንዘራበት ወቅት በሬው ለእርሻ ያወጣውን ፈሰስ በመከተል ማዳበሪያው በተጨመረበተ ቦታ ላይ ዘሩን መጥኖ በማንጠባጠብ የዘር ሥራ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
111 ማከናወን ይገባል። በሁለት መስመሮች መካከል 30 ሳ.ሜ እንዲሆን ጠባብ ድግር (30 ሳ/ሜ ስፋት ያለው ድግር) በመጠቀም ገምተን መዝራት ያስፈልጋል፡፡ በሬው በእርሻ ባወጣው መስመር ሲሄድ የተዘራውን ሲመለስ እንዲያለብስው ይደረጋል፡፡ የምግብ ሲናርን በመስመር ለመዝራት የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ይቻላል። • የተለያዩ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እንዲቻል ለምሳሌ አረም፣ ማዳበሪያ በአግባቡ ያለችግር በጎን ለመጨመር እና ማንኛውንም የግብርና ሥራዎችን ለመተግበር እንዲቻል በመስመር መካከል ያለው ስፋት 30 ሳ.ሜ. መሆን አለበት፣ • ታርሶ ለዘር በተዘጋጀው ማሳ ላይ ከ7 - 10 ሳ/ሜ ጥልቀት ያለው ቦይ ማውጣት • በወጣው ቦይ ውስጥ ለምግብ ሲናር ከተመከረው የማዳበሪያ መጠን (ኤን.ፒ.ስ (NPS) እና ዩሪያ በመቀላቀል በተመሳሳይ መልኩ በወጣው መስመር ላይ መጨመር እና አፈር ማልበስ ያስፈልጋል፡ • በተመለሰው አፈር ላይ እንደሚዘራው ለእያንዳንዱ መስመር የሚያስፈልግ ዘር መጥኖ ማዘጋጀት፣ • ለመስመር ተመጥኖ የተዘጋጀውን ዘር በማንጠባጠብ (drilling) መዝራት፣ • ለዘር በቂ የአፈር እርጥበት ካለ ዘሩ ከ3-4 ሳ.ሜ ጥልቀት ላይ ይዘራል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
112 4.8. የማዳበሪያ ዓይነትና መጠን ዩሪያ የምግብ ሲናር የናይትሮጅን ፍላጎት ከዘር ፍሬ ሙሉነት እና ከፍሬ ክብደት ጋር የተሳሰረ እንደሆነ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ ከፍተኛ መጠን (ከ100 ኪ/ግ/ሄክታር በላይ የሆነ ናይትሮጅን) መጠቀም ፍሬ ተሸካሚ ዛላን በማበራከት ለዘር ፍሬ ይዘት አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ ነገር ግን በተቃራኒው የናይትሮጅን መብዛት የዘር ፍሬን ክብደትና የዘር ሙሌትን በመቀነስ በዘር ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያመጣል፡፡ የዘር መዝሪያ ወቅትም ለናይትሮጂን አጠቃቀም፤ አደራረግ፤ ለዘር መሙላትና ጥራት ላይ ተጽዕኖ አለው፡፡ የተሟላ የዘር ፍሬ ጥራት (ሙሉዕነት) ባልዘገየ የዘር ወቅት ከተዘራ እና የናይትሮጅን ልገሳው መጠነኛ ከሆነ ሰብል እንደሚመረት ጥናቶች ያመላክታሉ:: ስለዚህም ዘግይቶ የተዘራ የሲናር ሰብል የዘር ፍሬ ጥራቱን ለመጠበቅ የናይትሮጅን ልገሳው ከመደበኛው እስከ ግማሽ ድረስ መቀነስ እንዳለበት ይመከራል፡፡ በአጠቃላይ ለምግብ ሲናር የናይትሮጅን ማዳበሪያ ልገሳ መጠን ከ 63 ኪ.ግ./ሄክታር የምርት ይዘትና ጥራት አመርቂ እንደሚሆን ይታወቃል፡፡ ይህ ማለት በሄክታር 112 ኪ.ግ ዩሪያ ማዳበሪያ ይሆናል። የናትሮጅን ማዳበሪያ ዩሪያ ( Urea ) አጠቃቀም 1/3ተኛው በዘር ወቅት ሲሆን ቀሪው 2/3ተኛ ሰብሉ በሚወልድበት ጊዜ ወይም ከዘር በኋላ ከ35-45 ቀን ባለው ጊዜ መሆን ይኖርበታል። የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
113 ኤን.ፒ፣ኤስ የኤን.ፒ፣ኤስ. ማዳበሪያ ለምግብ ሲናር ለዘር መጠንና ጥራት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው:: ስለሆነም ከ 23 ኪ.ግ. ፎስፌት/ሄክታር በዘር ጊዜ መጠቀም ይመከራል፡፡ የፎስፌት ማዳበሪያ ምንጭ ኤን.ፒ.ስ (NPS) ሲሆን አጠቃቀሙም 60 ኪ.ግ ኤን.ፒ.ስ በሄክታር በዘር ወቅት መጠቀም ይቻላል። የተፈጥሮ ማዳበሪያ እና ኖራ አጠቃቀም በኢትዮጵያ ለግብርና ስራ ከሚውለው መሬት ውስጥ 43% አሲዳማ አፈር ነው፡፡ አፈሩ አሲዳማ ነው የሚባለው የሀይድሮጅን፣ አሉሙኒየምና ብረት የተባሉት ንጥረ-- -ነገሮች ክምችት ሲበዛና በሌላ በኩል ደግሞ የካልሲየም፣ ፖታሲየም፣ ማግኒዚየም እና የመሳሰሉት ንጥረ-ነገሮች መጠን ሲያንስ ነው፡፡ እስካሁን ባለው ውስን መረጃ መሰረት አሲዳማ አፈሮች በሁሉም የአገራችን አፈር ዓይነቶች የሚገኙ ቢሆንም በብዛት በአሲዳማነት የሚታወቁት የአፈር አይነቶች /እንደ ስፋታቸው መጠን ከከፍተኛው ወደ ዝቅተኛው/ Nitosols,Vertisols, Cambisols, Luvisols, Lithosls, Acrist- tols/ በመባል የሚታወቁት ናቸው፡፡ እነዚህ የአፈር አይነቶች ለም የሆኑና ምርት በመስጠት የሚታወቁ ዋና የእርሻ መሬቶች ናቸው፡፡ በእርግጥ የተጠቀሱት የአፈር አይነቶች የሚገኙባቸው አካባቢዎች ሁሉ አሲዳማ ባይሆኑም የመጀመሪያው Nitosol /ቀይ አፈር/ በመባል የሚታወቀው ግን በአገራችን ካለው የቀይ አፈር መጠን ከ80 በመቶ ያላነሰው አሲዳማ ነው፡፡ አንድ የእርሻ መሬት አሲዳማ መሆኑንና አለመሆኑን የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
