Important Announcement
PubHTML5 Scheduled Server Maintenance on (GMT) Sunday, June 26th, 2:00 am - 8:00 am.
PubHTML5 site will be inoperative during the times indicated!

Home Explore በኢትዮጵያ_ፌደራላዊ_ዲሞክራሲያዊ_ሪፑብሊክ_የግብርና_ሚኒስቴር_የኬነዋ፣_የካሚሊና_እና_የምግብ_ሲናር_ኦትስ

በኢትዮጵያ_ፌደራላዊ_ዲሞክራሲያዊ_ሪፑብሊክ_የግብርና_ሚኒስቴር_የኬነዋ፣_የካሚሊና_እና_የምግብ_ሲናር_ኦትስ

Published by Gedion Nigussie, 2022-04-06 04:01:22

Description: በኢትዮጵያ_ፌደራላዊ_ዲሞክራሲያዊ_ሪፑብሊክ_የግብርና_ሚኒስቴር_የኬነዋ፣_የካሚሊና_እና_የምግብ_ሲናር_ኦትስ

Search

Read the Text Version

42 የሰብሉ የምግብ ንጥረ ነገር ይዘት፣አጠቃቀምና ለምግብና ለስርዓተ-ምግብ ዋስትና መረጋገጥ ያለው አስተዋጽኦ 10. የምግብ ንጥረነገር ይዘትና አጠቃቀም ኬነዋ ካለው ጠቀሜታ አንዱ ከፍተኛ የምግብ ንጥረ ነገር ይዘቱ ነው፡፡ ኬነዋ የተሟላ ፕሮቲን፣ አሰር፣ ቅባትና ሌሎች ንጥረ ነገሮችን በመያዝ የታወቀ ሲሆን በሃይል ሰጪነቱ ደግሞ በሃገራችን ከተለመዱት የእህል አይነቶች ጋር ተነጻጻሪ ነው (ሰንጠረዥ 1). ይህ ጥራት ያለው የንጥረ ነገር ይዘቱ በአለም ላይ እየታየ ላለው ከፍተኛ የኬነዋ ፍላጎት አይነተኛ ምክንያት ነው፡፡ ሆኖም ኬነዋ የብዙ የም ግብ ንጥረ ነገሮች መገኛ ቢሆንም ከሌሎች የተለያዩ የም ግብ አይነቶች ጋር እየቀላቀሉ መጠቀም በአጠቃላይ የበለጠ የተሟላ የምግብ ንጥረ ነገሮችን ለማግኘት ይረዳል፡፡ 10.1. ፕሮቲን የኬነዋ ፍሬ/ዘር የፕሮቲን ይዘት እንደ ዝርያው አይነት የተለያየ ሲሆን ከመቶ ከ 13.81 እስከ 21.9 እጅ ይደርሳል፡፡ ይህም ከተለመዱት የእህል አይነቶች ከሚይዙት መጠን ከፍ ያለ ነው:: ከኬነዋ የሚገኘው የፕሮቲን ጥራት ለሰውነት ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚሰጥ ሲሆን ሰውነታችን በራሱ ሊያዘጋጃቸው ስለማይችል የግድ በም ግብ ውስጥ መገኘት የሚገባቸውን ዋናዋና የአሚኖ አሲድ አይነቶችን ጨምሮ ሁሉንም አይነት አሚኖ አሲዶች የያዘ ነው፡፡ ይህም በአለም የምግብ ድርጅት የተቀመጠውን የሰዎች የምግብ ንጥረ ነገር ፍላጎት ደረጃ ለማሟላት የተቃረበ ሰብል ያደርገዋል፡፡ የኬነዋ የአሚኖ አሲድ ይዘት የአለም የምግብ ድርጅት ከ 3 እስከ 10 አመት ለሆኑ ሕጻናት ያስፈልጋል ብሎ ያስቀመጠውን ዝቅተኛ የዋና ዋና አሚኖ አሲዶች መጠን ይበልጣል (ሰንጠረዥ 2)፡፡ በመቶ ግራም ኬነዋ ውስጥ የሚገኘው የላያሲን መጠን ተመሳሳይ ክብደት ባለው በቆሎ ወይም የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

43 ማሽላ ውስጥ ከሚገኘው በአራት እጥፍ የበለጠ ሲሆን በጤፍ፣ በስንዴና በገብስ ውስጥ ከሚገኘው ደግሞ በእጥፍ ይበልጣል (ሰንጠረዥ 3) ፡፡ እንዲሁም የአሚኖአሲድ አይነቶች ላያሲን፣ ሜቲዮኒን፣ ትሪዮኒንና ትሪፕቶፋን ሲሆኑ እነዚህም ኬነዋ ውስጥ በበቂ ሁኔታ ይገኛሉ፡፡ 11.2 የምግብ ቅባት በሰንጠረዥ አንድ ላይ እንደተመለከተው በ100 ግራም ፍሬ ውስጥ በ አማካኝ 6 ግራም ቅባት የሚይዝ ሲሆን ይህም በሃገራችን የተለመዱት እህሎች ከሚይዙት እጅግ የበለጠ ነው፡፡ ቅባት ለሰውነታችን ጉልበት ከሚሰጡ ንጥረ ነገሮች ውስጥ አንዱ ከመሆኑም በላይ በቅባት የሚሟሙ የቫይታሚን አይነቶችን ወደ ሰውነትውስጥ ለማስረጽ ይረዳል፡፡ ኬነዋ ውስጥ ከሚገኘው ጠቅላላ ቅባት ውስጥ ከመቶ ወደ ዘጠና እጅ የሚሆነው አንሳቹሬትድ (ጤነኛ አይነት) ሲሆን ከዚህም ውስጥ ግማሽ የሚሆነው አስፈላጊ የሆኑ ኦሜጋ 6 እና ኦሜጋ 3 የሚባሉት የቅባት አይነቶች ናቸው፡፡ እነዚህ የቅባት አይነቶችን ሰውነታችን በራሱ ሊያዘጋጃቸውስለማይችል የግድ በምንመገበው ምግብ ውስጥ መገኘት አለባቸው፡፡ ኬነዋ በውስጡ ቫይታሚን ኢ የሚባለውን ንጥረ ነገር በመያዙ ምክንያት ከኬነዋ የሚገኝ ዘይት ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ መቆየት ይችላል፡፡ 11.3 ካርቦ ሃይድሬት/ ሃይል ሰጪ በ100 ግራም የእህል ዘር ውስጥከ 60 እስከ 70ግ የሚሆነው ስታርች ነው፡፡ ስታርች ደግሞ ካርቦ ሃይድሬትን በማመንጨት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ በኬነዋ ውስጥ ከ 58 እስከ 68 በመቶ የሚሆነው እስታርች ሲሆን 5 ከመቶ የሚሆነው ደግሞ ስኳር ነው፡፡ በተጨማሪም ካለው ቀስ በቀስ የሚዋሃድ ስታርች ተዳምሮ ኬነዋን በዝግታ ወደ ሰውነት የሚሰርጽ የሃይል ምንጭ ስለሚያደርገው ለጤንነት ተስማሚ ነው፡፡ ይህ የያዘው ከፍተኛጥራት ያለው ስታርችና ዝቅተኛ መጠን ያለው ግሉኮስና ፍሩክቶስ ኬነዋን ዝቅተኛ ግላይሴሚክ ኢንዴክስ ካርቦ ሃይድሬት ያለው ያደርገዋል፡፡ ይህም ማለት ከኬነዋ የሚገኝ ካርቦ ሃይድሬት የደምን የስኳር መጠን አይጨምርም የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

44 ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም ኬነዋ የማይፈተግ የእህል አይነት ስለሆነ (የሚወገድ የዘር ሽፋን ስለሌለው) ተፈትገው ወይም በፋብሪካ ተቀነባብረው ለምግብነት ከሚውሉት ሌሎች የእህል አይነቶች ጋር ሲነጻጸር ሰውነታችን ሊፈጨው የሚችለው በዝግታ ስለሆነ ለረጅም ጊዜ የረሃብ ስሜት እንዳይሰማን ከማድረጉም በላይ የደም የስኳር መጠን ሳይዋዥቅ እንዲቆይ ስለሚያደርግ የሰውነት የጉልበት (ኢነርጂ) ፍላጎትም እንዳይዋዥቅ ያደርጋል፡፡ 11.4 አሰር ኬነዋ ከፍተኛ መጠን ያለው አሰር የያዘ ሲሆን የፍሬው ጠቅላላ ክብደት እስከ 6 ከመቶ ይደርሳል:: ይህ ከፍተኛ የፋይበር ይዘት ምግብ በአንጀት ውስጥ የሚያደርገውን ዝውውር በማፋጠን፣ የኮሊስትሮል መጠንን በመቆጣጠርና አስፈላጊ የሆኑ ባክቴሪያዎች እንዲፈጠሩ በማድረግ የጨጓራ ካንሰርን ለመከላከል ይረዳል፡፡በአጠቃላይ ከእህል የሚሰሩ በተለይ ደግሞ ከኬነዋ የሚዘጋጁ ምግቦች ውሃ የመያዝና ለረጅም ጊዜ ሳይፈጩ የመቆየት ባህሪ ስላላቸው የጥጋብ ስሜትን ስለሚፈጥሩ ቶሎ ቶሎ በመመገብ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ ኬነዋ ዝቅተኛ የግሉተን መጠን ከመያዙም በተጨማሪ በግሉተን ከፍተኛ ይዘታቸው ከሚታወቁት ሰብሎች ጋር ምንም አይነት ቤተሰባዊ ዝምድና የሌለው በመሆኑ በግሉተን ኢንቶለራንስ (አለርጂ) ለሚጠቁ በሽተኞች አዲስ አማራጭ ሰብል ነው፡፡ 11.5 ማእድናትና ቫይታሚኖች በአማካይ ኬነዋ ከጤፍና ከቦለቄ በቀር ከሌሎች ሰብሎች የተሻለ የሚኒራል ይዘት አለው (ሰንጠረዥ 4). ኬነዋ የአማካይ ሰውን የቀን ፍላጎት መሰረት ባደረገ ስሌት በተለይ የብረት፣ የማግኒዚየምና የዚንክ ጥሩ ምንጭ ነው፡፡ ሠንጠረዥ1፡ የኬነዋ የዋና ዋና ንጥረነገሮች ይዘት (በ100 ግራም ውስጥ) ከሌሎች በኢትዮጵያ ከተለመዱ ሰብሎች ጋር ሲነጻጸር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