114 ለማወቅ በአፈር ምርመራ ላቦራቶሪ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ከዚያም በምክረ-ሃሳቡ መሰረት የታዘዘውን ያህል ኖራ በእርሻ መሬቱ ላይ በወቅቱ መጨመር ያስፈልጋል፡፡ በኢትዮጵያ ከ43% በላይ በአሲዳማነት የሚጠቃ ሲሆን በዚህም ምክንያት ምርት እና ምርታማነት በእጅጉ እየትጎዳ ይገኛል። በእነዚህ አካባቢዎች ምርት እና ምርታማነትን ለማሳድግ አሲዳማነትን በኖራ ማከም ዋነኛው የመፍትሄ አቅጣጫ ነው። ኖራ መጠቀም የመሬቱን የአሲዳማነት መጠን በመቀነስ የሰብሉን እድገት ሰለሚያፋጥን ምርታማነትን ለመጨመር ያስችላል። ስለሆነም በአሲዳማነት የተጠቃ መሬትን ለማከም የአፈሩን የሆምጣጤነት መጠን በመለካት በባለሞያ የሚያስፈልገው የኖራ መጠን መወሰን ይኖርበታል። የአፈር ለም ነትን ለማሻሻል እና የሰብልን ም ርታማነት ለማሳደግ ከሚጠቅሙት ዘዴዎች ውስጥ ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ የማንጠቀም ከሆነ እንደ አማራጭ የማሳውን የአፈር ለምነት ለማሻሻል ከ80-120 ኩ/ል ኮምፖስት በሄክታር መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ 5. የሰብል አመራረት ስርዓት 5.1. ሰብል ፈረቃ (crop rotation) የሰብል ፈረቃ ማለት ቁጥራቸዉ ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰብሎችን ትክክለኛ ዕቅድ በተከተለ መንገድ በአንድ የተወሰነ መሬት ላይ አፈራርቆ ማምረት ነዉ፡፡ ለሰብል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
115 ምርት መቀነስ አንዱ አይነተኛ ምክንያት በአንድ ማሳ ላይ ተመሳሳይ ሰብልን እና በአንድ ምድብ የሚገኙ ሰብሎችን (የብርዕ ሰብሎችን) በማከታተል መዝራት ነው። ሰብልን ማፈራረቅ የአፈር ለምነት ከመጠበቅ በተጨማሪ የቀጣዩን ሰብል (የሲናር) ምርታማነትን ያሻሽላል፡፡ በተጨማሪም ሰብልን ማፈራረቅ የአረም ጥቃት፣ ነፍሳት ተባዮችና አፈር ወለድ በሽታዎች በመቀነስ የሰብል ምርታማነትን ይጨምራል። የምግብ ሲናር ናይትሮጅንን ከአየር የሚሰበስቡ ሰብሎችን (ጥራጥሬ ሰብሎችን) አስከትሎ በመዝራት የሚጨመረው ዩሪያ መጠን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ ስለሆነም ከሲናር በፊትም ሆነ በኋላ የብርዕ ሰበሎችን ከመዝራት ጥራጥሬዎችን ( ባቄላ፣ አተርና ሽም ብራ)፤ ተልባ፣ ኑግ፤ጎመንና ድንች የመሳሰሉትን ሰብሎች መዝራት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያስገኛል:፡ ሲናርን ከነዚህ ሰብሎች ጋር በየሁለት ዓመቱ በማፈራረቅ ዘላቂ ምርታማነትን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ 6. የሰብል ጥበቃ ዘዴዎች 6.1. የአረም ቁጥጥር በተለያዩ ሲናር አምራች አካባቢዎች በከፍተኛ ጎጅነታቸው የተመደቡት አረሞች ግሸ፣ ሽዩ፤ ሙጃና መጭ ሲሆኑ መካከለኛ ጉዳት በማድረስ ቦረን፤ አሽክት፤ የውሻ ሰንደዶ፤ አቀንጭራና ሌሎች ቅጠለ ሰፋፊና የሳር አረሞች ናቸው፡፡ በሚገባ ታርሶ የለሰለሰና ከአረም የጸዳ ማሳ ማዘጋጀት፤ ከአረም ነጻ የሆነ ዘር መጠቀም፤ በመስመርና ቀድሞ መዝራት፤ ከተዘራ ከ18-20 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ በእጅ በመንቀል ማረም አስፈላጊ ነው። እንዲሁም ሁለተኛ አረም ከ30-40 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ሊከናወን የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
116 ይችላል:: የፀረ አረም ኬሚካሎችን ስንጠቀም በምክረ-ሃሳቡ ላይ በተገለጸው መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡ የምግብ ሲናር ከሳር ዝርያዎች አንዱ ስለሆነ የሳር አረም ማጥፊያ ኬሚካሎችን መጠቀም በጭራሽ አይመከረም። ስለሆነም በምግብ ሲናር ላይ የሳር አረም ን ለማጥፋት ብቸኛው መንገድ በእጅ ማረም ብቻ ነው። በም ክረ ሃሳቡ ከተገለጸው ውጭ መጠቀም አረሞች ኬሚካሉን እንዲላመዱ ስለሚያደርጋቸው ለወደፊት የአረም ቁጥጥርን አስቸጋሪ ያደርጋል፡፡ አረምን ለመቆጣጠርና ከአረም የፀዳ ሰብል ለማምረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተግባራት ማከናዎን ያስፈልጋል፡፡ • በሚገባ ታርሶ የለሰለሰና ከአረም የጸዳ ማሳ ማዘጋጀት፣ • ከአረም ነጻ የሆነ እና የጥራት ደረጃው የተመሰከረለት ዘር መጠቀም፣ • በእጅ የሚታረም ከሆነ እንደ አስፈላጊነቱ ከ1-2 ጊዜ ማረም፡፡ • 1ኛ አረም ሰብሉ ከተዘራ 18 - 20 ቀናት ፣ • 2ኛ አረም ከ30 - 40 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ይከናወናል፡፡ በኬሚካል መከላከል ሲናር ከሳር አረም ዘሮች የሚመደብ ስለሆነ በምግብ ሲናር ውስጥ የሳር አረምን ለመቆጣጠር ብቸኛው መፍትሄ በእጅ ማረም ብቻ ነው። ቅጠለ ስፋፊ አረሞችን ለመቆጣጠር 2.4 ዲ መጠቀም የሚቻል ሲሆን አጠቃቀሙም 1ሊትር በ200 ሊትር ውሀ በመበጥበጥ ለ 1 ሄክታር መርጨት ነው። የአረም መድሃኒቱን በምንረጭበት ጊዜ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። በመሆኑም ኬሚካሉን የሚረጨው ሰው የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
117 አስፈላጊ የሆኑ የጥንቃቄ አልባሳትን መጠቀም ይኖርበታል። ማሳሰቢያ፡- ስለኬሚካሉ አጠቃቀም በኬሚካሎች መያዣ ላይ ያለውን መግለጫ በተጨማሪ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡ 6.2. የተባይ ቁጥጥር በኢትዮጵያ በአዝመራ ወቅት በምግብ ሲናር ላይ የሚታይ ተባይ አይነት የሌለ ሲሆን ይህም የሆነው ሲናር የሚመረትበት አካባቢ የመስክ ተባይ የማይታይበት ደጋማው አካባቢ በመሆኑ ነው። በእስካአሁን በተካሄደው ምልከታ በምግብ ሲናር ላይ ያጋጠሙ የተባይ አይነቶች አልተመዘገቡም። አልፎ አልፎ የዝናብ እጥረት በሚከሰትበት ወቅት ክሽክሽ የሚባል ተባይ ሊከሰት ይችላል። ይህን ተባይ ለመከላከል ሴሌክሮን 0.5-0.6 ሊትር ለ1 ሄክታር ወይም ዳይሜትዮይት 2ሊትር ለሄክታር በ200 ሊትር ውሀ በጥብጦ መርጨት ተገቢ ነው። ማሳሰቢያ፡- ስለኬሚካሉ አጠቃቀም በኬሚካሎች መያዣ ላይ ያለውን መግለጫ በተጨማሪ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡ ሲናር ከተሰበሰበ በኋላ ከሚያጠቁት ተባዮች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ነቀዝ፣ ጥንዚዛ፣ የእሳት እራት እና አይጥ ሲሆኑ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ከዚህ ቀጥሎ በሰንጠረዡ ላይ የተጠቀሱትን ዘዴዎች መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን ተባዮች ለመቆጣጠር በሰንጠረዡ ከተቀሱት ዘዴዎች በተጨማሪ ዘመናዊ የእህል ማከማቻ ዘዴ መጠቀም ይቻላል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