45 ይዘት መለኪያ ኬነዋ የሰብልአይነት ቦለቄ 399 367 ጉልበት ኪ. ካሎሪ 16.5 ሩዝ በቆሎ ስንዴ 28 ፕሮቲን ግራም 6.3 372 408 392 1.1 ቅባት ግራም 69 7.6 10.2 14.3 61.2 ካርቦሃይድሬት ግራም 2.2 4.7 2.3 80.4 81.1 78.4 ሠንጠረዥ2 ከ3 እስከ 10 ዓመት ለሆኑ ሕጻናት አስፈላጊ ነው ተብሎ በአለም የምግብ ድርጅት ከተቀመጠው ወሳኝ የአሚኖ አሲድ ይዘት አንጻር ኬነዋ ከሌሎች ሰብሎችጋር ሲነጻጸር (koziol(1992) የአለም ምግብ ድርጅት በጠቀሰው መሰረት) ኤፍ.ኤ.ኦሀ የሰብልአይነትለ አሚኖአሲድ አይሶሉሲን መስፈርት ኬነዋ በቆሎ ሩዝ ስንዴ 3.0 4.9 4.0 4.1 4.2 ሉሲን 6.1 6.6 12.5 8.2 6.8 ላያሲን 4.8 6.0 2.9 3.8 2.6 ሜቲዮናይን 2.3 5.3 4.0 3.6 3.7 ፌናይልአላኒን 4.1 6.9 8.6 10.5 8.2 ትሪዮናይን 2.5 3.7 3.8 3.8 2.8 ትሪፕቶፋን 0.66 0.9 0.7 1.1 1.2 ቫሊን 4.0 4.5 5.0 6.1 4.4 ሀየአለም የምግብ ድርጅት እኤአ 2013 በምግብ ውስጥ የፕሮቲን ጥራት እንዴት እንደሚመዘን ካወጣው ጽሁፍ ውስጥ ከ3-10 አመት ለሆኑ ሕጻናት የሚያስፈልገውን ዝቅተኛ የአሚኖ አሲድ መጠን ከሚያሳየው ክፍል የተወሰደ።ለkoziol(1992) ሠንጠረዥ 3 ከወሳኝ የአሚኖ አሲዶች ይዘት አኳያ ኬነዋ በኢትዮጵያ ከተለመዱ ዋና ዋናሰ ብሎች ጋር ሲነጸጸር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

46 የሰብል አይነት ኬነዋ ማሽላ ጤፍ ስንዴ ቦለቄ ገብስ በቆሎ አሚኖአሲድ 0.504 0.309 0.501 0.443 1.031 አይሶሉሲን 0.383 0.248 0.840 1.085 1.068 0.898 1.865 ሉሲን 0.713 0.850 0.766 0.174 0.376 0.359 1.603 ላያሲን 0.391 0.195 0.309 0.145 0.428 0.228 0.351 ሜቲዮናይን 0.202 0.145 0.593 0.441 0.698 0.682 1.263 ፌናይልአላኒን 0.589 0.340 0.421 0.312 0.510 0.367 0.983 ትሪዮናይን 0.356 0.261 0.167 0.106 0.139 0.174 0.277 ትሪፕቶፋን 0.175 0.049 0.594 0.387 0.686 0.564 1.222 ቫሊን 0.515 0.351 0.407 0.167 0.301 0.357 0.650 ሂስቲዲን 0.236 0.211 ሠንጠረዥ 4 የኬነዋ የማዕድንና የቫይታሚን ይዘት በኢትዮጵያ ከተለመዱ ዋና ዋና ሰብሎች የማዕድንና የቫይታሚን ይዘት ጋር ሲነጻጸር ገብስ ነጭበቆሎ ኬነዋ ማሽላ ጤፍ ስንዴ ቦለቄ ሚኒራሎች 32 7 47 12 180 34 240 ካልሲየም 2.68 2.38 4.57 3.14 7.63 3.6 10.44 ብረት 96 93 197 123 184 137 190 ማግኒዢየም 296 272 457 278 429 357 301 ፎስፈረስ 309 315 563 324 427 363 1795 ፖታሲየም 45 5 3 12 2 16 ሶዲየም 2 1.73 3.1 1.63 3.63 2.6 3.67 ዚንክ 0.343 0.23 0.59 0.253 0.81 0.41 0.984 ኮፐር 1.034 0.46 2.033 1.258 9.24 4.067 1.796 ማንጋኔዝ ቫይታሚኖች 0.37 0.246 0.36 0.329 0.39 0.502 0.437 ታያሚን የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

47 ፎሌት 8 25 184 25 44 388 ሪቦፍላቪን 0.114 0.08 0.318 0.061 0.27 0.165 0.146 ኒያሲን 6.269 1.9 1.52 4.496 3.363 4.957 0.479 ቫይታሚንቢ6 0.396 0.37 0.487 0.325 0.482 0.407 0.318 ቫይታሚንኢ 0.57 0.42 2.44 0.5 0.08 0.71 0.21 • በማይክሮግራም ከሚለካው ከፎሌት በስተቀር ልኬቱ በሚሊግራም ነው ኬነዋ በሰንጠረዥ አምስት ላይ ከተመለከቱት ከሁሉም የአገዳና ብርዕ እህሎችና ጥራጥሬዎች የበለጠ ፎስፈረስና ማግኒዚየም የሚይዝ ሲሆን የፖታሲየም ይዘቱ ደግሞ ከሁሉም የአገዳና ብርዕ እህሎች የበለጠ ነው፡፡ በተጨማሪም ከገብስ፣ ከበቆሎ፣ ከማሽላና ከስንዴ የበለጠ ካልሲየም፣ ብረት፣ ዚንክና ኮፐር ይይዛል፡፡ ቫይታሚኖችን በተመለከተ ከሌሎች የአገዳና ብርዕ ሰብሎቸ ጋር ሲነጻጸር ኬነዋ ከፍተኛ ሪቦፍላቪንና ፎሌት፣ ተመሳሳይ መጠን ያለው ታያሚንና አነስተኛ ኒያሲን ይዟል፡፡ በተጨማሪም ምንም እንኳን በዝግጅትና በመብሰል ወቅት መጠኑ ቢቀንስም ኬነዋ ከማናቸውም ሰብሎች የበለጠ ቫይታሚን ኬ ይዟል፡፡ የኬነዋ ቫይታሚን የሚገኘው በዘሩ የውስጠኛው ክፍል ውስጥ ሲሆን ከዘሩ ላይ የሚገኘውን ሳፖኒን የተባለውን ኮምጣጣ ንጥረ ነገር የማስወገድ ሂደት ወቅት አይቀንስም፡፡ 11. የምግብ ዝግጅትና አጠቃቀም 11.1. 12.1 ሳፖኒን የማስወገድ ስራ የኬነዋ ዘር የውጨኛው ክፍል ኮምጣጣ ጣዕም ባለው ሳፖኒን በተባለ ኬሚካል የተሸፈነ ነው:: ሳፖኒን ስሙን ያገኘው ሳሙና (soap) ከሚለው የእንግሊዘኛ ቃል ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት በዉሃ ውስጥ ሲበጠበጥ አረፋ ስለሚሰራ ነው፡፡ ይህ ኬሚካል ከኬነዋ በተጨማሪ በበርካታ በሃገራችን የተለመዱ እንደ አጃ፣ አተር፤አኩሪ አተርና ሽንብራ የመሳሰሉ የሰብል አይነቶች ውስጥም በዝቅተኛ መጠን ይገኛል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

48 ሳፖኒንበተለያዩ ቦታዎች የተቀናጀ የተባይ መከላከያ ግብአት ሆኖ ያገለግላል፡፡ በሃገራችን ደሃና በሚባለው ወረዳ አካባቢ ከተገኘ የአርሶ አደሮች ተሞክሮ ለመረዳት እንደሚቻለው፤ በምግብ ዝግጅት ወቅት በፍተጋም ሆነ በማጠብ ከኬነዋ ዘር ላይ የተወገደ ሳፖኒን የከብቶችን የውጭ ጥገኛ ተባዮችን ለማጥፋት ይረዳል፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ በግለሰብ ደረጃ ሊተገበሩ የሚችሉ ሳፖኒን ማስወገጃ ዘዴዎች ዘሩን በውሃ ማጠብ፣ መፈተግና ሁለቱን ዘዴዎች (ማለትም ማጠብና መፈተግን) ማቀናጀት ናቸው:: በሃገራችን በገጠራማ አካባቢዎች ካለው የዉሃ እጥረት አኳያ ሳፖኒን በዉሃ አጥቦ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ከፍተኛ የሆነ የዉሃ ፍጆታ ያስከትላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ፍተጋ ብቻውን ሊያስወግደው የሚችለው የሳፖኒን መጠን እስከ 95 ከመቶ የሚሆነውን ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ሁለቱን ዘዴዎች በማቀናጀት በአነስተኛ የዉሃ ፍጆታ (ቀሪውን 5 ከመቶ ሳፖኒን ለማስወገድ) የተሻለ ውጤት ለማግኘት ይቻላል፡፡ ኬነዋን በእጥበት ለማስወገድ ከቀዝቃዛ ዉሃ ይልቅ የሞቀ ወይም አሲዳማ (ዉሃ አጋር የተደረገበት) ወይም ኮምጣጣ (ቤኪንግ ሶዳ የተቀላቀለበት) ዉሃ የተሻለ ውጤት ይሰጣል፡፡ ነገር ግን እነዚህን ኬሚካሎች በምን ያህል ብንጠቀም ጥሩ ውጤት እናገኛለን የሚለው ጥናት ይፈልጋል፡፡ በአጠባ ሳፖኒንን በሚጸዳበት ወቅት ዉሃው እየተቀየረ ዘሩ ሲታጠብ አረፋ መስራት ሲያቆም ሳፖኒኑ ታጥቦ ማለቁን ያሳየናል፡፡ም ንም እንኳን በሃገራችን ባይሞከርም በአንዳንድ አገሮች ሳፖኒንን ለማስወገድ ዘሩን በመጠኑ በእሳት ካመሱ በኋላ (ወደ ቡናማ ሲቀየር) ሙቀቱ ሳይለቅ ፈትጎ ማንፈስና ማጠብ (ምስል 45)፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

49 12 34 5 ምስል45. ኬነዋ ባህላ ዊምግብ በሆነባቸው አካባቢዎች የሳፖኒን አወጋገድ ዘዴ፡፡ ከላይ ከግራ ወደ ቀኝ-በእሳት ይታመሳል፤ በጎድጓዳ ድንጋይ ውስጥ በእግር ይፈተጋል፤ ይበራያል፤ይታጠባል፤ይሰጣል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

50 11.2. የምግብ ዝግጅት እስከ አሁን ድረስ በሃገራችን ከኬነዋ ዱቄት የተለያዩ ምግቦችን በማዘጋጀት ለማህበረሰቡ ለማስተዋወቅ ተሞክሯል፡፡ በዚህ መሰረት የኬነዋ ዳቦ፣ ቂጣ፣ ቅንጬ፣ ገንፎና እንጀራ አሰራርን ለማስተዋወቅ ተሞክሯል (ምስል 46)፡፡ በተለይእንጀራ ላይ በተደረገ ጥናት መሰረት ሶስት እጅ የኬነዋ ዱቄት ከ ሰባት እጅ የጤፍ ዱቄት ጋር በመቀላቀል የሚሰራ እንጀራ በጣዕሙና በልስላሴው (መተጣጠፍ መቻል) ሙሉ በሙሉ ከጤፍ ከተዘጋጀ እንጀራ እኩል እንደሆነ አሳይቷል፡፡ ነገር ግን የዚህ ጥናት ዋናው ግኝት ከላይ በተመለከተው መንገድ የተዘጋጀ የኬነዋ እንጀራ በፕሮቲን፣ በቅባትና በጠቅላላ ኢነርጂ (ሃይል ሰጪነት) ይዞታው ከጤፍ ብቻ ከተሰራ እንጀራ እንደሚበልጥ ማሳየቱ ነው፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

51 12 34 56 የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

52 የኬነዋ የምግብ ዝግጅት የሚጀመረው እንደማንኛውም እህል ሁሉ ከእህሉ ጋር የተቀላቀሉትን ቆሻሻዎች በሰፌድ በማነፈስ ወይም በእጅ በመልቀም ነው (ምስል 47-1 እና 2)፡፡ ከዚያም ዘሩ ከመሸክሸኩ በፊት ሳፖኒን ያለበት የዘሩ የውጨኛው ክፍል እንዲሰነጣጠቅና በፍተጋ በቀላሉ እንዲወገድ እህሉ ጸሃይ ላይ እንዲሰጣ ይደረጋል (ምስል 47-3)፡፡ ፀሃይ ሲመታው የሚግል ማስጫ እቃ መጠቀምና የጸኃይ ግለት ከፍተኛ በሚሆንበት ሰዓት ማስጣት ጥሩ ውጤት ያስገኛል፡፡ እህሉ ጸሃይ ከመታው በኋላ እዛው እተሰጣበት ቦታ እንዳለ እየቀነሱ ፀሐይ በመታው ሙቀጫ መሸክሸክ ሳፖኒኑ በቀላሉ እንዲለቅ ይረዳል (ምስል 47-4)፡፡ ኬነዋው በሚገባ ከተፈተገ በኋላ በሰፌድ በማንፈስ ከዘሩ የተላቀቀው ሳፖኒን በንፋስ እንዲለይ ማድረግ (ምስል 47- 5 እና 6)፡፡ እህሉ በሚገባ ከተነፈሰ በኋላ በንፋስ ሊወገዱ የማይችሉ ዘሩ ላይ የተጣበቁ ደቃቅ የሳፖንን ብናኞች ለማስወገድ በንጹህ ዉሃ ማጠብ (ምስል 48- 1):፡የሚቻል ከሆነ፤ በመጀመሪያ ሙቅ ዉሃ መጠቀምና በመቀጠል አረፋው እስኪጠፋ ዉሃውን እየቀየሩ በቀዝቃዛ ዉሃ ማጠብ፡፡ በመቀጠል የታጠበውን እህል በስሱ ጸሃይ ላይ ማስጣትና ቶሎ ቶሎ እያገላበጡ እንዲደርቅ ማድረግ (ምስል 48-2)፡፡ ኬነዋ እርጥበት ሲነካው በቀላሉ የሚበቅል (የሚያጎነቁል) በመሆኑ፤ በስሱ ማስጣትና ቶሎ ቶሎ ማገላበጡ ወሳኝ ተግባር ነው፡፡ እህሉ በሚገባ ከደረቀ በኋላ ቀጣዩ ስራ ወፍጮ ቤት ወስዶ ማስፈጨት ነው፡፡ ተፈጭቶ የመጣውን የኬነዋ ዱቄት በወንፊት መንፋትና አቡኩቶ (ምስል 48- 3 እና 4) ከላይ በተጠቀሰው መሰረት እንጀራ፣ ቂጣ፣ ዳቦና ገንፎ መስራት ይቻላል ፡፡ በምግብ ዝግጅት ወቅት ኬነዋውን ከሌላ እህል ጋር በዱቄትነት ለመቀላቀል ከመሞከር ይልቅ፤ ከመፈጨታቸው በፊት መቀላቀሉ በሚገባ የተዋሃደ ዱቄት ለማግኘት ያስችላል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

53 የእንጀራ አሰራር ጥሬ ዕቃዎች መጠን የጤፍ ዱቄት 1 ኪግ/ 4 ትልልቅ ብርጭቆ የኪነዋ ዱቄት ½ ኪ ግ/ 2 ትልልቅ ብርጭቆ እርሾ 50 ሚሊ/ 4 የሾርባ ማንኪያ ውሃ 3600 ሚሊ /12 ትልልቅ ብርጭቆ አሰራር • ዱቄቶቹ በመንፋት ማቡኪያ ውስጥ መደባለቅ • 4 ½ ትልቅ ብርጭቆ ውሃ በመጨመር በደንብ ማቡካት • እርሾውን በመጨመር ማቡኪያውን መክደን • ለሶሰት ቀን እስኪብላላ መተው • ያቀረረውን ውሃ ማስወገድ • 4 ½ ብርጭቆ ውሃ ማፍላት • 1 ½ ብርጭቆ ሊጥ በ2 ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ ማቅጠን • የቀጠነውን ሊጥ የፈላው ውሃ ውስጥ ጨምሮ ለ 4 ደቂቃ በማማሰል አብሲት ማዘጋጀት • አብሲቱን ወደ ተብላላው ሊጥ መጨመር • የቀረውን ውሃ በመጨመር ሊጡ እንደገና እንዲብላላ ከ2 እስከ 3 ሰዓት በቤት ውስጥ ማስቀመጥ • ምጣዱን ማጋልና እንጀራ መጋገር • እንጀራውን ፤ በሽሮ ወጥ ወይንም በክክ ወጥ ወይንም በስጋ ወጥ አትክልትን ጨምሮ መመገብ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

54 የዳቦ አሰራር ጥሬ ዕቃዎች መጠን • የስንዴ ዱቄት 500 ግ/ 2 ትልልቅ ብርጭቆ • የኪነዋ ዱቄት 125 ግ/ 1/2 ትልቅ ብርጭቆ • እርሾ 12 ግ/ 1የሻይ ማንኪያ • የዳቦ ቅቤ 25 ግ/ ½ የሻይ ማንኪያ • ስኳር 19 ግ/ 1 የሾርባ ማንኪይ • ጨው ለጣዕም • ለብ ያለ ውሃ 450 ሚሊ /1 ½ ትልቅ ብርጭቆ አሰራር • እርሾው ለብ ያለ ውሃ ያለበት ማቡኪያ ውስጥ መጨመር • ዱቄቶቹን በመንፋት ማቡኪያ ውስጥ መጨመር • የተቀሩት ጥሬ እቃዎች ማቡኪያው ውስጥ መጨመር • ላላ ያለ ሊጥ እስኪሆን ማቡካትና ለ30 ደቂቃ ያህል እስኪነሳ (ኩፍ እስኪል) መጠበቅ • ሊጡን በሚፈልገው መጠን ቆራርጦ ፓትራ ላይ ማስቀመጥ • ለአስር ደቂቃ ሙቀት ያለበት ቦታ ማስቀመጥ • በጋለ የዳቦ መጋገሪያ ምጣድ ወርቃማ ቀለም እስኪይዝ ድረስ መጋገር • ከወተት/ እንቁላል/ጭማቂ/እርጎ/ወጥ ጋር መመገብ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

55 ቅንጬ አሰራር መጠን ጥሬ ዕቃዎች 500 ግ/ 2ትልልቅ ብርጭቆ • የኪነዋ ፍሬ 20ሚሊ/ 1/2ትልቅ ብርጭቆ • ዘይት 1500 ሚሊ/ 5 ትልልቅ ብርጭቆ • ውሃ 5 ግራም/ ½ የሻይ ማንኪያ • ጨው አሰራር • ከሳፖኒን የጸዱ የኪነዋ ፍሬዎች ድስት ውስጥ መጨመር • ፍሬዎቹን የሚሸፍን ውሃ መጨምርና የሚንሳፈፉትን ማስወገድ • የተቀሩት ጥሬ እቃዎች ማቡኪያው ውስጥ መጨመር • ፍሬዎቹን እንደገና በደንብ ማጠብ • ውሃውን ማፍላት (5 ትልልቅ ብርጩቆዎች) • ዘይትና ጨው መጨመር • የኪነዋ ፍሬዎቹን የፈላው ውሃ ውስጥ መጨመር • እያማሰሉ ማደባለቅ • ምንም ሳያማስሉ ቅንጬው እስኪደርስ ማብሰል • ከወተት/ እንቁላል/ጭማቂ/እርጎ/አሳ/ቅቤ/ከስጋ ወጥ/ከተቀቀለ ጥራጥሬ ጋር መመገብ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

56 መጠን 250 ግ/ 2ትልልቅ ብርጭቆ ገንፎ አሰራር 20ሚሊ/ 1/2ትልቅ ብርጭቆ ጥሬ ዕቃዎች 1020 ሚሊ/ 5 ትልልቅ ብርጭቆ • የኪነዋ ዱቄት 20 ግ/3 የሻይ ማንኪያ • ዘይት 5 ግራም/ ½ የሻይ ማንኪያ • ውሃ • በርበሬ • ጨው አሰራር • ሰፌድ ላይ ዱቄቶቹ መንፋት • አንድ ሊትር ውሃ ብረት ድስት ውስጥ ማፍላት • ጨውና ዘይት የፈላው ውሃ ውስጥ መጨመር • ዱቄቱን ቀስበቅስ እየጨመሩ ማማሰል • የተቀረውን ውሃ ጨምሮ ብረትድስቱን በመክደን ለ5 ደቂቃ ያህል ማብሰል • እንደገና አልፎአልፎ ማማሰል • ጎድጓዳ ሰሃን ቅቤ ወይንም ዘይት መቀባት • ብረት ድስቱን ከምድጃ ላይ በማውረድ ወደ ጎድጓዳ ሳህን ገንፎውን ማሸጋገር • የቀጠነውን ሊጥ የፈላው ውሃ ውስጥ ጨምሮ ለ 4 ደቂቃ በማማሰል አብሲት ማዘጋጀት • ገንፎውን ቅርጽ ማስያዝና መሃል ላይ ቀዳዳ መስራት • ቀዳዳው ውስጥ በርበሬና ቅቤ/ዘይት መጨመርና ማደባለቅ • ምጣዱን ማጋልና እንጀራ መጋገር • በትኩሱ ከእርጎ ወይንም ሶስ ጋር መመገብ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

57 ቂጣ አሰራር መጠን ጥሬ ዕቃዎች • የእህል ዱቄት 1 ኪግ/ 4 ትልልቅ ብርጭቆ • የኪነዋ ዱቄት ½ ኪ ግ/ 2 ትልልቅ ብርጭቆ • እርሾ 50 ሚሊ/ 4 የሾርባ ማንኪያ • ውሃ 3600 ሚሊ /12 ትልልቅ ብርጭቆ አሰራር • ዱቄቶቹ ነፍቶ በማቡኪያ ውስጥ መደባለቅ • 4 ½ ትልቅ ብርጭቆ ውሃ በመጨመር በደንብ ማቡካት • እርሾውን በመጨመር ማቡኪያውን መክደን • ለሶሰት ቀን እስኪብላላ መተው • ያቀረረውን ውሃ ማስወገድ • 4 ½ ብርጭቆ ውሃ ማፍላት • 1 ½ ብርጭቆ ሊጥ በ2 ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ ማቅጠን • የቀጠነውን ሊጥ የፈላው ውሃ ውስጥ ጨምሮ ለ 4 ደቂቃ በማማሰል አብሲት ማዘጋጀት • አብሲቱን ወደ ተብላላው ሊጥ መጨመር • የቀረውን ውሃ በመጨመር ሊጡ እንደገና እንዲብላላ ከ2 እስከ 3 ሰዓት በቤት ውስጥ ማስቀመጥ • ምጣዱን ማጋልና እንጀራ መጋገር • እንጀራውን ፤ በሽሮ ወጥ ወይንም በክክ ወጥ ወይንም በስጋ ወጥ አትክልትን ጨምሮ መመገብ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