118 ሠንጠረዥ፡-4.የጎተራ ተባዮች የመከላከያ እና መቆጣጠሪያ ዘዴዎች የተባይ ዓይነት ባሕላዊ መከላከያ ዘዴዎች ፀረ ተባይ ኬሚካል የመቆጣጠር ዘዴ አክትሊክ25% EC ለ10 ኩንታል ከ16-40 ሚ.ሊ በ1 ወይም 2 ሊትር . ውሃ በጥብጦ መርጨት የጎተራ ንጽህና መጠበቅ እና ነቀዝ፤ ጥንዚዛ፤ ጎተራው ከመሬት ከፍ ብሎ አክትሊክ50% EC ለ10 ኩንታል ከ8-20 ሚ.ሊ የእሳት እራት በደረቅ ሁኔታ ማስቀመጥ በ 1 ወይም 2 ሊትር. ውሃ በጥብጦ መርጨት ዝርያዎች/ species larvae አክትሊክ 2% ዱቄት ከ500 ግራም በአካፋ በመዛቅ ወይም በፀረ ተባይ ማደባለቂያ በርሜል በ10 ኩ/ል እህል ጋር አደባልቆ ማከማቸት ተባዩ መታየት ሲጀምር አሉሚኒየም ፎስፌት ከ2-5 ታብሌት በ10 ኩ/ል እህልን ወይም ጎተራውን ተገቢነቱ በተረጋገጠ መሸፈኛ ሸፍኖ መዝጋት አይጦች ከእርሻ ወደ ጎተራ ላሚራት ባይት (ብሮሚዳየሎን)፤ ክሊራት ፔሌት ውስጥ እንዳይገቡ ጎተራውን በአይጦች ጉድጓድ በመሙላት መንገዳቸው ከማሳው ማራቅ ላይ በእያንዳንዱ 100 ግራም የተዘጋጀውን ኬሚካል ሌሎች እንስሳት በማይገኙበት ቦታ አይጥ የማያስገባ ጎተራ ማድረግ አይጥ መሥራት የአይጥ መከላከያ ቆርቆሮ ዚንክ ፎስፌይድ ከላይ በተገለጸው ሁኔታ ከጎተራው እግሮች ላይ በእያንዳንዱ ላይ 25 ግራም ማድረግ ማድረግ ድመት፤ ወጥመድ መጠቀም፤ ጎተራ ማጽዳት የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
119 ማሳሰቢያ፡- ስለኬሚካሉ አጠቃቀም በኬሚካሎች መያዣ ላይ ያለውን መግለጫ በተጨማሪ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ኬሚካሎች በተጨማሪ ሌሎች ጸረ ተባይ መድሃኒቶችን በግብርና ሚ/ር ም ዝገባ ውስጥ የተዘረዘሩትን መመልከት ተገቢ ነው፡፡ 6.3. የበሽታ ቁጥጥር የሲናር ዋና ዋና በሽታዎች በአውዳሚነት ቅደም ተከተል፡- የቅጠል ሻጋታ (Leaf rust/ Crown rust)፣ የአገዳ ሻጋታ (Stem rust)፣ የገብስ ቢጫ አቀጭጭ ቫይረስ (BYDV)፣ አረማሞ እና የቅጠል ዋግ (Fungal leaf spot) ናቸው፡፡ እነዚህን በሽታዎች ለመከላከል ዓይነተኛው ዘዴ በተፈጥሮ የመቋቋም ባህርይ ያላቸዉና ከምርምር ተቋሞች የሚለቀቁ አዳዲስ ዝርያዎችን ተከታትሎ በመውሰድ መጠቀም ነው፡፡ ሌላው የመከላከያ ዘዴ ለበሽታ መዛመት ሰበብ የሚሆኑ ምክንያቶችን ማስወገድ ነው፤ ለምሳሌ በማሳው ላይ ውሃ መተኛት፣ የሰብል ፈረቃ አለመጠቀም፣ በትክክለኛው ወቅት አለመዝራት፣ የተበከለ ዘር መዝራት የመሳሰሉት ሲሆኑ ለእነዚህ አጋላጭ ክስተቶች እልባት መስጠት የበሽታዎችን ጫና ወይንም ድግግሞሽ ይቀንሳል፡፡ የመጨረሻውና ውድ የሆነው መፍትሔ ደግሞ ጸረ-ሻጋት ኬሚካሎችን መጠቀም (ዘሩን ማከም፣ ሰብሉን መርጨት) ሲሆን ይህም ከአዋጭነት አንጻር መታየት ይኖርበታል፡፡ የሚከተሉትን የኬሚካል መድሀኒቶች መጠቀም ይቻላል። የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
120 • ናቲቮ 0.75 ሊትር በ200 ሊትር ውሃ በመበጥበጥ በአንድ ሄክታር ላይ በመርጨት የቅጠል እና የአገዳ ሸጋታን መከላከል ይቻላል • ሬብሲዶ 0.5 ሊትር በ200 ሊትር ውሃ በመበጥበጥ በአንድ ሄክታር ላይ በመርጨት የቅጠል እና የአገዳ ሸጋታን መከላከል ይቻላል • ፕሮሲድ-ፕላስ በዘር የሚተላለፉ በሽታዎችን በተለይም አረማሞን ለመከላከል አስተማማኝ መድሃኒት ሲሆን አጠቃቀሙም 200ግ.ም ኬሚካል ለ 2.5 ኩንታል ዘርን በማሸት መጠቀም ይቻላል። ምስል 3. የሲናር ክሮውን ረስት በሽታ Puccinia coronata ምስል4. የሲናር አረማሞ - Ustilago avenae የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
121 7. የድህረ-ምርት አያያዝ ዘዴ 7.1. ምርት መሰብሰብ የም ግብ ሲናርን ለመሰብሰብ ከ90 በመቶ የሚሆነው ቅጠል ነጣ ሲልና አገዳው ደግሞ ወደ ነጣ ያለ ቢጫነት/ወርቃማ ቀለም/ ሲለወጥ ሰብሉ መድረሱን የሚያመለክት ነው፡ ይህ የመድረሻ ምልክትን ካሳዬ በኋላ ከ7-10 ባሉት ቀናት መሰብሰብ አለበት፡፡ ሰብሉ በጣም ከደረቀ በኋላ መሰብሰብ በአጨዳ ወቅት ዘለላው የመሰባበርና ፍሬውን የመበተን ባህሪ ስላለው በወቅቱ መሰብሰብ ተገቢ ነው፡፡ የም ግብ ሲናር በባህላዊ እርሻ መሳሪያ በማጭድ ወይም በተሻሻሉ ሞተራይዝድ ማጨጃዎች መሰብሰብ ይቻላል:: በአደጉ ሀገራት ደግሞ ሰብሉን በኮምባይን ሀርቨስተር በመሰብሰብና በመውቃት ምርቱን የማስገባት ስራ ይሰራል፡፡ ምስል 5. በኮምባይን ሀርቨስተር በመሰብሰብ ላይ ያለ ሲናር መሰብሰብ የደረሰ ሲናር ሰብል ማድረቅ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