58 2 4 1 3 56 ምስል 47. ከኬነዋ የምግብ አዘገጃጀት ሂደት፡ (1 እና 2) ቆሻሻ ማጽዳት (3) ከሽክሸካ በፊት ጸሃይ ላይ ማሞቅ (4) በሙቀጫና ዘነዘና መሸክሸክ (5 እና 6) ሳፖኒኑን በእጅ በማፈስና በማነፈስ መለየት የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

59 78 10 9 ምስል 48 ከኬነዋ የምግብ አዘገጃጀት ሂደት፡(7) የተነፈሰውን ኬኔዋ በማጠብ ቀሪውን ሳፖኒን ማስወገድ (8) የታጠበው ኬነዋ በስሱ ጸሐይ ላይ ይሰጣል (9) ሲደርቅ ይፈጭና ዱቄቱ ይነፋል (10) ዱቄቱ ከሚፈለገው ዕህል ጋር ተደባልቆ ይቦካል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

II ክፍል ሁለት የካሚሊና (Camelina Sativa) (እማዋይሽ) ሰብል የአመራረት እና የአጠቃቀም ማንዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

61 1 . መግቢያ ካሚሊና ሳቲቫ (Camelina Sativa L) የቅባት እህል ሲሆን፣ ከጎመን ዘር ቤተሰብ ውስጥ (Brassicaceae family) የሚመደብ የሰብል ዓይነት ነው፡፡ ሰብሉ በእንግሊዝኛ ካሜሊና የሚል ስያሜ የያዘ ሲሆን በአማርኛው ደግሞ “እማዋይሽ” በሚል ስም ይጠራል፡፡ ይህ ሰብል በኢትዮጵያ ያልነበረ እና በቅርቡ በሀገር አቀፍ ደረጀ በ2011 እ.ኤ.አ. ወደ ኢትዮጵያ የገባ ሲሆን በ2014 እ.ኤ.አ በግብርና ሚኒስቴር ዘር አጽዳቂ ኮሚቴ ተገምግሞና ጸድቆ በዝርያ መመዝገቢያ መጽሃፍ ተመዝግቦ ዝርያው ተለቋል:: ካሚሊና መነሻው ከወደ አዉሮፓ እና መካከለኛው ኤስያ እንደሆነ እና ለብዙ ሺህ ዓመታት በመልማት የሚገኝ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው፤ ለሰው ልጅ ጤና ተስማሚ እና በቅባት እህልነቱ ተወዳጅ የሆነ ሰብል ነው (Davis, 2011)፡፡ በኢትዮጵያ እስከ አሁን በታዩት ሙከራዎች ሰብሉ በሰፊ ሥነ ምህዳሮች (ከ1600- 3200 ሜትር ከባሕር ጠለል በላይ) እና የአየር ንብረት (ከሞቃታማ እስከ ውርጫማ) ውስጥ ተላማጅ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ በደጋማው አየር ንብረት ደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ወሎ (በሊቦ ከምከም፣ በፋርጣ፣ እስቴ፣ በላይ ጋይንት፣ ዋድላ እና ሰሜን ሸዋ)፤ በቆላማው የስምጥ ሸለቆ (አለምጤና) እንዲሁም በደቡባዊው የሀገሪቱ ከፊል መጠነኛ ኮምጣጣነት ባለው የአፈር አካባቢ (ሀዲያ) ተፈትሾ መልካም ውጤት የሰጠ ሰብል ነው፡፡ ሰብሉ የመሬት ለምነትን በማሻሻል፤ተባይና በሽታዎችን የመቋቋም አቅሙ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

62 የተመሰከረለት እና ውርጭ በሚያጠቃቸው ደጋማ አካባቢዎች ላይ የተሻለ ተላማጅ ሰብል እንደሆነ በተደረጉ የሙከራ ሥራዎች ላይ ታይቷል፡፡ በተጨማሪ ሰብሉን የተራቆተና እርጥበት አጠር መሬት ላይ መልማት የሚችል መሆኑ የተለየ ያደርገዋል፣ (ORDA, Annual report)፡፡ ካሚሊና ከአካባቢዉ ከተለመዱት የቅባት እህሎች የተሻለ ብቅለት፤ እድገትና አቋም ያለው ሲሆን በጥሩ ሁኔታ ያብባል፣ ያፈራል፣ ምርትም ይሰጣል፡፡ እስካሁን በተደረጉ ሙከራዎች ከ12 እስከ 18 ኩንታል ምርት በሄክታር ይሰጣል፡፡ የዘይት ይዘቱም ከ 34 እስከ 44% እና የፋጉሎ ይዘቱ ደግሞ እስከ 43% የሚደርስ ሲሆን ዘይቱም ጤናማ በሆኑ እንደ ኦሜጋ 3 እና 6 የቅባት ንጥረ ነገሮች የበለጸገ (64%) ነው፡፡ የካሚሊና ሰብል 24.5% የፕሮቲን ይዘት ያለውና ለጤና ጠቃሚ ነው፡፡ (PASTER, 2016)፡፡ የማንዋሉ ዓላማና ግብ ዓላማ • የምርትና ምርታማነት ማነቆዎችን በመፍታት የምግብና ሥርዓተ- ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፤ • የካሚሊናን ሰብል ለማምረትና ለመጠቀም አርሶ አደሮች አዳዲስ ቴክሎጂዎችን እና አሰራሮችን በመጠቀም እንዲያመርቱ ምክረ ሀሳቦችን ተደራሽ ለማድረግ፤ • በየደረጃው ያሉ የግብርና ልማት ባለሙያዎችን የካሚሊና አመራረት እና አጠቃቀም የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

63 ዘዴዎችና ቴክኖሎጂዎች ጋር በማስተዋወቅ ለአርሶ አደሩ ያልተቋረጠ ክትትልና የሙያ ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ አቅም ለመገንባት፤ • በካሚሊና ሰብሎች በምርምር የተገኙ አዳዲስ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ ለአርሶ አደሩ እንዲደርሱ እና አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን በማስቻል ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ተፈላጊ የሆኑ ምርቶችን በስፋት እንዲመረቱ ድጋፍ ለማድረግ፡፡ የማንዋሉ ግቦች • በደጋማ አካባቢዎች ተስማሚ የሆኑ አማራጭ የቅባት ሰብል ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮች ለአርሶ አደሮች ተደራሽ ሆነዋል፤ • በተሻሻሉ የአመራረት ዘዴዎችና ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ የካሚሊና ምርት ተመርቷል፤ • ለአግሮ ፐሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ በግብዓትነት የሚውል የካሚሊና ሰብል በመጠንና በጥራት ቀርቧል፡ የማንዋሉ አስፈላጊነት • የካሚሊና ምርት ለሥርዓተ ምግብ ዋስትና የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ፤ • የካሚሊና ሰብል ለሀገር ውስጥ የምግብ ፍጆታ እና ለኢንዱስትሪ ግብዓት ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ፤ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

64 • የካሚሊና ሰብል በሀገራችን ያልተስፋፋ በመሆኑ የተሻሻሉ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ስለሚያደርግ፡፡ • የተሻሻሉ አሰራርና ቴክኖሎጂዎችን ምክረ ሀሳብ በአርሶ/ከፊል እንዲሰርፅ ተከታታይ የሆነ ምክርና ክትትል ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፡ • በዘርፉ ከሚንቀሳቀሱ የምርምርና የተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመስራት በምግብ ሰብል ልማት የሚስተዋሉ የክህሎት ክፍተቶችን መሙላት ማስፈለጉ፤ • የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ዋስትና በማረጋገጥ ጤናማ አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር ማስፈለጉ፤ 2 . የሰብሉ ገጽታና የመላመድ አቅም ካሚሊና ሳቲቫ (Camelina sativa (L) Crantz) እንደጎመን ዘር (Canola & must- tard) ሁሉ የጎመን ቤተሰብ ነው፡፡ ይህ ሰብል እንደ ተልባ የፍሬው አቃፊ ተመሳሳይነት ያለው ነው። ካሚሊና በሜዲቲራኒያን እና ማዕከላዊ ኤሲያ አካባቢዎች የቀደምትነት መገኛ ሥፍራው ሲሆን የዓመታዊ ሰብል ምድብ ውስጥ ይገኛል (Fleenor, richard a. 2011) ፡፡ የፍሬ አቃፊያቸው /ምስል 1/ ከ6-14 ሚ.ሜትር ርዝመት ያለውና ከ8-10 ቢጫ ወይም ቡናማ ቢጫ ፍሬዎችን የያዘ እና አራት ማዕዘን ቅርፅና ሻካራ ገጽታን ያያዘ ነው፣ (ምስል1/MoA, Crop Variety Registration, 2014)፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

65 ምስል1. የፍሬ አቃፊ /እምቡጥ/ ያወጣ እና ካሚሊና ዘር ካሚሊና (እማዋይሽ) በአጭር ጊዜ ፈጥኖ የሚደርስ ዝርያ (ከ100-120 ቀናት) ድርቅንና ከፍተኛ የአየር ሙቀትን እንዲሁም ቅዝቃዜን መቋቋም የሚችልና የፍሬ አቃፊው የማያፈስ ነው፡፡ ብቅለቱም በሳምንት ውሰጥ ይጠናቃቀቃል /ምስል 2/፡፡ (ORDA, website hhtp. www.orda.org.et) ፡፡ ምስል 2 ፡- የካሚሊና ሳቲቫ የብቅለት /ከስድስት ቀን በኋላ/ ሁኔታ በደ/ታቦር ኢትዮጵያ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

66 ካሚሊና በዕድገቱ እስከ 90 ሳንቲሜትር ቁመት ያለው ሲሆን ወደ ደጋማ አካባቢዎች በሄደ ቁጥር ቁመቱ ይጨምራል፡፡ ይህ ሰብል ቅርንጫፍ የሚያወጣና /ምስል 2/ ለስላሳ ወይም ፀጉራማ መሐል ግንድ ያለው ነው፡፡ ቅጠሎቹ የቀስት ቅርጽ ያላቸው ጫፎቻቸው ሹል ሆነው ከ5 እስከ 8 ሳ.ሜ. እርዝመት የሚደርሱና ለስላሳ ጠርዝ የያዙ ናቸው፡፡ አበባቸው በመጠናቸው ትናንሽ ሀምራዊ ወይም አረንጓዴ-ቢጫ እና ባለአራት የቅጠል አቃፊን የያዘና በአብዛኛው በራስ የሚራባ ዘር /self-pollinated/ ያለው ሰብል ነው (ምስል 3:4:5) ፡፡ ምስል3. የካሚሊና የአበባ ገጽታ የሚያሳይ ፎቶ ምስል 4፡- የካሚሊና ሳቲቫ ለመሰብሰብ ሲደርስ የሚያሳየው ገጽታ በአረካ 2011 እ.ኤ.አ/ እና በውጭ ሀገር ካናዳ የተወሰደ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