122 የምግብ ሲናር ከተሰበሰበ በኃላ ወደሚወቃበት አውድማ በማጓጓዝ እስከሚደርቅ ድረስ መከመር ተገቢ ነው፡፡ የተሰበሰበው ሲናር ሲከመር ከመሬት ከ20-30 ሴ.ሜ. ከፍ ብሎ መከመር፤ ለምስጥ ጥቃት እንዳይጋለጥ እና ዝናብ ከዘነበም በእርጥበት ምክንያት ለሻጋታ እንዳይጋለጥ ይረዳል፡፡ ሰብሉ በሚሰበሰብበት ወቅት ያለወቅቱ የሚጥል ዝናብ ከተከሰተ ክምሩ ውሃ እንዳይገባበት ተደርጎ መከመር ይኖርበታል፡፡ ምስል4. የሲናር አረማሞ - Ustilago avenae 7.2. ሰብል መውቃት የምግብ ሲናር በበቂ ሁኔታ መድረቁን ካረጋገጡ በኋላ መዉቃት ይገባል፡፡ ሰብሉን የመዉቃት ሥራ በሸራ እና በአግባቡ በሲሚንቶ የተሠራ አውድማ ላይ መዉቃት ያስፈልጋል፡፡ በተለምዶ ሲናር የሚወቃው በአግባቡ ባልተሰራ አውድማ ላይ ስለሆነ የጥራት ጉድለት ያለው ምርት ስለሚመረት የብክነት መጠኑ ከፍተኛ ነው፡፡ በዉቂያ ጊዜ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ነጥቦች፡- የም ግብ ሲናር ምርት ከአለአስፈላጊ ነገሮች ጋር እንዳይቀላቀል ጥንቃቄ ማድርግና ዘሩም የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
123 እንዳይበተን /እንዳይባክን/ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ምርቱ ከሌሎች የሰብል ዓይነቶችና ዝርያዎች ጋር እንዳይቀላቀል የሚወቃበትን አውድማ ማጽዳትና ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሲናር አብቃይ አርሶ አደሮች ለጤፍ ወይም ለስንዴ መውቂያ አውድማ አሰራርን ባለመከተል በመሬት ላይ አድርጎ መዉቃት የተለመደ በመሆኑ በጥራትም ሆነ በክብደት ላይ ቅነሳ ያስከትላል፡፡ የተሰባበረና የተሰነጣጠቀ ዘር ደግሞ በቀላሉ በተባይና በሻጋታ የሚበላሽ ሲሆን በሚዘራበት ጊዜ ላይበቅል ይችላል፡፡ ምስል7. የምግብ ሲናር በባህላዊ ዘዴ በበሬ ሲወቃ 7.3. ምርት ማከማቸት የም ግብ ሲናር ከተወቃ በኋላ ወደ ጎተራ ከመግባቱ በፊት ከ1-2 ቀን በጸሀይ መድረቅ ይኖርበታል:: ምርቱን ለማድረቅ ንጹህና በአግባቡ የጸዳ ሸራ ወይም ፕላስቲክ ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ ማንኛዉም ለምርት ማስቀመጫ የሚዉል ጎተራም ሆነ ጆን ንፁህና ከነፍሳት ተባይና በሽታ የፀዳ መሆኑን ማረጋገጥ ተገቢ ነዉ፡፡ ምርቱ ወይም ዘር ወደ ጎተራ ከመግባቱ በፊት የዘር እርጥበት መጠን ከ11-13% እስኪደርስ መድረቅ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
124 አለበት፡፡ በደንብ ማድረቅ የዘርን የመሻገት ዕድል የሚቀንስ ሲሆን ድርቀትን በአግባቡ ባለመጠበቅና በክም ችት ወቅት በሚፈጠር እርጥበት ም ክንያት ሻጋታ ቢፈጠር ሪብሲዶ መጠቀም ተገቢ ነው፡፡ ምርቱ ወይም ዘሩ በጆንያም ወይም በሌላ ዕቃ ዉስጥ ከተደረገ በኋላ ማከማቻዎቹ በደረቅ /እርጥበት የሌለበት/ እና በደንብ አየር የሚገባበት ቦታ መቀመጥ አለበት፡፡ ምርቱ በባህላዊ ጎተራ የሚከማች ከሆነ አይጥና አይጠ መጎጥ እንዳይበሉት በእያንዳንዱ የጎተራዉ ቋሚ እግር ላይ በተዘጋጀ ክብ ቆርቆሮ ውስጥ እንዲጠልቅ በማድረግ በጎተራው እግር 45 ሳ.ሜ ከመሬት ከፍ ብሎ በሚስማር መምታት ወይም በሽቦ ማሰር ያስፈልጋል፡፡ በጎተራው ላይ ይህን መከላከያ ለመስራት ካልተቻለ አይጦችና አይጠመጎጦችን በወጥመድና በአይጥ መርዝ መግደል ይቻላል፡፡ የአይጥ መርዝ በምንጠቀምበት ጊዜ መርዙ ከምርቱ/ ወይም ከዘሩ ጋር ንክኪ እንዳይኖረው መጠንቀቅ አለብን፡፡ በጆንያ የተሞላዉ ምርት ወይም ዘር በመጋዘን ለማከማቸት ከታሰበ ጆንዎቹ ከመሬትና ከግድገዳ ጋር እንዳይነካካ በማድረግ ከእርጥበት መከላከል ያስፈልጋል፡፡ ጆንያዎቹ ከግድገዳዉ ቢያንስ አንድ ሜትር ያህል የራቀና በእንጨት ርብራብ ላይ መቀመጥ አለበት፡፡ የቆየዉ /አሮጌዉ/ ምርት ወይም ዘር በተባይ ተበክሎ ከሆነ ወደ አዲሱ ምርት የመዛመት እድል ሊያጋጥመዉ ሰለሚችል አዲስ የተሰበሰበው የምግብ ሲናር ምርት በመጋዘን ከቆየው ጋር ተደባልቆ መከማቸት የለበትም፡፡ በአሁኑ ወቅት በምርምር ማዕከላት የተረጋገጡ አየር የማያስገቡ የብረት ጎተራዎች (meta- al sailo) ለአርሶ አደሮች በመተዋወቅ ላይ ስለሆነ መጠቀም አንዲችሉ ማስተዋወቅ ያስፈልጋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ጎተራዎችን እንደ ም ርቱ መጠን በተለያየ መጠን ማሰራት የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
125 ሲቻል ምርቱን ከተባይና ከእርጥበት በሚገባ የመከላከል የብክነት መጠኑን መቀነስ ይቻላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በገበያ ላይ የሚገኙ አየር የማያስገቡ የፕላስቲክ ከረጢቶች /ሄርሜቲክ ባግ/ መጠቀም የጎተራ ተባዮችን ለመከላከል ጠቀሜታው የላቀ ነው፡፡ በድህረ ምርት ወቅት የሚከሰቱ ነፍሳት ተባዮች ማለትም ነቀዝን ለመከላከል ምርቱን በትከክለኛ ወቅት መሰብሰብ፤ አዘዉትሮ በፀሀይ ማድረቅ፤ መጋዝንን ንፁህ ማድረግ እና ፕሪሚፎስሚታይል አከቴሊክ 2% መጠቀም ተገቢ ነው፡፡ ምስል8. አየር የማያስገቡ የድህረ ምርት ቴክኖሎጂዎች (ከግራ ወደ ቀኝ አየር የማያያስገባ ጆንያ፣ የብረት ጎተራ እና ኮኩን ናቸው) የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