67 ምስል 5፡ ካሚሊና በአበባ ጊዜ፣ ደቡብ ጐንደር ሊቦ ከምከም 2007 ዓ.ም 3 . የካሚሊና ዋና ዋና ጠቀሜታ ካሚሊና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ያሉት የሰብል ዓይነት ሲሆን፣ በዋናነት የሚሰጣቸው ጥቅሞች እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡ 3.1 ለምግብነት የካሚሊና ሰብል በተለያዩ አዘገጃጀቶች ለተለያዩ ምግብ አይነቶች ግብዓትነትና ማባያነት ያገለግላል፡፡ ዱቄቱ እንደተልባ በውሀ ተበጥብጦ ሌሎች ማጣፈጫዎችን በመጨመር በቀጥታ ለምግብነት መዋል የሚችል ሲሆን፣ እንደ ማባየነት በወጥ መልክ ለመጠቀም ካሚሊናውን እሳት ገባ አድርጎ በመቁላት ወቅጦ ሽሮ ወጥ በሚሠራው ልክ በማዘጋጀት ከዳቦ እና ከእንጀራ ጋር ለም ግብነት መዋልም ይቻላል፡፡ በተለያዩ ም ግቦች የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

68 እንደ ግብዓትነት በተወሰነ መጠን በማቀላቀል የምግቡን ጣዕም እና የንጥረ ይዘት ሁኔታ ማሻሻል ያስችላል። ለምሳሌ በሽሮ እና የእንጀራ ዱቄት ዝግጅት ወቅት ቀላቅሎ በማስፈጨት መጠቀም ይቻላል፣ (ዶክመንተሪ በአማራ መገናኛ ብዙሀን የተሰራ 2007 ዓ.ም 3.2 ለዘይትነት የካሜሊና ዘይት እንደካኖላ ሁሉ በኢንዱስትሪ አብዮት ወቅት ይጠቀሙበት ነበር:: የካሚሊና ሳቲቫ የዘይት ንጥረ ነገር ተመራጭ በመሆኑም የቆይታ ጊዜው ረጅም መሆኑ፣ የመርጋት ችግር የሌለው መሆኑ እና በኦሜጋ-3 እና ኦሜጋ-6 (Omega3-6) የበለፀገ በመሆኑ /ስንጠረዥ1፤ ስእል6// ተመራጭ ያደርገዋል፤ በተለይም በውጭ ዓለም ተወዳጅ ለጤና ተስማሚና ተመራጭ የምግብ ዘይት በመሆኑ በአሜሪካ፣ ካናዳ እና በአውሮፓ በውድ ዋጋ የሚሸጥ ነው፡፡ በካናዳ በተደረገው ጥናት ካሚሊና ከ38- 43% ዘይትና ከ27-32% ፕሮቲን መያዙ ተረጋግጧል ( Ehrensing, 2010) ፡፡ ምስል 6፡- የካሚሊና ዘይት እና ፋጉሎ በሀገር ውስጥ የተመረተ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

69 ካሚሊና የተለያዩ የቅባት ንጥረ ነገሮችን (fatty acid) በመቶኛ የያዘ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ኦሊክ ከ12.8-14.7% ሊንኦሊክ ከ16.3%-17.2% ሊንአሊኒክ ከ36.2-39.4% እና ኤይኮሰኖይክ ከ14-15.5% ይይዛል( Ehrensin g, 2010) ፡፡ ስንጠረዥ1፡ የምርታማነትና ንጥረ ነገሮች ምጣኔ በተለያዩ የቅባት ሰብሎች የቅባት ምርታማነት የምግብ ንጥረ ነገር ይዘት እህል ኦሜጋ አይነት ኩንታል/ የዘይት የፕሮቲን 3 እና 6 አንቲ- የፀረ የባዮ ፉይል ሰሊጥ በሄክተር መጠን/ ቅሪት /% ምንጭነት ተልባ የቅባት ኦክሲዳንት ኮሌስትሮል ሱፍ 7 27 25 ዝቅተኛ 4.5 29 26 አይነቶች ዝቅተኛ መጠን ዝቅተኛ 8 24 23 መካከለኛ መካከለኛ ዝቅተኛ ከፍተኛ መካከለኛ (50%) - መካከለኛ - - ካሚሊና 10.5 34 43 ከፍተኛ ከፍተኛ ከፍተኛ ጥቅሞች 18-45% 12-20% 47% የበለፀገ የበለጸገ የበለጸገ ከፍተኛ የበለጸገ 3.3 ለአማራጭ የኃይል ምንጭነት (ባዮ ፊውል ቴክኖሎጅ) ከሚሊና በውጪው ዓለም የባዩ ፊውል /Bio-fuel/ ምንጭ አቅሙ የተመሰከረለትና ተፈላጊ ምርት እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ በአሜሪካ የአየር ኃይልም ይህንን ዘይትና የባዮ ፊውል /Bio-fuel/ ጥራት ደረጃ በመወሰን የካሚሊና ሰብል በዋናነት በአየር ኃይል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

70 ተቋም የምርምር ሥራ በማከናወን ለአውሮፕላን ዘይት ይገለገሉበታል፡፡ ለባዮ ፊውል አማራጭነት ወደፊትም ሰፊ ጠቀሜታ ያለው እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ፣ (Ehrensi- ing, 2010)፡፡ 3.4 ለእንስሳት መኖነት ከሚሊና ገለባው (ደፈጫው) እና ወደ ዘይትነት ሲቀየር የሚወጣው ተረፈ ምርት (ፋጉሎ) ለእንስሳት መኖነት ያገለግላል፡፡ የፋጉሎው በፕሮቲን ንጥረ ነገር ይዘቱ የበለጸገ (35%) በመሆኑ ለእንስሳትና ለዶሮ መኖነት ዓይነተኛ ጠቀሜታ ያለው ሰብል መሆኑን በሀገራችን በተደረገው ምርምር ተረጋግጧል፡፡ በውጭው ዓለም የካሚሊና ፋጉሎ የተመገቡ ዶሮዎች እንቁላል ጥራት የተሻለ በመሆኑ በገበያ ላይ በልዩነት ይሸጣል፡፡ በሌላ በኩል በሀገራችን በተደረገው ሙከራ ለበግ እና ለፍየል ማድለቢያነት ተፈላጊ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ 3.5. ለንቦች ቀሰምነት ካሚሊና ቢጫማ ቀጫጭን ለዓይን የሚስቡ ብዙ አባባዎች የሚያወጣ ሰብል በመሆኑ በከፍተኛ ደረጃ ንቦች ስለሚወዱት አበባውን በመቅሰም ለማር ዝግጅት ይጠቀሙበታል፡፡ የካሚሊና የዘይትነት ንጥረ ነገር ይዘት ለንቦችም ተስማሚ በመሆኑ በመዓዛው በመሳብ በአበባው ላይ ቆይታ ያደርጋሉ፣ /ምስል 7/ (Camelina product- tion manual, 2010)፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

71 ምስል 7፡ ንቦች ቀስም ምንጭ በዋደላ (ሰሜን ወሎ) 3.6. የመሬት ለምነት ለማሻሻልና ለመጠበቅ ካሚሊና ማዕድን አጠቃቀሙ አናሳ መሆኑ፣ የአፈር እርጥበት መጠበቅና፣ ቅጠሉን መሬት ላይ በማራገፉ የመሬቱን የካርበን ይዘት (organic matter) ስለሚጨምር የአፈሩን ለምነት ያሻሽላል፡፡ በዚህ ረገድም በተደጋጋሚ በስንዴ የታረሰ መሬት በሰብሉ ቢፈራረቅ መሬቱን የተሻለ ምርታማ ያደርገዋል፡፡ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ካሚሊና የተዘራበት መሬት በሚቀጥለው የምርት ዘመን ስንዴ ሲዘራበት ከ15-20% የምርት ጭማሪ እንዳለው ተረጋግጧል፡፡ ይህም በሆሳእና አካካባቢ በተደረገ ሙከራ የተረጋገጠ ሲሆን ለሰፊው የሀገራችን የስንዴ አዝመራ በፍርርቆሽ ውስጥ በመግባት ከፍተኛ የምርታማነትና ጤናማ አመራረት ጥቅም እንደሚያበረክት ይታሰባል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

72 3.7. በረዶ የመቋቋም አቅም በተለያዩ የማለማድ ሥራ በተለይም ደግሞ በአማራ ሊቦ ከምከምና ዋድላ እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ ሆሣዕና ሰብሉ ከ2-3 ጊዜ የበረዶ ጥቃት ደርሶበት ተመጣጣኝ ምርት የሰጠ መሆኑን በ2004 ዓ.ም እና በ2005 ዓ.ም የምርት ዘመን ተረጋግጧል:: አርሶ አደሮች የሰብሉን አቅም ሲገልጹ “ሲያይዋት ደቃቅ ለበረዶ ግን ኃያል” ናት ሲሉ ገልፀዋል፡፡ በተደረጉ የጥናት ሥራዎች ሰብሉ በበረዶ የተለያየ አካሉ ቢቆራረጥም እንደገና በማገገም ተመጣጣኝ ምርት የሚሰጥ ሰብል መሆኑ ታውቋል፣ (Hossahen- na poultry farm cooprative feed back, 2005) and ORDA annual report, 2005)፡፡ 3.8 ኢንዱስትሪያዊ ጠቀሜታ የካሚሊና ምርት ከምግብነት ባሻገር ለቀለም፤ ለቅባት፤ ለዘይት፤ ለኮስሞቲክስ፣ ለማጽጃ፤ ወዘተረፈ…ግብዓትነት ይውላል፡፡ በሀገራችን ማህበረሰቡ ለምጣድ ማሰሻነት ለመጠቀም ተመራጭ ነው (Britton, 2010)፡፡ በተለይም የዘይት ይዘትና ጥራቱን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሰብሉን በማልማት ለኢንደስትሪ ግብዓትነት አይነተኛ አማራጭ የጥሬ ም ርት ግብዓት የቅባት ሰብል ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ተስፋ አለው፡፡ 3.9 ማህበረሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የካሜሊና ሰብል በተለያየ መንገድ በመጠቀም የኢኮኖሚ አቅምን የሚጨምር ሲሆን የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

73 በተለይ ዘይትን በማምረት ላይ ሀገራዊ ፋይዳው ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም ሲባል ከውጭ የሚገባውን ዘይት በመተካት ጤናማ ዘይት ማህበረሰቡ እንዲያገኝ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው:፡ በተጨማሪ በእሴት ሰንሰለቱ ውስጥ ያሉትን ተዋናዮች በየደረጃው ተጠቃሚ ያደርጋል፤የሥራ እድል በቀላሉ ይፈጥራል፤የመሬት ለምነትን በማሻሻል የአፈር ማዳበሪያ ወጪን ይቀንሳል፤ ምርታማነትን በማሳደግ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ይጨምራል (Robert, 2011) ፡፡ 4 . ተስማሚ ሥነ ምህዳር ሰብሉ ከቆላ እስከ ደጋማው አካባቢ ድረስ ሰፊ የመላመጃ ስነ ም ህዳር አለው፡፡ በአማራ ክልል ብቻ በብዙ መቶ ሺዎች ሄክታር ለሰብሉ ተስማሚ መሆኑን ማየት ተችሏል (ካርታ 1) በካርታዉ ማፕ እንደተደረገው በአማራ ክልል ብቻ ከ300 000 ሄክታር በላይ ማሳ አቅም እንዳለ ታይቷል፡፡ 4.1. ከባሕር ጠለል በላይ ከፍታ፡-ሰብሉ ከቆላ እስከ ውርጭ የአየር ንብረት ክልል የመላመድ አቅም ያለው ሲሆን ከ1600 - 3200 የባሕር ጠለል ከፍታ የተሻለ ምርት ጭማሪ እና ሰፊ የመላመድ አቅም ያለው መሆኑ ተለይቷል፡፡ 4.2. የአየር ሙቀት ፡-ለተፋጠነ ብቅለት፣ ለመጀመሪያ እድገት እና ለአበባ ማበብ ከ 25 ዲ/ሴ/ግ እስከ 28 ዲ/ሴ/ግ የአየር ሙቀት ያስፈልገዋል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