126 የምግብ እና ስርዓተ ምግብ 8. የሰብሉ የምግብ ንጥረ ነገር ይዘት፣አጠቃቀምና ለምግብና ለስርዓተ-ምግብ ዋስትና ያለው አስተዋጽኦ 8.1. የሰብሉ ንጥረ ምግብ ይዘትና ለእለታዊ የምግብ ንጥረ ነገር ፍላጎት ያለው አስተዋፅኦ የምግብ ሲናር ጤናማና ምሉዕነት ያለው የእህል የምግብ ንጥረ ነገር ምንጭ ሲሆን የአሰር፣ የቫይታሚን፣ የማዕድናትና አንቲኦከስዳንት የም ግብ ንጥረ ነገር ም ንጭ ናቸው:: በዚሁ መሰረት ግማሽ ኩባያ (በአማካይ ወደ 78 ግራም አከባቢ) የደረቀ የም ግብ ሲናር እንደ ቅድመ ተከተላቸው መሰረት የምግብ ንጥረ ነገር እለታዊ ፍላጎት በአማካይ 191 በመቶ፣ 41 በመቶ፣ 34 በመቶ፣ 24 በመቶ፣ 20 በመቶ፣ 20 በመቶ፣ 11 በመቶ፣ 10 በመቶ ለማንጋኒዝ፣ ለፎስፈረስ፣ ለማግኒዥም፣ ለመዳብ፣ ለብረት፣ ለዚንክ፣ለፎሌት፣ ለቫይታሚን ቢ-1 (ታይሚን)፣ ለቫታሚን ቢ-5 (ፓንቶቴኒክ አሲድ) እለታዊ ፍላጎት መሟላት አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ የም ግብ ሲናር በሀገራችን በስፋት ጥቅም ላይ ከሚውሉ የተለያዩ የእህል ውጤቶች ጋር ሲነፃፀር የተሻለ የምግብ ንጥረ ነገር ይዘት እንደለው የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡- የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
127 ሰንጠረዥ5 ፡ የም ግብ ሲናር የም ግብ ንጥረ ነገር ይዘት ከሌሎች መደበኛ ሰብሎች ጋር በንፅፅር ሀይል / ፕሮቲን ቅባት ካርቦሀይድሬት አሰር የምግብ አይነት በካሎሪ/ /ግ/ /ግ/ /ግ/ /ግ/ 2.4 የገብስ ዱቄት 370.9 10.1 1.7 78.8 የምግብ ሲናር 8 በቆሎ ዱቄት 303 13 9 51 ጤፍ ዱቄት ነው ወይ 2.1 376 8.1 4.4 76 8 351 13.3 2.4 65.1 ከድህረ ገጽ የተወሰደ ሰንጠረዥ 6፡ የምግብ ሲናር የአሚኖ አሲዲ ይዘት ከሌሎች የእህል አይነቶች አንፃር ሲታይ የምግብ ስንዴ በቆሎ ገብስ ሩዝ የአሚኖ አሲድ አይነት (በ100ግራም ሲናር ፕሮቲን) 5.4 4.6 4.8 5.2 5.2 2.4 2.0 2.9 2.1 2.5 ፌናይል አለኒን 4.2 3.0 3.6 3.6 4.1 ሂስታዲን 7.5 2.3 12.4 6.6 8.6 አይሶሉሲን 4.2 1.2 2.7 3.5 4.1 ላይሲን - 2.4 0.5 1.5 1.4 ሜታዮኒን 5.8 3.6 4.9 5.0 5.8 ቲሪፕቶፋን ቫሊን ምንጭ፡ British Nutrition Foundation Nutrition Bulletin, 2004፡ 29, 111– 142 የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
128 ሩዝ ሠንጠረዥ 7፡ የቅባት ንጥረ ነገር ይዘት የቅባት አይነት (በ ግ/ 100 ግራም ምግብ) የምግብ ሲናር ስንዴ ገብስ ጠቅላላ ቅባት 9.2 1.2 1.2 2.8 ሳቹሬትድ ቅባት 1.61 0.16 0.29 0.74 ሞኖ አንሳቹሬትድ 3.34 0.13 0.14 0.66 ፖሊ አንሳቹሬትድ ቅባት 3.52 0.48 0.70 0.94 ኦሜጋ -6 0.19 0.03 0.94 0.04 ኦሜጋ-3 ምንጭ፡ British Nutrition Foundation Nutrition Bulletin, 2004፡ 29, 111– 142 ሠንጠረዥ 8፡ የቫይታሚን ንጥረ ነገር ይዘት መጠን (በ ግ/በ100 ግ፣ የሰብል ቫይታሚን ኢ ታይሚን ራይቦፍላቪን ኒያሲን ቫይታሚን ፎሌት አይነት (ማ.ግ) ቢ-6 (ማ.ግ) የምግብ 1.5 0.9 0.09 3.4 0.33 60 ሲናር ስንዴ 0.3 0.03 0.03 3.6 0.15 22 ገብስ 0.4 0.4 0.05 4.8 0.22 20 ቦቆሎ 11.3 0.18 0.11 1.7 0.20 3 0.1 0.02 0.02 5.8 0.31 20 ሩዝ ምንጭ፡ British Nutrition Foundation Nutrition Bulletin, 2004፡ 29, 111– 142 የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
ሰንጠረዥ 9፡ የሰብሎች የማዕድን የምግብ ንጥረ ነገር ይዘት 129 የሰብል ሶዲዬም ፖታሲዬም ካልሽዬም ማግንዜዬም ብረት ዚንክ ሴላኒዬም (ማ.ግ) አይነት (ማ.ግ) 3 የምግብ ሲናር 9 3.3 2 350 52 110 3.8 0.6 6 2.9 1 ስንዴ ዱቄት 3 150 140 20 2 2.1 ሩዝ 3 340 38 120 3.9 ገብስ 3 270 20 65 3.0 8.2. ምርቱ ከሥርዓተ-ምግብና ጤንነት አንጻር ያለው ጠቀሜታ የም ግብ ሲናር በውሰጡ በያዘው ዝቅተኛ የሀይል መጠንና ከፍተኛ የግላሲሚክ ኢንዴክስ እና በውሃ የሚሟሙ ቤታ ጉሉታን የተባለ የአሰር አይነት ምክንያት የኮሌስተሮል መጠንን በከፍተኛ መጠን በመቀነስ የልብና የተያያዙ በሽታዎች ለመካለከል አስተዋጽኦ አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የምግብ ሲናር የፕሮቲንና የአሚኖ አሲድ ይዘቱ ከፍተኛ በመሆኑም በቀላሉ የሚፈጭ እና ለህጻናትና ለልጆች ተጨማሪ የምግብ ዝግጅት ለማዘጋት ይጠቅማል፡፡ የምግብ ሲናር የግሉትን ይዘቱ አነስተኛ ከመሆኑ አንጻር በሴላይክ ህመም ለተጠቁ የህብረተሰብ ከፍሎች እንደአማራጭ ምግብ ሊወሰድ የሚችል በመሆኑ ጤናማ ምግብ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ 8.3. የምግብ አዘጋጀጀት እና የተሰባጠረ አመጋገብ ሁኔታ (ሪሲፒ) የምግብ ሲናር በሀገራችን ለተለያዩ ባህላዊና ዘመናዊ የምግብ አይነቶች እንደ ምግብ ግብዓት ጥቅም ላይ የሚወሉ ሲሆን በእንጀራ መልክ፣ በገንፎ፣ በሾርባ፣ በቂጣ፣ በአነባበሮ፣ በሾርባ፣ በጠላና ወዘተ ምግቦችና በመጠጥ አይነቶች መልክ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
130 የምግብ ሲናር የእንጀራ ዝግጅት የጤፍ እንጀራን በምናዘጋጅበት ሂደት ውስጥ የምግብ የሲናር ዱቄት እንደእርሾ በመጠቀም በማቡካት ለእንጀራ ይውላል፡፡ አንድ ሶስተኛ እጅ የሲናር ዲቄት በመጨመር በጤፍ ዱቄት ቡኮ ውስጥ የአብሲት ዝግጅት መጠቀም ይቻላል፡፡ የምግብ ሲናር ቂጣ ደረቅ ቂጣም ሆነ አነባሮ በአብዛኛው የሲናር ዱቄትን በውሃ በማቡካት ትንሽ ጨው ጣል በማድረግ የሚዘጋጅ ሲሆን እንጀራ ሳይኖር እንደአማራጭ የሚቀርብ ይሆናል:: ቂጣ በሀገራችን ከተለያዩ የምግብ አይነቶች ጋር ጥቀም ላይ ሚወሉ ሲሆን እንደ ጎመን፣ ቅቤ በመቀባት፣ ከወተት፣ ከአሬራ፣ ከእርጎ እና ከኑግ ወይም ከተልባ ጋር ለምግብነት የሚቀርቡ ሲሆን የተሰባጠረ አመጋጋብን የሚያበረታታ ስለሆነ ነው፡፡ የምግብ ሲናር አጥሚት በተለያዩ አከባባዎች በተለያዩ ህመሞች ለተጎዱ እና የአጥንት ስብራት ለገጠማቸው እና ለወላድ እናቶች በተለየ መልኩ የሚዘጋጅ ሲሆን በስሱ ታምሶ የተፈጨ የም ግብ ሲናር፣ ስኳር፣ ጨው፣ ቅቤ፣ ተልባ እና መሰል የምግብ ግብዓቶችን በመጠቀምና በማዘጋጀት በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ይሆናል፡፡ የምግብ ሲናር ገንፎ ገንፎ በተለያዩ የሀገራችን አከባቢዎች ለምግብነት ጥቅም ላይ የሚወል ሲሆን የምግብ ሲናርን ለገንፎ ዝግጅት ከተለያዩ የእህል ሰብሎች (የስንዴ ዱቄት፣ በቆሎ፣ ገብስ) የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
131 ጋር በመቀላቀል (1፡1) በማመጣጠን የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡ በሀገራችን በተለምዶ ገንፎ በአመዛኙ ለወላድ እናቶችና ለህጻናት ም ግብነት ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡ የም ግብ ሲናርን በመፈተግ እና በስሱ በመቁላት በማስፈጨት የተዘጋጀውን ዱቄት በፈላ ውሃ ውስጥ ዱቄቱን በመለወስ የሚዘጋጅ የም ግብ ዓይነት ነው፡፡ የተዘጋጀውን ገንፎ ከአርጎ፣ ከቅቤ፣ ከተልባ ድልህ፣ ከማር በመቀላቀል ለምግነት የሚቀርብ ይሆናል፡፡ መሰረታዊ የሲናር ገንፎ (ለልጆቸ ከስድስት ወር ጀምሮ)ግብዓዓቶች ከነመጠናቸው • ሁለት የሾርባ ማንኪያ የሲናር ዱቄት • አንድ ኩባያ ውሃ መጨመርና ለ3 ደቂቃ ማፍላት ሲቀዘቅዝ መመገብ • (ውሃን በወተት መተካት ጠቃሚ ነው) የምግብ ሲናር ከሙዝ ጋር ገንፎ • ከሁለት እስከ ሶስት የሾርባ ማንኪያ የሲናር ዱቄት • አንድ ኩባያ ውሃ መጨመርና ለሶስት ደቂቃ ማፍላት • ሲቀዘቅዝ አንድ ሙዝ ግማሽ ሳህን ላይ በሹኪያ ጫን ጫን በማድረግ መለንቀጥ፤ • የፈላውን ውሃ በሲናር ዱቄት እና በሙዝ ልንቅጡ ላይ በመጨመር መመገብ (በሙዝ ፈንታ ስትሮበሪ፣ ወይም ዘቢብ መተካት ይቸላል) የምግብ ሲናር ከካሮት ጋር ገንፎ • ከሁለት እስከ ሶስት የሾርባ ማንኪያ የሲናር ዱቄት • አንድ ኩባያ ውሃ፤ አንድ ካሮት ሳህን ላይ መፈቅፈቅና ድስት ውስጥ መጨመር • ለሶስት ደቂቃ ማፍላት ሲቀዘቅዝ መመገብ (ካሮትን በዱባ መተካት ይቻላል) የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
132 የምግብ ሲናር ከስፒናች ጋር ጥሬ እቃ መጠን • የምግብ ሲናር ዱቄት 2-3 የሾርባ ማንኪያ • ውሀ አንድ ኩባያ • የተከተፈ ስፒናች 1የሾርባ ማንኪያ • ውሃ ድስት ውስጥ በማብሰል የደቀቀ ስፒናቸ አንድ የሾርባ ማንኪያ ለሶስት ደቂቃ ማፍላትና ሲቀዘቅዝ መመገብ፤ የሲናር- አፕል ገንፎ • ከሁለት እስከ ሶስት የሾርባ ማንኪያ የሲናር ዱቄት • ሁለት ኩባያ ውሃ፤ አንድ አፕል ሳህን ላይ መፈቅፈቅና ድስት ውስጥ መጨመር • ለሶስት ደቂቃ ማፍላት ሲቀዘቅዝ መመገብ የምግብ ሲናር- ቴምር ገንፎ ከሁለት እስከ ሶስት የሾርባ ማንኪያ የሲናር ዱቄት አንድ፡ ኩባያ ውሃ፤ ከሁለት እስከ ሶስት ቴምር ፍረዉን ማሰወገድና በደቃቁ መክተፍና ድስት ውስጥ መጨመር ለሶስት ደቂቃ ማፍላት ሲቀዘቅዝ መመገብ የምግብ ሲናር ጠላ የተለያዩ የእህል አይነቶችን ለጠላና ለተለያዩ ባህላዊ መጠጦች ዝግጅት ግብዓትነት የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
133 መጠቀም እንደሚቻለው ሁሉ የምግብ ሲናርም እንደሌሎች የብርዕና አገዳ ሰብሎች ለዚህ አገልግሎት ይውላል፡፡ 8.4. የምግብ ማቆያና የኢ-ንጥረ ምግብ መቀነሻ ዘዴዎች የምግብ ሲናር እንደማናቸውም የእህል ሰብሎች በተፈጥሮ የተለያዩ ኢ-ንጥረ ምግብ ይዘት ያላቸው ሲሆን በአብዛኛውም እንደ ፋይቴት፣ ታኒን፣ ኦግዛሌት እና መሰል ኢ-ንጥረ ምግብ ይዘት የያዘ ሲሆን መጠናቸውም ከዝርያ ዝርያ የሚለያይ ይሆናል፡፡ እነዚሀም ኢ-ንጥረ የም ግብ ይዘት ከሰብሎቹ የሚዘጋጁትን የም ግብ አይነቶች የመፈጨትና በሰውነት ወስጥ የመዋሃድ ሁኔታን የሚቀንስ ከመሆኑም ባሸገር እንደ ብረትና ዚንክ ያሉ ወሳኝ የማዕድን አይነቶችን የሰውነት አጠቃቀም በከፍተኛ መጠን ይቀንሳሉ፡፡ በመሆኑም የተለያዩ እንደ ማቆንቆል፣ ማብላላት (ፈርመንት ማድረግ)፣ መቀቀል፣ በስሱ መቁላት፣ መጋጋር ያሉ ባህላዊ የምግብ አዘገጃጀቶችን በመተግበርየሰብሎቹን አ-ንጥረ ም ግብ ይዘት መቀነስ ይቻላል፡፡ ሠንጠረዥ 10፡ የም ግብ ሲናር ኢ-ንጥረ ም ግብ ይዘቶች ኢ-ንጥረ ምግብ ይዘት የምግብ ሲናር በቆሎ ስንዴ ሩዝ ፋይቴት (ሚ.ግ/100ግ) ታኒን (ሚ.ግ/100ግ) 278.7 87.2 - 683.2 795-800 93.70 ኦግዛሌት (ሚ.ግ/100ግ) 44.7 48 የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
134 8.5. በምግብ ዝግጅት ሂደቶች ወቅት ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች • የምግብ ሲናርን እንደ ግብዓት በመጠቀም የተለያዩ የምግብ አይነቶች ሲዘጋጁ የምግቡን ጥራትና ደህንነት ለመጠበቅ ንፅህናን መጠበቅ መሰረታዊ እና ቁልፍ ተግባር ነው፡፡ ምግቡ ከሚበስልበት ወይም ከማድቤት ንፅህና አጠባበቅ ጀምሮ፣ የምግቡ ማዘጋጃ ቁስ ንጽህናን መጠበቅ እና የምግብ አዘጋጅ ግለሰብ የግል ንፅህናን መጠበቅን የሚያጠቃልል ተግባር ነው፡፡ በዚህ መሰረት ለምግብነት የሚውሉ የምግብ አይነቶችን የምናዘጋጅ ከሆነ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መርህዎች ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ • የምግብ ማብሰያ ቦታን /ኩሽናን/ ንፅህናውን በመጠበቅና የሚበስለውንም ምግብ ከተለያዩ ባካይ ተባዮች መከላከል፣ • ምግብን የሚያበስሉ ከሆነ የእጆን ጥፍር ማሳጠርና ንጽህናውን በአግባቡ መጠበቅ ያስ ፈ ል ጋ ል፣ • ምግብን ከማዘጋጀት በፊትም ሆነ በዝግጅት ሂደቱ ረዘም በሚልበት ወቅት በምግቡ ዝግጅት ሂደቱ መካከል እጆን በደንብ በሳሙናና በሞቀ ውሃ መታጠብ፣ • ም ግብን ለማዘጋጀት የም ንገለገልባቸውን ቁሳቁሶች በፈላ ውሃ እና በሳሙና በደንብ ካጠብናቸው በኋላ በንፁህ ውሃ በማለቅለቅ በፈላ ውሃ ውስጥ በመቀቀል /ster- ilize/ በአግባቡ ማድረቅ፣ • በማንኛውም መልኩ ምግብን በሚያዘጋጁበት ወቅት ምግቡን በእጅ በቀጥታ ከመንካት ይልቅ እንደ ማማሰያና ማንኪያ ያሉ ቁሶችን መጠቀም፤ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