74 4.3. የዝናብ መጠን፡ ሰብሉ በዝናብ መልማት የሚችል ሲሆን በእድገት ዘመኑ ከ 500-800 ሚ.ሜ ዝናብ ካገኘ የተሻለና ጥራት ያለው ምርት ይሰጣል፡፡ 4.4. የአፈር ዓይነት፡ አሸዋ ቀመስ ለም አፈር እና ዉሃ በቀላሉ የሚያሰርግ ጥቁር አፈር እና ለም ቡናማ አፈር ይስማማዋል፤ የአፈር ጣዕም / ፒ.ኤች/ 6.0─ 8.0 የሆነ አፈር ለምርታማነቱ ተስማሚ ነዉ፡፡ የአፈር ለምነትን በማሻሻል የምርቱን መጠንና የሥነ ምግብ ይዘት ማሳደግ ያስችላል፣ ካርታ 1፡- የካሚሊና የሰብል ተስማሚ ቦታዎች ካርታ በአማራ ክልል ሽፋን 2007 ዓ.ም /ምንጭ፡ አማራ መልሶ ማቋቋም ድርጅት ባ/ዳር ኢትዮጵያ/ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

75 5. በምርት ላይ ያሉ ዝርያዎች በሀገራችን የካሚሊና ዝርያ በስፋት የሚታወቅ አይደለም። ይሁን እንጂ ላለፉት ጥቂት አመታት በተካሔደ የማላመድ ሥራ ሁለት ዝርያዎች በ2014 እ.ኤ.አ በብሔራዊ ዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ አማካይነት ተመዝግበው ተለቋል (ስንጠረዝ 2) ፡፡ ከእነዚህም ዝርያዎች አንዱ ዝርያ በአርሶ አደር እጅ በሰፊው የደረሰና በምርት ላይ የሚገኝ ነው፡፡ የዝርያው ተስማሚ የዝናብ የዘር ለመድረስ የዘር የዘይት ምርታማነት የተለቀቀበት መስራች ዘር ስም መጠን መጠን ቀለም መጠን (ኩንታል/ሄክታር) ዓ.ም. አራቢ አባዥ ዘይቴ 1 ከፍታ (ሚሜ) የሚያስፈል በምርምር በአርሶ ዘይቴ 2 (ኪ/ግ) ማዕከል 1575- 700- 3300 1250 ገዉ ቀናት ማሳ አደር (እ.ኤ.አ) 1575- 700- 2-4 98 3300 1250 ነጣ ያለ 40-45 ማሳ 2014 ኢ/ግ/ም/ኢ 2-4 93.3 12-16 10-12 ወርቃማ 11-14 9-12 2014 ኢ/ግ/ም/ኢ ፈዘዝ ያለ 40-45 ወርቃማ ሠንጠረዥ 2፡-በኢትዮጵያ የዝርያ ም ዝገባ ሥርዓት የተለቀቁ የካሚሊና ዝርያዎች 5.1. ዘይቴ 1 ይህ ዝርያ በዶ/ር ውድነህ ሊነጫሞ በተባሉ የአካባቢው ተወላጅ ከአሜሪካ ሀገር እንደገባ ይታወቃል፡፡ ሰብሉን በሆሳእና የማይክሮ ዶሮ እርባታ አባላት አማካይነት እንደተላመደና ከግ/ም/ኢ ጋር በመቀናጀት ወደ ዝርያነት የደረሰ እንዲሆን ግንዛቤ አለ:: ዝርያዉ በደቡብ ክልል በሆሣዕና አካባቢ የመመረት አቅም እንዳለዉ በመረጋገጡ በአማራ ክልልም ይህ ዝርያ ለሁለት ዓመታት የማላመድ ሥራና ለ1 ዓመት የዝርያ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

76 ብዜት የተሞከረና የተሻለ ዝርያ መሆኑ ተረጋግጧል (crop variety registration, 2014) ፡፡ 5.2. ዘይቴ 2 ከሶሪያ ሀገር በዶ/ር ስያድ እና ዶ/ር አስናቀ ተግባቦት አማካኝነት ገብቶ ማላመድና ወደ ዝርያነት የደረሰ ሰብል ነው፡፡ ዝርያዉ በአጠቃላይ 120-140 ቀናት የሚደርስ ሲሆን አረንጓዴና በአደራረሱ ከአሜሪካዊ ዝርያ ከ15-30 ቀናት በሆነ ጊዜ ይዘገያል። ሁለቱም ዝርያዎች በአብዛኛው በራስ ጥቅ /Self pollinated/ ዘር /ምስል 8/ ሰብል እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ደግሞ ለሀገራችን አስተማማኝና ለረጅም ጊዜ ምርታማ ሆኖ የሚቀጥል ዝርያ አለው፡፡ ሰብሉ የተሻለ የአልሚ ምግብ ይዘት ያለው እንደመሆኑ አምራቹ ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲያለማቸው የማስተባበር እና የመምከር ሥራ ከግብርና ዘዴ ባለሙያዎች ድጋፍ ማድረግ ይጠበቃል፡፡ ምስል 8. የካሚሊና ዘር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

77 6. የአመራረት ዘዴ የካሚሊና ሰብል አመራረት ከማሳ መረጣ በመነሣት የማሳ ዝግጅት፣ የአመራረት ሥርዓት፣ አዘራር ዘዴ፣ ማዳበሪያ አጠቃቀም፣ ሰብል እንክብካቤ፣ ሰብል ጥበቃ እና የድህረምርት አያያዝን የሚያካትት ሲሆን በዝርዝር ቀጥሎ ተመላክቷል፡፡ 6.1. የማሳ መረጣ እና ዝግጅት ካሚሊና ሰብል ለጎመን ዘር የሰብል ዓይነቶች ተስማሚ የሆኑ የአፈር ዓይነቶች ላይ ሊለማ ይችላል፡፡ የመሬቱም አቀማመጥ ሰብሉ ተዳፋትነቱ (slop) እስከ 4% ያለውን እና ውሃ የማያቁር በጣም ዳገታማ ያልሆነ ማሳ ይፈልጋል፡፡ እንደማንኛውም ሰብል በቂ የሆነ የማሳ ዝግጅት ማለትም በግንቦት፣ በሰኔ እና በዘር ወቅት 3 ጊዜ መሬቱ ታርሶ መለስለስ ይኖርበታል፡፡ የካሚሊና ምርት በሄ/ር ከ16- 27 ኩ/ል እንደሚደርስ ጥናቶች ቢያሳዩም ውሃ በሚተኛባቸው ቦታዎች ምርቱ ከ27-32% ይቀንሳል፡፡ በመሆኑም ከካሚሊና የተሻለ ምርትና ምርታማነት ለማግኘት የቦታ ተስማሚና ትክክለኛ የማሳ መረጣ ማድረግ የሚጠበቅ ይሆናል፣ (Robert, 2011)፡፡ ተዳፋታማ (ከ4% በላይ) ስፍራ ላይ ሰብሉ በቀላሉ በጎርፍ ስለሚወሰድ ምርታማነት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ አለው፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

78 6.2. የዘር ወቅት በኢትዮያ በዋናው የመኸር የዘር ወቅት ከሰኔ 20 እስከ ሐምሌ 10 ድርስ ባሉት ቀናት ተስማሚ መሆኑ በማላመድ ሥራ ተለይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ተለያይነት ባላቸው አካባቢዎች እየታየ ማስተካከል ይቻላል፡፡ ካሚሊና በበልግ እና በመስኖ ሊመረት የሚችል እምቅ አቅም ያለው ሰብል መሆኑን ግንዛቤ የተወሰደ ሲሆን ወቅቱን በተመለከተ እንደየአካባቢው የተወሰነ ልዩነት ሊኖረው ይችላል፡፡ 6.3. የዘር መጠንና አዘራር ዘዴ የካሚሊና ዘር መጠን ትንንሽ በመሆኑ ለአንድ ሄ/ር ከ 6-8 ኪሎግራም በቂ ሲሆን የዘር ጥልቀቱ ከ2-3 ሳንቲሜትር በማድረግ በስሱ አፈር በማልበስ መሸፈን ያስፈልጋል፡፡ ዘሩን በብተና ወይም በመስመር መዝራት ይቻላል፡፡ ካሚሊና በመስመር ሲዘራ በሰብሎች መካከል 10 ሳንቲ ሜትር እና በመስመር መካካል 30 ሳንቲሜትር ርቀት በመጠበቅ የመስመሩን ትልም በመከተል ዘር በመዝራት ቡቃያው 2-3 ቅጠል ሲያወጣ /ምስል 2/ እንደ አስፈላጊነቱ ማሳሳት ይገባል፡፡ በተለያዩ አየር ንብረት አካባቢዎች የብቅለት ቀናቱ ሰብሉ በሚያገኘው አየር ሙቀት መጠን ላይ የሚወሰን ነው፡፡ በአጠቃላይ የካሚሊና ሰብል ከተዘራ 4ኛው ቀን ጀምሮ ብቅለት በማሳየት ከ7-9 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ በሙሉ ይበቅላል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

79 በመስመር ሲዘራ ዘር በአግባቡ መጠቀም ያስችላል፤ የተሻለ ምርት ይሰጣል፤ ተክሉ በቂ የአየር እና የፀሐይ ብርሃን ያገኛል፤የተባይ መስፋፋትን ይቀንሳል፤ አረም፤ተባይና በሽታን ለመቆጣጠር ያመቻል በተጨማሪም ሰብሉን ለመንከባከብ እና ምርታማነትን ለመጨመር ይረዳል:፡(ምስል 4) 6.4. የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀም ዘዴ ካሚሊና በተለያዩ የአፈር ዓይነቶች የሚለማና ለማዳበሪያ አጠቃቀም ምላሽ በመስጠት በኩልም እንደ ካኖሎና እና ጎመን ዘር ተመሳሳይነት ባሕርይ ያለው ሰብል ነው፡፡ ለምነት ባጠራቸው አፈር ዓይነቶች ላይ፡- በዕድገቱ ወቅት 100 ኪ.ግ ኤን.ፒ.ኤስ፤ 75 ኪሎ ግራም ዩሪያ በሄ/ር ሲሆን፤ ዩሪያውን ግማሹን በዘር ወቅት እና ሁለተኛውን ግማሽ በ30 ቀን ልዩነት መጨመር ያስፈልጋል:: ይህንንም ከምስል 10 የምናየው የሰብል ሁኔታ ልዩነቶቹን ያሳያል፡፡ የሰው ሰራሽ ቅይጥ ማዳበሪያ በምክረ ሐሳቡ መሠረት መጠቀም የሰብሉን እድገትና የምግብ ንጥረ ነገር ይዘቱን ያሻሽላል፣ (Debretabor university progress rep- port, Annual 2010) ፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