135 • ፀጉር በተለይ ለሴቶች ረዥም ከሆነ ጠቅልለው በማሰር በሻሽ መሸፈን ይኖርበታል፣ • ምግብ በሚበስልበት ጊዜና ቦታ ትንባሆ አለማጤስ፤ የሚያስነጥስና የሚያስል ከሆነም አፍና አፍንጫን በክንዳችን በመሸፈንና ከም ግቡ ላይ ፊትን ዘወር በማድረግ ማሳል ወይም ማስነጠስ ምግቡን ከብክለት መከላከል ያስችላል፣ • ለምግብ ማብሰያ እቃ ማጠቢያ የሚያገለግሉ የተለያዩ ሳሙናዎች በተቻለ መጠን ከመጠቀማችን በፊት የምግብ ደረጃ እንዳላቸው ማረጋገጥ፤ ከተጠቀምን በኋላ በአግባቡ ማለቅለቅ የማጠቢያው ኬሚካል ቅሪት በእቃው ላይ እንዳይቀር በማድረግ ከምግብ ወለድ በሽታዎች ለመከላከል የሚጠቅሙ መርህዎች በመሆናቸው ተግባራዊ ማድረግ ይመከራል፡፡ • የምግብ ማጓጓዣ፣ መያዣ፣ ማከማቻ፣ ማብሰያ ቦታዎችን እና ቁሶችን በአግባቡ በሞቀ ውሃና የምግብ ደረጃ በያዙ ማጽጃ ኬሚካሎችና ሳኒታይዘሮች ማጠብና በአግባቡ ማለቅለቅ ይመከራል፣ • የማከማቻ፣ መያዥና ማብሰያ ቁሶች አፅድተን ከመጠቀማችን በፊት መድረቃቸውን ማረጋገጥ፣ • ምግብ የሚበስልበትን አካባቢና ኩሽና ቶሎ ቶሎ ማጽዳት፣ • ለማጽዳት የም ንጠቀም ባቸውን እንደ ፎጣና ስፖንጅ ያሉ ቁሶችን ለም ግብ ማብሰያም ሆነ ም ግብ ማቅረቢያ ለማጠብ ከመጠቀማችን በፊት በአግባቡ ማጽዳትና ማድረቅ ይ መ ከ ራ ል፣ • በምግብ ማብሰያ ቦታዎችና ምድጃ ውስጥ የምግብ ተረፈ ምርት/ቅሪት እንዳይቀር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
136 ይመከራል፡፡ ይህም ተረፈ ምግቦቹ ለበሽታ አምጪ ተህዋሲያን መራቢያነት የሚያገለግል በመሆኑ የም ግብ ብክለት በከፍተኛ ደረጃ የሚያጋልጥ በመሆኑ ነው:: 9. ሰብሉን ለማስተዋቅና ለማላመድ የሚከናነወኑ የኤክስቴንሽን ኮሚኒኬሽን ተግባራት፡- • ሰብሉን በማስተዋወቅና ማላመድ ሂደት በሁለት አካት መካከል የሚደረግ ግንኙነት (Two way communication) ተግባራዊ ማድረግ፣ • በአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላትና በሞዴል አርሶ አደሮች ሰርቶ ማሳያ በማካሄድ የቅምሻ ፕሮግራም እንዲኖር በማድረግ፣ • የሰብሉን ከማምረት እስከ መመገብ ያለውን ሂደት ለማሳለጥ ግንባር ቀደም የሆኑ አርሶ/አርብቶ/ከፊል አርብቶ አደር እማወራ እና አባወራ መምረጥና ማስተዋወቅ፣ • የሰው ኃይል ማደራጀትና የባለሙያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና መስጠት፣ • አርሶ/አርብቶ/ከፊል አርብቶ አደር ሥልጠና መስጠት፣ • ሰብሉን ለማምረት የግብዓት አቅርቦት ፍላጎት መፍጠር፣ • በሰብሉ ምርት ላይ እሴት በመጨመር የሚዘጋጁ የተለያዩ የምግብ ዓይነቶችን ማስተዋወቅና የሰብሉን ተፈላጊነት እንዲጨምር ማድረግ፣ • የሰብሉን ምርት በተለያየ መንገድ መጠቀም እንዲችሉ ለማቀነባበሪያ ማዕከላት የማስተዋወቅ ሥራ ማከናወን፣ • በኤግዚቢሽን ማዕከላት ላይ ከሰብሉ የሚዘጋጁ የተለያዩ ምግቦችን ማስተዋወቅ፣ • የምግብ ዐውደ ርእይ በማዘጋጀት እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚዘጋጁ የምግብ አይነቶችን በቅምሻ እንዲተዋወቁ ማድረግ፣ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
137 • የሰብሉን ከማምረት እስከ መመገብ ያለውን ሰንሰለት ለማሳለጥና ለማስረፅ በትላልቅ ሆቴሎች የማላመድ ስራ መስራት • የገበያ ትስስር ከሚመለከተው ጋር መፍጠር፣ • የተለያዩ የመልዕክት የማስተላለፊያ ዘዴዎችን ተጠቅሞ ሰብሉንና ከሰብሉ የሚዘጋጁ ምግቦቸን በሚከተሉት የግንኙነት ዘዴዎች በመጠቀም ማስተዋወቅ፣ o ግላዊ መልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴ፣ o ቡድናዊ የመልእክት ማስተላለፊያ ዘዴ (Group extension method) o የመስክ በዓል ማዘጋጀት፣ o የመገናኛ ብዙሀን ዘዴዎች፣ የህትመት ውጤቶች (ፖሰተር፣በራሪ ፅሁፎችን፣ጋዜጣ…)፤ ዲጂታል የብዙሀን መገናኛ ዘዴዎች (የማህበረሰብ ሬድዮ፣ ኤፍኤም ሬድዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ማህበራዊ ትስስር፣ ድህረ ገፆች…)፣ • የዘር አምራች አርሶ አደሮችን መፍጠርና የዘር አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ጥረት ማድረግ፣ • በአርሶ/አርብቶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት የሰብሉን ሰርቶ ማሳያ ማካሄድና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የልምድ ልውውጥ ማድረግ፣ • የሰብሉን ከማምረት እስከ መመገብ ያለውን ሰንሰለት ለማሳለጥና ለማስረፅ አጋር አካላት ከሞዴል አርሶ አደሮች እና ከግበርና ምርምር ማዕከላት ጋር ተቀናጅተው እንዲሠሩ በማድረግ፤ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
138 • ሰብሉን ከማምረት እስከ መመገብ ባለው ሰንሰለት ከተጠቃሚ ማህበረሰቡ የሚሰጡ ግብረ መልሶችን በማሰባሰብ ለግብርና ምርምር ማዕከላት ማቅረብና ለተፈፃሚነቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ክትትል ማደረግ፣ • የሰብሉን ስርፀት ለማረጋገጥና የህብረተሰቡን አመጋገብ ስርዓት ለማሻሻል ተከታታይነት ያለው ሙያዊ ድጋፍና ክትትል ማካሄድ፣ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
139 10. ዋቢ መጽሀፍት • Hand book of national variety releasing committee, minister of agriculture, 2010 and 2012 printed. • Mebrate Tamrat, Sakatu Hunduma, Tesfahun Alemu, and Medemedemiyaw Neknikie . 2021. Influence of Seeding Rates and NP Fertilization on Quality, Yield and Yield Com- ponents of Food Oats in the Central Highlands of Ethiopia. In Progress report of Agronomy. HARC, Holetta. • Wioletta Biel, Katarzyna Kazimierska , Ulyana Bashutska . 2020. Nutritional value of wheat, triticale, barley and oat grain. Acta Sci. Pol. Zootechnica 19(2) 2020, 19–28 • Fekadu Mosissa, Biadge Kefala and Yadesa Abeshu. Poten- tial of Oats (Avena sativa) for Food Grain Production with its Special Feature of Soil Acidity Tolerance and Nutritional Quality in Central Highlands of Ethiopia. Adv Crop Sci Tech 2018, 6:4. DOI: 10.4172/2329-8863.1000376 • Edouard Lemire, Kate M. Taillon, and William H. Hendershot. 2005. Using pH-dependent CEC to determine lime require- ment። Can. J. Soil Sci. 86: 133–139 የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
140 • የ.ግ.ም.ኢ 2008. የብርዕና አገዳ ሰብሎች አምራረት እና አያያዝ. የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት. አዲስ አበባ. የገጽ ብዛት 131. • African bollworm, <http://infonet-biovision.org/ • Atul Bhargava and Shilpi Srivastava, 2013; Quinoa Botany, Production and Uses, CAB international. • Comai, S., Bertazzo, A., Bailoni, L., Zancato, M., Costa, C., and Allegri, G. (2007). The content of proteic and nonproteic (free and protein-bound) tryptophan in quinoa and cereal flours. Food Chem. 100, 1350–1355. • D. Bazile, D. Bertero & C. Nieto, eds. Rome. FAO & CIRAD. 2015. State of the Art Report of Quinoa in the World in 2013. • E. A. Oelke, D. H. Putnam, T. M. Teynor, and E. S. Oplinger; Quinoa, http://corn.agronomy.wisc.edu/Crops/Quinoa.aspx • FAO Regional Office for Latin America and the Caribbean, Quinoa: An ancient crop to contribute to world food secu- rity, July 2011. • FAOSTAT, Food and agriculture data; http://www.fao.org/ home/en የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
Search
Read the Text Version
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 6
- 7
- 8
- 9
- 10
- 11
- 12
- 13
- 14
- 15
- 16
- 17
- 18
- 19
- 20
- 21
- 22
- 23
- 24
- 25
- 26
- 27
- 28
- 29
- 30
- 31
- 32
- 33
- 34
- 35
- 36
- 37
- 38
- 39
- 40
- 41
- 42
- 43
- 44
- 45
- 46
- 47
- 48
- 49
- 50
- 51
- 52
- 53
- 54
- 55
- 56
- 57
- 58
- 59
- 60
- 61
- 62
- 63
- 64
- 65
- 66
- 67
- 68
- 69
- 70
- 71
- 72
- 73
- 74
- 75
- 76
- 77
- 78
- 79
- 80
- 81
- 82
- 83
- 84
- 85
- 86
- 87
- 88
- 89
- 90
- 91
- 92
- 93
- 94
- 95
- 96
- 97
- 98
- 99
- 100
- 101
- 102
- 103
- 104
- 105
- 106
- 107
- 108
- 109
- 110
- 111
- 112
- 113
- 114
- 115
- 116
- 117
- 118
- 119
- 120
- 121
- 122
- 123
- 124
- 125
- 126
- 127
- 128
- 129
- 130
- 131
- 132
- 133
- 134
- 135
- 136
- 137
- 138
- 139
- 140
- 141
- 142
- 143
- 144
- 145
- 146
- 147
- 148
- 149
- 150
- 151
- 152
- 153
- 154
- 155
- 156
- 157
- 158