80 ምስል 10. ካሚሊና በመስመር በምርምር 0 ናይትሮጂን ከመሀል የሚታየው ሆኖ በስተግራ 100ኪ. ግና በስተቀኝ 75 ኪ.ግ ናይትሮጂን የተሰጠው ሰብል በማሳ ውስጥ ሲታይ፣ /በግብርና ሚኒስቴር ሰርቶ ማሳያ 2011 ዓ.ም/ የማዳበሪያ አጠቃቀም ውጤታማነቱ፡- በማሳ ዝግጅት ጥራት፣ ተስማሚ የሰብል ዝርያ መረጣ፣ በወቅቱ መዘራት፣ የአዘራር ዘዴው፣ የተክል ቁጥር በማሳ ስፋት ተመጣጥኖ መገኘት፣ በቂ የእርጥበት ሁኔታ መኖር፣ የሰብሉ ደህንነት ከአረም፣ ነፍሳት ተባይና በሽታ የፀዳ መሆን፣ ተመጣጣኝ የሆነ የማዳበሪያ መጠን አቅርቦትና የአጨማመሩ ተገቢነት የተመሠረተ ነው፡፡ በአጠቃላይ የካሚሊና ሰብል በምርት ውጤቱ ላይ በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ ማዳበሪያ ጥሩ ምላሽ የሚሰጥ ሲሆን በሌሎች ሀገራት የተፈጥሮ ማዳበሪያ ከሰው ሠራሹ ማዳበሪያ ጋር በማቀናጀት በሰብሉ ምርት እና በዘይት ይዘት መጠኑ ላይ አዎንታዊ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

81 7. የሰብል አመራረት ሥርዓት ሰብል ፈረቃ፡-ካሚሊና ከተለያዩ የብርዕና አገዳ ሰብሎች ጋር በማፈራረቅ የተባይ እና በሸታ ጥቃት እንዳይኖር ከመከላከሉ ባሻገር የምርት መጠኑ እና የምግብ ንጥረ ነገር ይዘት እንዲሻሻል ይረዳል፡፡ በመስክ ምልከታ ረገድ ከካሚሊና ቀጥለው የሚዘሩ ብርዕ ሰብሎች (ስንዴ) ምርታማነቱና የምርት ጥራቱ እንደተሻሻለ አርሶ አደሮች ፡፡ ይህም በዋነኝነት የካሚሊናው ምርት ሲደርስ ቅጠሉ ሙሉ ለሙሉ በመርገፍ ከአፈሩ ጋር ስለሚዋሐድ የአፈሩን ለምነት በማሻሻሉ እንደሆነ አመላካች ነው፡፡ ለተከታዩም ሰብል ትቶት የሚያልፈው የሰብሉ ተረፈ ምርት በማሳው ላይ በመበስበስ የማሳውን አፈር ስትራክቸር በማሻሻል ውሃ የመያዝ አቅሙን ያሳድጋል፡ ዳግም ሰብል ልማት፡- ሰብሉ በባሕርይው እርጥበት አጠር ሁኔታዎችን ስለሚቋቋም ከተለያዩ ሰብሎች ጋር በማጎዳኘት ለዳግም ሰብል ልማት እምቅ አቅም እንዳለው ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም በሀገራችን የሰብሉ መድረሻ ጊዜ በአማካኝ ከ100 እስከ 120 ቀናት መሆኑ በምርምር የተረጋገጠ ሲሆን፤ በሌላው ዓለም ይህንን የመድረሻ ጊዜ በመጠቀም ለምሳሌ ከስንዴ ወይም ሌላ ብርእ ሰብል ጋር የዳግም ሰብል ልማት አማራጭ ሆኖ ይሰራበታል፣ (Robert, 2010)፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

82 8 . ሰብል ጥበቃ 8.1 አረም ቁጥጥር ካሚሊና በብቅለት ጊዜው ማሳው ከአረም የፀዳ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የቡቃያ ዕድገቱን ከጨረሰ በኋላ በተፈጥሮዉ ፈጥኖ ማሳውን በመሸፈን በራሱ ጊዜ አረምን የመከላከልና የመቆጣጠር አቅም ያለው ሰብል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በመጀመሪያዎቹ የብቅለት ሳመንታት አረምን የመቋቋም አቅሙ ደካማ ስለሆነ ከበቀለ 15 ቀን ጀምሮ በየ10 ቀን ልዩነት ከ2-3 ጊዜ ሊታረም ይገባዋል ፡፡ ካሚሊና በተዘራበት ማሳ የአረም ተግባር በጊዜው በትኩረት ማከናወን የሚጠበቅ ዐበይት ጉዳይ ነው፡፡ በመጀመሪያዉ አረምና በሁለተኛዉ የአረም ወቅት አብሮ መኮትኮት የበለጠ ቅርንጫፍና ዛላዉን በመጨመር በምርታማነት ላይ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ 8.2. እጽዋት በሽታና ቁጥጥር ዘዴ ካሚሊና በአጠቃላይ በሽታ እና ነፍሳት የመቋቋም አቅም ያለው ሰብል ነው፡፡ ይሁን እንጂ ካሚሊና በምርት ሂደት ከአየር እና አፈር እርጥበት ጋር በተያያዘ እስካሁን በኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ በማሳ ላይ እንዳለ ነጭ አመዳይ (mildew) በሽታ በታችኛው የቅጠል ገጽታ፣ ግንድና ፍሬ አቃፊው ላይ /ምስል 11 ና 12 / በሽታው ሊከሠት ይችላል:: ስለሆነም የበሽታው ጥቃት እንዳይስፋፋ በተቻለ መጠን እርጥበትን የመቆጣጠር ሥራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

83 ምስል 11. በዳዎን ሚልዲው የተከሠተበት ካሚሊና ግንድና ዘር አቃፊ ምስል12. ነጭ ዋግ የተከሠተበትን የካሚሊና ቅጠል የሚያሳይ ፎቶ የካሚሊናን አረምና በሽታ በመከላከል ሂደት በማሳና በክምችት ሁኔታ ርጭት ላይ የሚውሉ ፀረ ተባይ ኬሚካሎች አጠቃቀም በአግባቡ በዕውቀትና ክህሎት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በማሳ ላይ ሆነ በማከማቻ መጋዘን የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

84 የሚደረጉ ርጭቶች ጥንቃቄ ካልተደረገባቸው በምርቱ ላይ ከተፈቀደው በላይ የኬሚካል ክም ችት Minimum Recommendation Level (MRLs) በመፍጠር በሰው ጤና ላይ የሚያስከትሉት አደጋ የከፋ እና የአልሚ ምግብ ይዘቱን የሚቀንስ ይሆናል፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ በሀገራችን በሰብሉ ላይ የተከሠቱ ነፍሳት ተባዮች የሉም፡፡ ዳሩ ግን የአይጥ እና የወፍ ጥቃት ይከሰትበታል፡፡ 9. የሰብል አሰባሰብና ድህረ ምርት አያያዝ ዘዴ የድህረ ምርት አያያዝ ችግር የምርት መጠንና ጥራት ደረጃን በማውረድ እንዲሁም የምረቱን ጣዕም መቀየርና የንጥረ ነገር ይዘት መቀነስ የሚያመጣ በመሆኑ ቀጥሎ የተመላከቱትን የድህረ ምርት አያያዝ ሒደቶች በአግባቡ መተግበር ያስፈልጋል፡፡ 9.1. የሰብል ምርት አሰባሰብ እና ወቅት ካሚሊና እንደየ ሥነ ምህዳሩ ሁኔታ ከ100 እስከ 120 ቀናት ውስጥ ይደርሳል፡፡ ሰብሉ ለመሰብሰብ መድረሱ የሚታወቀው ሙሉ ለሙሉ ቅጠሉን ቢጫና ሲደርቅ እንዲሁም ሲያረግፍ፣ እንቡጦቹ ደግሞ ወደ ግራጫማ መልክ ሲቀየሩ ነው፡፡ 9.2. አጨዳ ሰብሉ ከደረሰ በኋላ ከሰሊጥ በተለየ እስከ ሁለት ሳም ንት በማሳ ላይ ምርቱን ሳያራግፍ (non-shatering) የመቆየት አቅም ያለው ቢሆንም፤ ሰብሉን ለመሰብሰብ የዝርያውን የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

85 መድረሻ ጊዜ በትክክል ማወቅ እና ለአጨዳ መዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ ሰብሉ በማሳ ላይ 75% ያህሉ ወደ ቢጫነት ሲለወጥ ለአጨዳ መድረሱን የሚያመላክት በመሆኑ መሰብሰብ ይገባል /ምስል 13/፡ ሰብሉ የመሰብሰብ ሥራው በማጭድ የሚከናወን ይሆናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዘመናዊ የማጨጃ መሣሪያዎችን በመጠቀም ሰብሉን መሰብሰብ ይቻላል፡፡ ምስል 13፡ የካሜሊና ሰብል ለአጨዳ መድረሱንና ሲታጨድ የሚያሳይ ፎቶ 9.3. ማድረቅና መውቃት ካሚሊና ንጽህናው በተጠበቀ ሥፍራ የዘር እርጥበቱ 10% እስኪደርስ ድረስ ማድረቅ ይገባል፡፡ ይህም የሚሆነው የታጨደው ሰብልን በማሰር በሸራ ላይ ተደጋግፎ እንዲቆም እና እንዲደርቅ በማድረግ ለአደራረቁ እንዲያመች የዘር ጭንቅላቱን ወደ ላይ በማድረግ ማከማቸት እና ባለበት ሥፍራ በማቆየት በአውድማ ምትክ ለመውቃት የሚያስችል ሸራ በማንጠፍ ወይም የሲሚንቶ አውድማ በመጠቀም ውቂያ ማከናወን ይቻላል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

86 በአማራጭነትም በማሳ ላይ ድርቀቱን እስኪጨርስ ድረስ በማቆየት ማጨድ ይቻላል፡፡ ምርቱን ከግርዱ የመለየት ሥራ በማናፈስ እና በማበጠር መሥራት የምርቱን የእርጥበት መጠን በቀጣይ ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡ በማዝራት ወቅት የዘሩ ክብደት አነስተኛ በመሆኑ በነፋስ ኃይል በቀላሉ እንዳይወሰድ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ 9.4. ምርት ማጓጓዝ ምርት በሚጓጓዝበት ወቅት ጥንቃቄን የሚሻ በመሆኑ ለመጓጓዣ የምንጠቀምባቸው ጋሪዎች እና የማጓጓዣ መሣሪያዎች ከተባይ እና ምርቱን ለብክነት ከሚዳርጉ ነገሮች የተጠበቀ መሆኑን በቅድሚያ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ የመያዣ (ፒክስ ባግ) ከረጢቶች እና ዘርዛራ ያልሆኑ ጆንያዎች ከኬሚካል የጸዱ እና ያረጁ አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ይገባል፡፡ ምርቱን ለማጓጓዝ መጫን እና ማውረድ የሚጠይቅ በመሆኑ በዚህን ሒደት የመፍሰስ አደጋ በማያስከትል መልኩ በጥንቃቄ መሥራት ይገባል፡፡ 9.5. ምርት ማከማቸት ካሚሊና ከተወቃ በኃላ የዘር እርጥበቱ ከ10% ሆኖ ንፁህ፣ ደረቅና ነፋሻማ በሆነ ደረጃውን በጠበቀ ማከማቻ ውስጥ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሰብሉ በቀላሉ እርጥበቱን በመሳብ የመበላሸት ባሕርይ አለው፡፡ ክምችቱ በጆኒያ፣ በጎተራና በተለያዩ የማከማቻ ቴክኖሎጂዎች /ምስል 14:15፤16/ ሊደረግ ይችላል፡፡ ተገቢውን የካሚሊና ምርት እርጥበት መጠን ለማወቅም መለኪያ መሣሪያ የሚያስፈልግ ቢሆንም የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

87 በየአካባቢው በአርሶ አደሩ ዘንድ መሣሪያው ስለማይኖር በአርሶ አደሮች ባህላዊ ልምድ በመታገዝ ፍሬውን በጥርስ በመስበር በሚሰጠው ቀጭ የሚል ድምጽ እርጥበቱን መገመት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የእህል እርጥበትን ይዘት መጠንን በመስክ ደረጃ በቀላሉ ለመገመት የጨው እና የጠርሙስ ዘዴን መጠቀም አንዱ አማራጭ ነው ፡፡ በዚህ ዘዴ ለመጠቀም በሚገባ የደረቀ ባዶ ጠርሙስ እና መጠኑ ከ5-10 ማንኪያ የደረቀ ብትን ጨው ማዘጋጀት እና የጠርሙሱን 3 እጅ በእህል በመሙላት እና የተዘጋጀውን ጨው ጨምሮ እና በቡሽ ከድኖ የተወሰነ ደቂቃ ማወዛወዝ ከዚያም የተጨመረው ጨው በጠርሙሱ ግድግዳ እና በእህሉ ላይ ተጣብቆ/ ተለጥፎ የሚታይ ከሆነ የምርቱ/ ዘር የእርጥበት መጠን ከ15 በመቶ በላይ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ስለዚህ ይህ እርጥበት መጠኑ ከፍተኛ ስለሚሆን እህሉን የበለጠ በማድረቅ ለማከማቸት ወደ 10% ማውረድ ያስፈልጋል ፡፡ በመጋዘን የተከማቸ ዘርን በየጊዜው መፈተሽ፣ ም ርት ማክረም የግድ ከሆነ የተሻለ ደረጃ ላይ ያለውን መርጦ ማቆየት ይመረጣል፡፡ እንዲሁም ያለ ከረጢት በሸራ የተከማቸ ምርትን በየጊዜ በማገላበጥ ማናፈስ ይኖርብናል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

88 ምስል 14 ፒክስባግ ምስል 15 የብረት ጎተራ ምስል 16 ኮከንስ 9.6. የሰብል ምርት ብክነት መንሥኤዎችና መፍትሄያቸው ሰብሉ በማሳ ላይ ለብዙ ጊዜ ከቆየ እና በውቂያና ክምችት ወቅት እርጥበት ከተከሠተ የምርት ብክነት ያስከትላል፡፡ በማሳ ላይ ለረዥም ጊዜ መቆየት፡- ሰብሉ ሳይታጨድ በማሳ ላይ ረዥም ጊዜ ከቆየ በአጨዳ ወቅት በመሰባበር በመርገፍ በእንስሳት በመበላት እና በመሳሰሉት ምክንያቶች ለብክነት ይዳረጋል፡፡ ሰለዚህ ወቅቱን ጠብቆ ምርቱን መሰብሰብ አላስፈላጊ ብክነቶችን ያስወገግዳል፡፡ አላስፈላጊ እርጠበት መከሠት፡- ሰብሉ ከደረሰ ወይም ከተመረትም በኋላ እርጥበት የሚያገኘው ከሆነ ለምርት ብክነትና መበላሸት ስለሚጋለጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ምርት በማጓጓዝ ወቅት የሚከሠት ብክነት፡- ይህ ብክነት ትክክለኛ የማጓጓዣ እቃ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

89 ባለመጠቀም፤ የማጓጓዣው ዓይነት ምቹ ያለመሆን፤ በመሳሰሉት ሊከሠት የሚችል ሲሆን አስፈላጊው ማድረግ ይገባል፡፡ የድህረ ምርት ተባይ፡- በድህረ ምርት አያያዝ ሥርዓት ውስጥ የሚገጥመው ተባይ የባለአከርካሪ ተባይ (RODENTS) ሲሆን እነዚህ የአይጥ ዝርያዎች በምርት ላይ የሚያደርሱት ጥፋት ከፍተኛ (15%) በመሆኑ ለመከላከል በሚያስችል የመከላከያ ዘዴዎች ማስወገድ ይገባል፡፡ ባህላዊ የአይጥ መከላከያ ዘዴዎቹ፡- አይጦች ወደ ማከማቻ ውስጥ እንዳይገቡ በተቻለ መጠን የማከማቻ አካባቢውን ማጽዳት፣ ማከማቻዎች አይጦችን እንዳያስገቡ አድርጎ መሥራት፣ የአይጥ መከላከያ ቆርቆሮ / 25 ሳ.ሜ ዲያሜትር/ በ 4 ቱም የማከማቻ መቆሚያ እግሮች ላይ ማድረግ፤ የአይጥ ወጥመድን መጠቀም፣ የጅብ ሽንኩርትን ጨቅጭቆ ከሌላ ተለዋሽ ምግብ ጋር በማደባለቅ በመመላለሻ መንገዶችና ቀዳዳዎች ውስጥ መጨመር፣ ማከማቻዎች በሚገባ መጠገን፤ በግድግዳ፣ አካባቢ ያሉ ስንጣቆዎች በወለል እና በጣራ ያሉ ቀዳዳዎች በሚገባ መደፈን አለባቸው፡፡ አይጥን በኬሚካል መከላከል፡- አስገዳጅ ከሆነ የምንጠቀማቸው የኬሚካል ቁጥጥር /የጸረ ተባይ ዓይነት እና መጠን /ላኒራት /ብሮሚዳይሎን / የተባለውን ጸረ አይጥ በስንዴ በመቀላቀል ወይም የተቀላቀለውን መጠቀም፣ ክሊራት የተባለውን ጸረ አይጥ ፔሌት መጠቀም፣ በአይጦች ጉድጓድ እና በየሁለት ሜትሩ መመላለሻ መንገዳቸው ላይ በእያንዳንዱ 100 ግራም የተዘጋጀውን ኬሚካል ሌሎች እንስሳት ሊያገኙት በማይችሉበት ሁኔታ ማስቀመጥ፣ ዚንክ ፎስፋይድ ከስንዴ ገለባ ጋር ማቀላቀል እና ከላይ በተገለጸው ሁኔታ በእያንዳንዱ 25 ግራም ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

90 የሰብሉ የምግብ ንጥረ ነገር ይዘት፣አጠቃቀምና ለምግብና ለስርዓተ-ምግብ ዋስትና መረጋገጥ ያለው አስተዋጽኦ 10. የምግብ ንጥረ ነገር ይዘትና አጠቃቀም ካሚሊና የተለያዩ ጠቃሚ የስብ አሲድ (fatty acid) በመቶኛ የያዘ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ኦሊይክ ከ12.8-14.7% ሊንኦይሊክ ከ16.3%-17.2% ሊንኦይሊኒክ ከ36.2- 39.4% እና ኤይኮሰኖይክ ከ14-15.5% መያዙን በሃገራችን ተረጋግጣል፡፡ 10.1. የሰብሉ ንጥረ ምግብ ይዘትና ለእለታዊ የምግብ ንጥረ ነገር ፍላጎት ያለው አስተዋፅኦ ካሜሊና በንጥረ ምግብ ይዘቱ የበለጸገ በተለይም በኦሜጋ 3 እና 6 የበለጸገ መሆኑ እና የቅባት እህሎች የሚሰጡትን ንጥረ ነገር ይዘት በተሟላና በበለጸገ ሁኔታ የያዘ መሆኑ ተመራጭ ያደርጋዋል፡፡ በኢትዮጵያ የቅባት እህል አጠቃቀም የተለመደ ሲሆን በባህላዊም ሆነ በዘመናዊ የአመጋገብ ዘይቤ በም ግብ ስርዓቱ ታሳቢ በማድረግ ግለሰቦች እና ማህበረሰቡ ቢጠቀም ለጤና እና ለአእምሮ ግንባታ ጉልህ ሚና አለው፡፡የካሚሊና የምግብ ንጥረ ይዘት በአለም አቀፍ ጥናት በእጅጉ የተሰራ ሲሆን ንጽጽራዊ የንጥረ ነገር ይዘቱን የሚያሳይ በሰንጠረዥ 3 እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ይሁን እንጅ በጥልቀት የሰብሉን የንጥረ ነገር ይዘትና መጠን ሙሉውን የሚያሳይ መረጃ በላቦራቶሪ ምርመራ ወደፊት ሊረጋገጥ ይገባል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

91 ምንጭ፡ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (2013) የዝርያ አይነት እርጠበት ቅባት (%) አሰር (ክሩድ ፕሮቲን (%) ኢ-ንጥረ ምግብ ይዘት (%) ፋይቴት (ሚሊ ታኒን (ሚሊግ/ ከሚሊና ዝርያ 1 5.185 ፋይበር) (%) 45.435 11.5385 ግ/100 ግ) 100 ግ) 23.943825 471.4757 99.2495 ካሚሊና ዝርያ 2 5.645 45.27 13.619 21.93045 525.2101 159.9171 ፋጉሎ 5.18 14.1335 473.9011 332.249 ሠንጠረዥ 3፡ የተለያዩ የካሚሊና ዝርያዎች የም ግብ ንጥረ ነገር ይዘት 10.2. ምርቱ ከሥርዓተ ምግብና ጤንነት አንጻር ያለው ጠቀሜታ ካሚሊና በተለያዩ ሀገራት ለምግብነት የሚጠቀሙበት ሲሆን በሀገራችንም በተወሰኑ ክልሎች ጥቅም በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በአብዛኛው በዘይት መልክ የሚያገለግል ሲሆን በሰሜኑ የሀገራችን አካባቢ ተልባን በሚጠቀሙበት አግባብ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ ካሚሊና በውስጡ ለሰው ልጅ ጤንነት ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ የም ግብ ንጥረ ነገር ይዘት ያለው ሲሆን ከእነዚህም ከፍተኛ የኦሜጋ-3፤ ኦሜጋ-6 (Omega3 & 6) እና ፕሮቲን ንጥረ ምግቦች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ሰውነታችን በተፈጥሮ ማዘጋጀት የማይችላቸው ሆኖም ከምግብ ልናገኛቸው የሚገቡ የምግብ ንጥረ ነገሮች አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ኦሜጋ 3 እና 6 ፋቲ አሲድ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ለጤንነት ያላቸውም ጠቀሜታ፡- በውስጣቸው ያለው ንጥረ ነገር የልብ እና የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል