Important Announcement
PubHTML5 Scheduled Server Maintenance on (GMT) Sunday, June 26th, 2:00 am - 8:00 am.
PubHTML5 site will be inoperative during the times indicated!

Home Explore በኢትዮጵያ_ፌደራላዊ_ዲሞክራሲያዊ_ሪፑብሊክ_የግብርና_ሚኒስቴር_የኬነዋ፣_የካሚሊና_እና_የምግብ_ሲናር_ኦትስ

በኢትዮጵያ_ፌደራላዊ_ዲሞክራሲያዊ_ሪፑብሊክ_የግብርና_ሚኒስቴር_የኬነዋ፣_የካሚሊና_እና_የምግብ_ሲናር_ኦትስ

Published by Gedion Nigussie, 2022-04-06 04:01:22

Description: በኢትዮጵያ_ፌደራላዊ_ዲሞክራሲያዊ_ሪፑብሊክ_የግብርና_ሚኒስቴር_የኬነዋ፣_የካሚሊና_እና_የምግብ_ሲናር_ኦትስ

Search

Read the Text Version

ከማምረት በላይ ህዳር /2014



በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

የይዘት ማውጫ ክፍል አንድ የኬነዋ (Quinoa) ሰብል የአመራረት እና የአጠቃቀም ማንዋል...............................................................................1 1. መግቢያ.............................................................................................................................................................................1 2. የሰብሉ ገጽታና የመላመድ አቅም........................................................................................................................................4 3. የኬነዋ ዋና ዋና ጠቀሜታዎች.............................................................................................................................................6 3.1. ለምግብነት...............................................................................................................................................................6 3.2. የአፈር ጨዋማነት መቋቋም......................................................................................................................................6 4. ተስማሚ ሥነ-ምህዳር........................................................................................................................................................7 4.1. ከባሕር ጠለል በላይ ከፍታ.......................................................................................................................................7 4.2. አስፈላጊ አካባቢያዊ ሁኔታዎች..................................................................................................................................7 4.3. የዝናብ መጠን.........................................................................................................................................................7 4.4. የማዳበሪያ መጠንና አደራረግ...................................................................................................................................8 5.ምርት ላይ ያሉ ዝርያዎች....................................................................................................................................................9 6. የአመራረት ዘዴ.................................................................................................................................................................9 6.1. የማሳ መረጣና የመስክ ዝግጅት.................................................................................................................................9 6.2. የዘር ወቅት.............................................................................................................................................................12 6.3. ዘር፣ የዘር መጠንና የአዘራር ዘዴ..............................................................................................................................12 6.4. ማሳሳት.................................................................................................................................................................17 6.5. የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀም ዘዴ.........................................................................................................................19 7. ሰብል ጥበቃ......................................................................................................................................................................20 7.1. አረም ቁጥጥር..........................................................................................................................................................20 7.2. ነፍሳት ቁጥጥር.......................................................................................................................................................21 7.2.1. እስከ አሁን ከተመዘገቡት ከ 56 በላይ የኬነዋ ተባዮች......................................................................................21 7.2.2. ክሽክሽ (ኤፊድ)............................................................................................................................................26 7.2.3. የጎተራ ተባይ............................................................................................................................................... 29 7.3. በሽታ....................................................................................................................................................................30 7.3.1. ዳውኒ ሚልዲው.......................................................................................................................................................................................30 8. የምርት አሰብሰብና ድህረ ምርት አያያዝ.......................................................................................................................................................................34 8.1. ምርት የመድረሱ ምልቶች..............................................................................................................................................................35

8.2. ምርት አሰባሰብና አወቃቅ....................................................................................................................................36 9. ኬነዋን በመስኖ የማምረት ዘዴ.........................................................................................................................................39 10. ዘር በማምረት ወቅት የሚደረጉ ጥንቃቄዎች......................................................................................................................41 የሰብሉ የምግብ ንጥረ ነገር ይዘት፣አጠቃቀምና ለምግብና ለስርዓተ-ምግብ ዋስትና መረጋገጥ ያለው አስተዋጽኦ ....................... 42 11. የምግብ ንጥረ ነገር ይዘትና አጠቃቀም...............................................................................................................................42 11.1. ፕሮቲን ................................................................................................................................................................42 11.2 የምግብ ቅባት........................................................................................................................................................43 11.3 ካርቦ ሃይድሬት/ ሃይል ሰጪ...................................................................................................................................43 11.4 አሰር.....................................................................................................................................................................44 11.5 ማእድናትና ቫይታሚኖች.........................................................................................................................................44 12. የምግብ ዝግጅትና አጠቃቀም...........................................................................................................................................47 12.1 ሳፖኒን የማስወገድ ስራ...........................................................................................................................................47 12.2. የምግብ ዝግጅት....................................................................................................................................................50 ክፍል ሁለት የካሚሊና (Camelina Sativa) (እማዋይሽ) ሰብል የአመራረት እና የአጠቃቀም ማንዋል......................................... I 1. መግቢያ............................................................................................................................................................................61 2. የሰብሉ ገጽታና የመላመድ አቅም.....................................................................................................................................64 3.የካሚሊና ዋና ዋና ጠቀሜታ..............................................................................................................................................67 3.1 ለምግብነት.............................................................................................................................................................67 3.2 ለዘይትነት.............................................................................................................................................................68 3.3 ለአማራጭ የኃይል ምንጭነት (ባዮ ፊውል ቴክኖሎጅ...............................................................................................69 3.4 ለእንስሳት መኖነት.................................................................................................................................................70 3.5. ለንቦች ቀሰምነት....................................................................................................................................................70 3.6. የመሬት ለምነት ለማሻሻልና ለመበቅ.......................................................................................................................71 3.7. በረዶ የመቋቋም አቅም..........................................................................................................................................72 3.8. ኢንዱስትሪያዊ ጠቀሜታ......................................................................................................................................72 3.9. ማህበረሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ.....................................................................................................................72

4.4. ተስማሚ ሥነ ምህዳር ...........................................................................................................................................73 4.1. ከባሕር ጠለል በላይ ከፍታ............................................................................................................................73 4.2. የአየር ሙቀት................................................................................................................................................73 4.3. የዝናብ መጠን..............................................................................................................................................74 4.4. አፈር ዓይነት...............................................................................................................................................74 5. በምርት ላይ ያሉ ዝርያዎች..........................................................................................................................................75 5.1. ዘይቴ 1.........................................................................................................................................................75 5.1. ዘይቴ 2.......................................................................................................................................................76 6. የአመራረት ዘዴ.........................................................................................................................................................77 6.1. የማሳ መረጣ እና ዝግጅት..............................................................................................................................77 6.2. የዘር ወቅት..................................................................................................................................................78 6.3. የዘር መጠንና አዘራር ዘዴ............................................................................................................................78 6.4. የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀም ዘዴ..............................................................................................................79 7. የሰብል አመራረት ሥርዓት .........................................................................................................................................81 8. ሰብል ጥበቃ .............................................................................................................................................................82 8.1.አረም ቁጥጥር................................................................................................................................................82 8.2. እጽዋት በሽታና ቁጥጥር ዘዴ........................................................................................................................82 9. የሰብል አሰባሰብና ድህረ ምርት አያያዝ ዘዴ................................................................................................................82 9.1. የሰብል ምርት አሰባሰብ እና ወቅት.................................................................................................................84 9.2. አጨዳ.........................................................................................................................................................84 9.3. ማድረቅና መውቃት.......................................................................................................................................85 9.4. ምርት ማጓጓዝ.............................................................................................................................................86 9.5. ምርት ማከማቸት...........................................................................................................................................86 9.6. የሰብል ምርት ብክነት መንሥኤዎችና መፍትሄያቸው......................................................................................88 የሰብሉ የምግብ ንጥረ ነገር ይዘት፣አጠቃቀምና ለምግብና ለስርዓተ-ምግብ ዋስትና መረጋገጥ ያለው አስተዋጽኦ 10. የምግብ ንጥረ ነገር ይዘትና አጠቀም..........................................................................................................................90 10.1. የሰብሉ ንጥረ ምግብ ይዘትና ለእለታዊ የምግብ ንጥረ ነገር ፍላጎት ያለው አስተዋፅኦ........................................90 10.2. ምርቱ ከሥርዓተ ምግብና ጤንነት አንጻር ያለው ጠቀሜታ.............................................................................91 10.3. የምግብ አዘጋጃጀት እና የተሰባጠረ አመጋገብ ሁኔታ (ሪሲፒ)........................................................................92

10.3.2. ካሚሊና የተቀላቀለበት እንጀራ እና ሽሮ አዘገጃጀት................................................................94 10.3. የካሚሊና ዱቄት ለማሰሻነት...................................................................................................94 10.4. የምግብ ማቆያና የኢ-ንጥረ ምግብ መቀነሻ ዘዴዎች........................................................................94 10.5. በዝግጅት ሂደት ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች...............................................................................95 ክፍል ሶስት የምግብ ሲናር የአመራረትና የአጠቃቀም ማኑዋል............................................................................................III . 1. መግቢያ..............................................................................................................................................................................................................97 2. የማኑዋሉ ዓላማና ግብ.........................................................................................................................................................................................100 2.1. ዓላማ...................................................................................................................................................................................................................100 2.2. የማኑዋሉ ግቦች.........................................................................................................................................................................................100 2.3. የማኑዋሉ አስፈላጊነት................................................................................................................................................................................101 3 . ሰብሉን የሚመረትበት ስነ-ምህዳሮች.................................................................................................................................................................102 3.1. ከባህር ጠለል በላይ ከፍታ ..............................................................................................................................................................................102 3.2. የአየር ሙቀት.............................................................................................................................................................................................102 3.3. የዝናብ መጠን.............................................................................................................................................................................................102 3.4. የአፈር ዓይነት.............................................................................................................................................................................................103 4 . የተሸሻሉ አመራረት ዘዴዎች..............................................................................................................................................................................104 4.1. ማሳ መረጣ..................................................................................................................................................................................................104 4.2. የማሣ ዝግጅት............................................................................................................................................................................................104 4.3. ዘር መረጣ..................................................................................................................................................................................................106 4.4. ዘርን ማከም................................................................................................................................................................................................108 4.5. የዘር ወቅት.................................................................................................................................................................................................108 4.6. የዘር መጠን እና አዘራር ዘዴ....................................................................................................................................................................109 4.7 የአዘራር ዘዴ.................................................................................................................................................................................................110 4.8. የማዳበሪያ ዓይነትና መጠን........................................................................................................................................................................112 5. የሰብል አመራረት ስርዓት.....................................................................................................................................................................................114 5.1. ሰብል ፈረቃ (crop rotation)..................................................................................................................................................................114 6. የሰብል ጥበቃ ዘዴዎች ........................................................................................................................................................................................115 6.1. የአረም ቁጥጥር ...........................................................................................................................................................................................115 6.2. የተባይ ቁጥጥር............................................................................................................................................................................................117

6.3. የበሽታ ቁጥጥር...........................................................................................................................................................................................119 7. የድህረ-ምርት አያያዝ ዘዴ ........................................................................................................................................121 7.1. ምርት መሰብሰብ..........................................................................................................................................121 7.2. ሰብል መውቃት..........................................................................................................................................122 7.3. ምርት ማከማቸት.........................................................................................................................................123 8. የሰብሉ የምግብ ንጥረ ነገር ይዘት፣አጠቃቀምና ለምግብና ለስርዓተምግብ ዋስትና ያለው አስተዋጽኦ..............................126 8.1. የሰብሉ ንጥረ ምግብ ይዘትና ለእለታዊ የምግብ ንጥረ ነገር ፍላጎት ያለው አስተዋፅኦ ........................................126 8.2. ምርቱ ከሥርዓተ-ምግብና ጤንነት አንጻር ያለው ጠቀሜታ...............................................................................130 8.3. የምግብ አዘጋጀጀት እና የተሰባጠረ አመጋገብ ሁኔታ (ሪሲፒ)...........................................................................133 8.4. የምግብ ማቆያና የኢ-ንጥረ ምግብ መቀነሻ ዘዴዎች..........................................................................................133 8.5. በምግብ ዝግጅት ሂደቶች ወቅት ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች..........................................................................134 9. ሰብሉን ለማስተዋቅና ለማላመድ የሚከናነወኑ የኤክስቴንሽን ኮሚኒኬሽን ተግባራት.......................................................136 10. ዋቢ መጽሀፍት.......................................................................................................................................................139 11. አባሪ.......................................................................................................................................................................145 12. የምርት አዋጭነት ስለማስላት...................................................................................................................................145

I የክቡር ሚኒስትር ዴኤታ መልዕከት የግብርና ሴክተሩ የእርሻ፤ የተፈጥሮ፤ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፎችን በማሳደግ፣ የኤክስፖርት ሰብሎችን አማራጭ ለማስፋት፣ ከውጭ የሚገቡትን ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርቶች ለመተካት፣ ለአግሮ ኢንደስትሪ በጥራትና በበቂ መጠን የጥሬ ዕቃ ለማቅረብና የምግብና ስርዓተ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ ላይ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ ባለፉት ዓመታት እንደ ሀገር ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አንፃር ሰፋፊ ውጤቶች የተመዘገቡ ቢሆንም ከአገሪቱ የህዝብ እድገት ጋር ሲነጻጸር ያነሰ በመሆኑ የህዝቡን ምግብና ስርዓተ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ አንጻር ውስንነት አለበት፡፡ ይህን ስር የሰደደ ችግር ለመቅረፍ የምግብ ሥርዓትን ማዕከል ያደረገ የግብርና መር አሰራር (Agri- Food System) አዋጭና ዘላቂ የሆነ አካሄድ መሆኑ ይታወቀል፡፡ ግብርና ሚኒስቴርም በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት ስርዓተ ምግብ ተኮር የአመራረትና የአመጋገብ ስርዓትን በመዘርጋት የተለያዩ በምግብ ንጥረ ነገር የበለጸጉ የሰብል ዝርያዎችን በግብርና ምርምር ማዕከላት እንዲፈልቁና በአርሶ/አርብቶ አደሮች ዘንድ እንዲተዋወቁ በማድረግ ወደ ምርት ስርዓት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ እነዚህ በምግብ ንጥረ ነገር ይዘታቸው የበለጸጉ የኬናዋ፣ የካሚሊ እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) ሰብሎች ለሀገራችን አርሶ አደሮችና ባለሙያዎች አዲስ እንደመሆናቸው የአመራረት እና አጠቃቀም ማኑዋሎች ተዘጋቶላቸዋል፡፡ የተዘጋጁት ማኑዋሎች የተሻሻለ የአመራረት ስርዓት እንዲዘረጋ ሚናቸው የጎላ ነው፡፡ ስለሆነም ማኑዋሎቹ በፌደራል፣ በክልል እና በወረዳ ደረጃ በሰብል ልማት፣ በሰብል ጥበቃ፣ በግብርና ኤክስቴንሽን፣ በእሴት ጭመራ እና በስርዓተ ምግብ ዋስትና ሥራ ላይ ለተሰማሩ ባለድርሻ አካላት እንደ መመሪያ እንዲጠቀሙበት እንዲሁም ለፖሊሲ አውጭዎች፣ ለተመራማሪዎች፣ ለሌሎች ሙያተኞች እና ለስቪክ ማህበረሰቡ እንደ ማጣቀሻ እንዲገለገሉበት እመክራለሁ፡፡ በመጨረሻም ይህንን ሰነድ በማዘጋጀት በኩል አስተዋጽ ላደረጉ የግብርና ሚኒስቴር፤ ምርምር ማዕከላት፤ ዳን ቸርች ኤድ እና የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ ዶ/ር መለስ መኮንን የእርሻ ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

1 መግ ቢያ ኬነዋ በሚያስደንቅ ሁኔታ በተለያዩ የእርሻ ስነ ምህዳሮች ውስጥ ሊመረት ይችላል፡፡ ኬነዋ በደርቅና ሞቃት ቦታዎች ፣ የአየር እርጥበቱ ከ 40 እስከ 88 % በሚደርስበት ቦታዎች እና የአየሩ ሙቀት ከዜሮ በታች 8 ዲ.ሴ እስከ ከዜሮ በላይ 38 ዲ.ሴ በሚደርስባቸው ቦታዎች ሁሉ መመረት ይችላል:: በተጨማሪም ከፍተኛ የውሃ እጥረትን የመቋቋም ችሎታ ስላለው በዓመት ውስጥ ከ 100 እስከ 200 ሚ.ሜ ዝናብ ብቻ በሚያገኙ ቦታዎች ሁሉ መመረት ይችላል፡፡ ኬነዋ ሁሉንም ለሰውንት አስፈላጊ የሆኑ አሚኖ አሲድ የተሰኙ ንጥረ ነገሮችን ፣ ሌሎች አስፈላጊ ሚኒራሎችና ቫይታሚኖችን አሟልቶ ከመያዙም በላይ ግሉቲን የተባለውንና በብዙ ሰዎች ላይ የሆድ ህመም የሚያስከትለውን የፕሮቲን ስለማይዝ ለምግብነት ተመራጭ ነው፡፡ የኬነዋ አሚኖ አሲድ በዘሩ የውስጠኛው ክፍል ውስጥ ስለሆነ የሚገኘው፣ ከማብሰል በፊት ዘሩን ለምግብነት ለማዋል በሚደረግ እንደ መፈተግ በመሳሰሉ ዝግጅቶች ወቅት አይቀንስም፡፡ በሌሎች ሰብሎች ላይ ግን መፈተግን የመሳሰሉ ዝግጅቶች የምግብነት ይዘትን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳሉ፡፡ በተጨማሪም ኬነዋ በጨው ምክንያት ሌሎች ሰብሎችን ማብቀል በማይችል አፈር ላይ መብቀልና ምርት መስጠት ይችላል፡፡ በአንዲስ አካባቢ የሚገኙት ፔሩ፣ ቦሊቪያና ኢኳዶር የኬነዋ ዋና አምራች አገሮች ናቸው (ምስል 1)::ፔሩና ቦሊቪያ ብቻቸውን የአለምን ምርት 90 ከመቶ የሚሸፍኑ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ሰብሉ በአውሮፓ፣ በኤስያና በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ አገሮች ውስጥ እየተስፋፋ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ኬነዋ አስቸጋሪ ሁኔታን መቋቋም በመቻሉ፤ የሰው ልጅን የምግብና የንጥረ ነገር ፍላጎት ለማሟላት ባለው ስትራተጂክ ጠቀሜታ ምክንያት በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ያለው ተፈላጊነት እየጨመረ መጥቷል፡፡ ኬነዋ ለመጥፎ የአየር ጸባይ ሁኔታ የተጋለጡ ከሰሃራ በታች ያሉ ድሃ የአፍሪካ ሃገሮች ያጋጠማቸውን የምግብ እጥረት ለመፍታት አይነተኛ መፍትሄ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ 2መጠን የሚለው የእያንዳንዸን አሸዋ ትንሽነት ወይም ትልቅነት ለማመላከት እንጂ ብዛቱን አይደለም የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

2 በምስል አንድ ላይ እንደተመለከተው እ.ኤ.አ በ 2004 እና 2014 ዓ.ም መካከል የአለም የኬነዋ ምርት በ 2.5 እጥፍ የጨመረ ሲሆን፤ በተለይ ከ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ምን አልባትም የአለም የም ግብ ድርጅት ሰብሉን በአለም ላይ ለማስተዋወቅ ያደረገው ዘመቻ ተከትሎ እድገቱ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ይህ ከፍተኛ የኬነዋ ፍላጎት ከፍተኛ የኬነዋ ዋጋ መጨመርን አስከትሏል:፡ ይህም ለአርሶ አደሮች ከፍተኛ የገቢ መጨመርን ከመፍጠሩም በላይ የአካባቢን የጉልበት ዋጋ ከፍ በማድረግ አካባቢያዊ ግብይትን ያነቃቃል፡፡ በአለማችን ላይ ከባህር ወለል ጀምሮ እስከ 4000 ሜትር በሆኑ አካባቢዎች ሊበቅሉ የሚችሉ የኬነዋ ዝርያዎች ወይም አይነቴዎች አሉ፡፡ ይህም ማለት እንደ ኢትዮጵያ በተለያየ ስነ-ም ህዳሮች ለተከፋፈሉ ሃገራት ለእያንዳንዱ ስነ- ምህዳር የሚስማሙ የኬነዋ ዝርያዎቸ አሉ፡፡ በመሆኑም ትክክለኛው ዝርያ ወይም አይነቴ እስከተለየ ድረስ ኬነዋን የተለያየ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ አወቃቀር ባላቸው በማንኛውም የሃገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ማምረት ይቻላል ማለት ነው፡፡ የማንዋሉ ዓላማና ግብ ዓላማ የምርትና ምርታማነት ማነቆዎችን በመፍታት የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፤ የኬነዋ ሰብል ለማምረትና ለመጠቀም አርሶ አደሮች አዳዲስ ቴክሎጂዎችን እና አሰራሮችን በመጠቀም እንዲያመርቱ ምክረ ሀሳቦችን ተደራሽ ለማድረግ፤ በየደረጃው ያሉ የግብርና ልማት ባለሙያዎችን የኬነዋ አመራረትና አጠቃቀም ዘዴዎችና ቴክኖሎጂዎች ጋር በማስተዋወቅ ለአርሶ አደሩ ያልተቋረጠ ክትትልና የሙያ ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ አቅም ለመገንባት፤ ስለኬነዋ ሰብል በምርምር የተገኙ አዳዲስ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ ለአርሶ አደሩ እንዲደርሱ እና አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን በማስቻል ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ተፈላጊ የሆኑ ምርቶችን በስፋት እንዲመረቱ ድጋፍ ለማድረግ፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

3 የማንዋሉ ግቦች ለአብዛኞቹ በሃገራችን ላሉ ስነ-ምህዳሮች ተስማሚ የሆነ ድርቅን የመቋቋምና ከፍተኛ የንጥረ ነገር ይዘት ያለው ሰብል ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮች ለአርሶ አደሮች ተደራሽ ሆነዋል፤ በተሻሻሉ የአመራረት ዘዴዎችና ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ የኬነዋ ምርት ተመርቷል፤ የማንዋሉ አስፈላጊነት • ኬነዋ ለምግብና ለሥርዓተ-ምግብ ዋስተናየሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ፤ • የኬነዋ ሰብል ለሀገር ውስጥ የምግብ ፍጆታ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ፤ • የኬነዋ ሰብል በሀገራችን ያልተስፋፋ በመሆኑ የተሻሻሉ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ስለሚያደርግ:፡ • የተሻሻሉ አሰራሮችና • ቴክኖሎጂዎች ምክረ ሀሳብ በአርሶ/በከፊል አርሶ አደሩ ዘንድ እንዲሰርፅ ተከታታይ የሆነ ምክርና ክትትል ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፡ • በዘርፉ ከሚንቀሳቀሱ የምርምርና የተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመስራት በምግብ ሰብል ልማት የሚስተዋሉ የክህሎት ክፍተቶችን መሙላት ማስፈለጉ፤ • የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ዋስትና በማረጋገጥ ጤናማ አምራች ማህበረሰብ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤ ምስል 1. በአለም ላይ የኬነዋ ምርት አጨማመር ከ 2002 እስከ 2011 በሺህ ቶን የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

4 1. የሰብሉ ገጽታና የመላመድ አቅም በምርት ተግባር ላይ የዋሉት የኬነዋ አይነቶች ከፍተኛ ዘረመላዊ ልዩነት ያሳያሉ፡፡ ይህም ልዩነት በቀለም (በተክል፣ በአበባና በዘር) ፣ በአበባ ጭንቅላት ቅርጽ፣ በፕሮቲን ይዘት፣ በሳፖኒን ይዘት እና በቅጠሎች ቢታ ሳያኒንና ካሊሲየም ኦክሳሌት ይዘት ይገለጻል፡፡ ይህም በመሆኑ ሰብሉ በተለያዩ ስነ- ምህዳራዊ ሁኔታዎች ውስጥ (የአፈር አይነት፣ የእርጥበት መጠን፣ የሙቀት መጠን፣ ከባህር ወለል በላይ ከፍታ፣ ውርጭ እና የአፈር ጨዋማነትና አሲድነት) መብቀልና ምርት መስጠት ይችላል፡፡ ኬነዋ እንደ ዝርያው አይነት ቁመቱ ከ0.5 እስከ 2 ሜትር ሊደርስ ይችላል፡፡ ተክሉ ወፍራም ቀጥ ያለና ቅርንጫፍ ያለው ወይም የሌለው እንጨታማ ግንድ ሲኖረው ቅጠሎቹ ደግሞ ሰፋፊና የዳክዬ እግር ቅርጽ ያላቸው ናቸው፡፡ በወጣት ተክሎች ላይ የሚበቅሉ ቅጠሎች አብዛኛውን ጊዜ አረንጓዴ ሲሆኑ የተክሉ እድሜ እየጨመረ በመጣ ቁጥር ቀለማቸው ወደ ቢጫ፣ቀይ ወይም ሃምራዊነት ይቀየራል፡፡ ስሩ አንድ ዋና ግንድ ይኖረውና ከዚያ ላይ የሚነሱ መጋቢ ስሮች በመፍጠር ብዛት ያላቸው ቅርንጫፎች ይኖሩታል ፡፡ የዚህ አይነቱ ስር ተክሉ ለሚያሳየው ድርቅን የመቋቋም ባሕሪ አንደኛው ምክንያት ነው፡፡ እንደ ዝርያዎች አይነት የኬነዋ ምርት መድረሻ ጊዜ ባብዛኛው ከ 110 እስከ 240 ቀናት ሊደርስ ይችላል፡፡ የተለያዩ አካላት ኬነዋ የሚያሳያቸውን የእድገት ደረጃዎች በተለያየ ሁኔታ የሚገልጹት ሲሆን በሳይንሳዊ ጥናቶች መሰረት ኬነዋ ከተዘራ ጀምሮ የሚኖረው እድገት በሰባት ሂደቶች ይጠቃለላል እነዚህም፤ የብቅለት ሂደት (ከዘር እስከ ከአፈር መውጣት) ፣ የቅጠል እድገት ሂደት (ሁለት እውነተኛ ቅጠል እስከሚያወጣ ድረስ) የቅርንጫፍ እንቡጥ ማውጣት ሂደት የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

5 (ከእውነተኛ ቅጠል እስከ የቅርንጫፍ እንቡጥ ማውጣት) ፣ የአበባ እንቡጥ ማውጣት ሂደት (ከቅርንጫፍ እንቡጥ እስከ ዋና አበባ እንቡጥ ማውጣት)፣ የማበብ ሂደት (ከእንቡጥ እስከ አበባ መፍካት) የፍሬ ሂደት (ከአበባ እስከ ፍሬ መስጠት) እና የፍሬ መሙላት ሂደት (የዘር እራስ ቀለም መቀየርና የስረኛ ቅጠሎች መድረቅ) ተብለው ሊለዩ ይችላሉ (ምስል 2) ፡፡ የኬነዋ ዘር ምንም አይነት የመኝታ ጊዜ (ዶርማንሲ) የሌለው ስለሆነ አስፈላጊው ሁኔታዎች ከተሟሉ ገና በተክሉ ላይ እያለም ቢሆን እንኳ ሊበቅል ይችላል፡፡ ነገር ግን የጫካ ኬነዋ ዝርያዎች ሳይበቅሉ በአፈር ውስጥ ከ ሁለት እስከ ሶስት አመታት ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ አሁን በሃገራችን እየተመረተ ያለው የኬነዋ ዝርያ ቲቲካካ የሚባል ሲሆን በአማካይ ቁመቱ ከ 100 እስከ 120 ሳ.ሜ ይደርሳል፡፡ ዝርያው ለም ርት ለመድረስ በአማካኝ ሶስት ወራት የሚፈጅበት ሲሆን፤ ምርቱ በሚደርስበት ወቅት ጠቅላላ የተክሉ ቀለም ወደ ቢጫ ወይም ቡርቱካናማነት ይለወጣል፡፡ ምስል 2፡ የኬነዋ የእድገት ደረጃዎች ከዘር እስከ ምርት መድረስ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

6 2. የኬነዋ ዋና ዋና ጠቀሜታዎች ኬነዋ ዘርፈ ብዙጥቅሞች ያሉት የሰብል ዓይነት ሲሆን፣ በዋናነት የሚሰጣቸው ጥቅሞች እንደሚከተለው ተገልጸዋል፡፡ 2.1. ለምግብነት በተለምዶ ኬነዋ መጀመሪያ ተቆልቶ ይፈጭና በተለያየ መልኩ በዳቦነት በጥቅም ላይ ይውላል:: እንዲሁም ተቀቅሎ ሊበላ ይችላል፣ እንደ ሾርባ ይሰራል፣ እንደ ፓስታ ሊሰራ ይችላል፡፡ በሌሎች ሃገራት በተደረጉ ጥናቶች መሰረት 2 እጅ የኬነዋ ዱቄትን ከ 3 እጅ የስንዴ ዱቄት ጋር በመቀላቀል ተቀባይነት ያለው ዳቦ መስራት ይቻላል:: በሌላ በኩል 3 እጅ የኬነዋ ዱቄት ከ 2 እጅ ስንዴ ጋር በመቀላቀል ለስላሳ ኬኮችን መስራት የሚቻል ሲሆን 7 እጅ ኬነዋን ከ 3 እጅ ስንዴ ጋር በመቀላቀል ደረቅ ብስኩት ለመስራት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ በፋብሪካ ደረጃ የሚቀነባበሩ ምግቦችም ከኬነዋ ይሰራሉ፡፡ ቅጠሉና ግንዱ ደግሞ ለከብቶች ምግብነት ይውላል፡፡ በተለይ አንደ ዶሮና አሳማ ላሉ አንድ የጨጓራ ክፍል ላላቸው እንሰሳት ኬነዋን መቀለብ ከፍተኛ የምርት ጭማሪ ለማግኘት ያስችላል፡፡ 2.2. የአፈር ጨዋማነት መቋቋም ኬነዋ የአፈር / የዉሃ ጨዋማነትን መቋቋም ከሚችሉ የተክል አይነቶች በዋነኛነት የሚጠቀስ ነው:: አሁን በአገራችን እየተመረተ ያለው የኬነዋ ዝርያ የጨዋማነት ይዘቱ እስከ 20 ዴ.ሲ1 በሆነ አፈር ላይ ሙሉ የምርት አቅሙን መግለጥ የሚችል ሲሆን፤ የጨዋማነት መጠኑ እስከ 40 ዴ.ሲ በሆነ አፈር ላይ ደግሞ እስከ 60 ከመቶ የምርት አቅሙን መግለጥ ይችላል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የጨዋማነት ይዘቱ 16 ዴ.ሲ የደረሰ አፈር ከኬነዋ ውጪ በጣም ጨው ይቋቋማሉ የሚባሉ ተክሎችን የመጉዳት አቅም አለው፡፡ ከዚህ አንጻር ሲታይ ኬነዋ በጨው በተጠቃ አፈር ላይ በቀላሉ ሊመረት ይችላል፡፡እንዲሁም ኬነዋን ጨዋማ መሬት ላይ በመዝራትና ምርቱ ከመድረሱ በፊት በመሰብሰብ የአፈሩን ጨዋማነት ማከም ይቻላል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

7 3. ተስማሚ ሥነ-ምህዳር ኬነዋ በበረሃ፣ ሞቃታማና ደረቅ ፣ ቀዝቃዛና ደረቅ፣ ቀዝቃዛና ዝናባማ፣ ቀዝቃዛና እርጥብ በሆኑ አካባቢዎች ሊበቅሉ የሚችሉ በርካታ ዝርያዎች አሉ፡፡ በመሆኑም ኬነዋ በተለያዩ ስነ- ምህዳሮችና በተለያየ የአየር ጸባይ ውስጥ ማደግና ምርት መስጠት ይችላል፡፡ 3.1. ከባሕር ጠለል በላይ ከፍታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከባሕር ጠለል እስከ ከባሕር ጠለል 4000 ሜትር ድረስ መብቀልና ምርት መስጠት የሚችሉ የኬነዋ ዝርያዎች አሉ፡፡ አሁን በሃገራችን ያለው የኬነዋ ዝርያ ከባሕር ጠለል በላይ ከ 550 እስከ 2986 ሜትር በሆኑ አካባቢዎች ተሞክሮ ምርት እንደሚሰጥ ታይቷል፡፡ ነገር ግን እስከ አሁን ባለው መረጃ መሠረት፤ በተለይ የአፈሩ አይነት ተስማሚ እስከ ሆነ ድረስ ከላይ በተጠቀሰው የከፍታ ክልል ውስጥ እስከሆነ ድረስ የባሕር ጠለል ከፍታ እምብዛም በምርት ላይ ልዩነት አያመጣም፡፡ 3.2. የአየር ሙቀት ምንም እንኳን ኬነዋ ከዜሮ በታች 8 ዲ.ሴ እስከ 38 ዲ.ሴ (በቅርንጫፍ ደረጃና ከለስላሳ የዘር እደገት ደረጃ በኋላ) ድረስ በሚደርስ የሙቀት መጠን ውስጥ ማደግ ቢችልም እጅግ የሚስማማው 15 እስከ 20 ዲ . ሴ ያለው ነው፡፡ ከተክሉ የእድገት ደረጃ በተጨማሪ ኬነዋ ለዝቅተኛ የሙቀት መጠን የሚያሳየው የመቋቋም ባሕሪ የሚወሰነው በዝርያው አይነትና ቅዝቃዜው በሚቆይበት የጊዜ እርዝመት ነው፡፡ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ38 ዲ.ሴ በላይ የሆነ ሙቀት ተክሉ እድገቱን እንዲያቆም ከማድረጉም በላይ ወንዴውን ዘር በመግደል መካንነትን ያመጣል፡፡ በአጠቃላይ እጅግ ከፍተኛ የቀን ሙቀትና ሞቃታማ ሌሊት ኬነዋ ዘር እንዳይሰጥ ተጽዕኖ ያደረጋሉ፡፡ 3.3. የዝናብ መጠን ኬነዋ የእርጥበት ማነስን የመቋቋም አቅሙ እንደ ዝርያው አይነትና እንደ ስነ- ምህዳሩ ሁኔታ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

8 ይለያያል፡፡ ኬነዋ ከሌሎች ሰብሎች የተለየ የአፈር እርጥበት ማነስን የመቋቋም ችሎታ አለው:: አንደኛው የዚህ ችሎታ መሰረት በተፈጥሮው ዝቅተኛ የዉሃ ፍላጎት ያለው መሆኑ ሲሆን ሁለተኛው ድግሞ የዉሃ እጥረት ከተከሰተ በኋላ ውሃ በሚያገኝበት ጊዜ ሙሉ የቅጠል ዕድገትና የምግብ ዝግጅት (ፎቶ ሲንተሲስ) አቅሙን መልሶ ማግኘት መቻሉ ነው፡፡ በመሆኑም ሰብሉ ምንም የመስኖ ዉሃ በሌለባቸውና ዝቅተኛ ዝናብ በሚያገኙ በከፊል ደረቅና ደረቅ አካባቢዎች መመረት እንዲችል አድርጎታል፡፡ የኬነዋ የዉሃ ፍላጎት ከ 250 (ከቦሊቪያ አካባቢ የወጡ ዝርያዎች) እስከ 1500 ሚ.ሜ (ከአንዲስ ሸለቆ አካባቢ የወጡ ዝርያዎች) የሚደርስ ሲሆን ም ንም እንኳን ከፍተኛ የዉሃ እጥረትን መቋቋም የሚችል ቢሆንም በመጀመሪያዎቹ የእድገት ጊዜያት በቂ እርጥበት ይፈልጋል፡፡ በቂ የአፈር ውስጥ እርጥበት እስካለ ድረስ ኬነዋ ከሁለት እስከ ሶስት እውነተኛ ቅጠል እስከሚያወጣበት ጊዜ ድረስ ተጨማሪ ዉሃም አይፈልግም:: ኬነዋ ከመነሻው ዘገምተኛ እደገት የሚያሳይ ቢሆንም ከፍተኛ ድርቀትን በመቋቋም እስከ 40 ሚ.ሜ እና ከዚህም በታች በሆነ እርጥበት መኖር ይችላል፡፡ 3.4. የአፈር ዓይነት በአለም ላይ ለሌሎች ሰብሎች ማምረቻነት ሊውል በማይችል አፈር አይነት ላይ ሊመረቱ የሚችሉ የኬነዋ ዝርያዎች አሉ፡፡ ይህ አፈር ዝቅተኛ ዉሃ የማጠንፈፍና ለምነት ያለው፣ አሲድ (4.5 ፒ.ኤች.) ወይም ኮም ጣጣ (9.5 ፒ.ኤች) የሆነ ነው፡፡ ነገር ግን አሁን በሃገራችን እየተመረተ ያለው ዝርያ ግን መጠነኛ የመሬት ተዳፋትነት፣ ጥሩ ዉሃ የማጠንፈፍ አቅም፣ መካካለኛ ለም ነትና ከፍተኛ ብስባሽ ባለው አሸዋማ አፈር ላይ ከፍተኛ ም ርት ይሰጣል፡፡ ሆኖም ግን ዝርያው የትርፍ ዉሃ መንጣለል እስካለጋጠመው ድረስ በአሸዋማም ሆነ በከባድ አፈር ላይ ቢመረት ተመጣጣኝ ምርት ሊሰጥ ይችላል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

9 4. በምርት ላይ ያሉ ዝርያዎች በሃገራችን በምርት ላይ ያለው የኬነዋ ዝርያ ቲቲካካ የተባለው ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ተጨማሪ ዝርያዎችን ለማውጣት እስከ አስር የሚጠጉ ዝርያዎች በሙከራ ላይ ናቸው:: 5. የአመራረት ዘዴ በአንጻራዊነት ኬነዋ ለአለም አዲስ ሰብል ነው፡፡ በመሆኑም ያሉት የተሻሻሉ አመራረት ዘዴዎችና የምርምር ውጤቶች በጣም ውስን በመሆናቸው ሰብሉን በተለያዩ ስነ- ምህዳሮችና ሁኔታዎች ውስጥ ለማምረት የሚያስችል መረጃ ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል:፡፡ ያሉት ውስን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሚገባ በተዘጋጀ አፈር ላይ በተዘጋጁ እርቀታቸው ከ 30 እስከ 80 ሳ.ሜ በሆኑ መስመሮች ላይ እስከ 10 ኪ.ግ የሚደርስ የተጣራ ዘር መዝራትና ከበቀለ በኋላ ሁለት እውነተኛ ቅጠሎችን ሲያወጣ ማረምና ማሳሳት ተመራጭ የአመራረት ዘዴ ነው፡፡ ከ 40 እስከ 200 ኪ.ግ ዩሪያ (በአንድ ጊዜ በማድረግ ወይም በዘርና በአፈር ማስታቀፍ ወቅት ከፋፍሎ) በማድረግ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ይቻላል፡፡ ምርት በሰው ሃይል ወይም ማሽን በመጠቀም ሊሰበሰብ ይችላል። በተስማሚ የአየር ሁኔታ (ዝናብና የአየር ሙቀት) ውስጥ ከበቀለ ኬነዋ በአንድ ሄክታር እስከ 50 ኩንታል የሚደርስ የእህል ምርትና ከ 50 እስከ መቶ ኩንታል የሚደርስ ለከብት መኖ የሚሆን ተረፈ ምርት እንደሚሰጥ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ 5.1. የማሳ መረጣና የመስክ ዝግጅት ከዚህ ቀደም ኬነዋ በሃገራችን የማይታወቅ ቢሆንም በቤተሰብ ደረጃ የሚዛመዱት ሰብሎችም ሆኑየአረም አይነቶች አሉ። ስፒናች፣ ቆስጣ፣ ሬድቢት፣ ሹገር ቢት፣ ፎደር ቢት፣ አማራንተስና ላምበስ ኳርተርስ ከኬነዋ ጋር የሚዛመዱ ሰብሎች/አረም ሲሆኑ በዚህም ዝምድና ምክንያት በነዚህ ተክሎች ላይ የሚታዩ ተባዮች በኬነዋ ላይም ሊከሰቱ ይችላሉ። ዴ.ሲ ማለት ዴሲ ሲመን ማለት ሲሆን የአፈርን ወይም የዉሃን ጨዋማነት ለመለካት የሚውል መስፈርት ነው፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

10 ስለዚህ እነዚህን ተባዮች ለማስወገድ ኬነዋን ለማምረት የሚመረጠው መስክ በቀደሙት ሶስት አመታት ውስጥ ከላይ ለተዘረዘሩት ሰብሎች ማምረቻነት ያልዋለ መሆን አለበት። ምስል 3 ትርፍ ዉሃ ማንጣፈፍ የማይችል ማሳ ላይ የበቀለ ኬነዋ ምንም እንኳን ኬነዋ ከፍተኛ የውሃ አጠቃቀም ችሎታ ቢኖረውም ትርፍ ውሃን ግን መቌቌም አይችልም (ም ስል 3) ። በመሆኑም ኬነዋን ለማምረት የሚውል መሬት ትርፍ ውሃን ሊያንጣፍፍ የሚችል ወይም መጠነኛ ተዳፋትነት (እስከ 3%) ሊኖረው ይገባል ። ኬነዋ ዘሩ ትንንሽ በመሆኑ ምክንያት በዘር ወቅት አፈር ውስጥ በጣም መጥለቅ የለበት። ይህም በመሆኑ ማሳው ረባዳማ ወይም ተዳፋትነቱ ከ 3 % ያልበለጠ ካልሆነ በስተቀር ከፍተኛ ዝናብ በሚኖርበት ወቅት ዘሩ በቀላሉ በውሃ ሊታጠብ ወይም በደለል ሊሸፈን ይችላል (ምስል 4ሀ እና ለ) ። ምስል 4. በዝናብ የታጠበና በተለያዩ ቦታዎች ዉሃ ያቆረ የኬነዋ ማሳ (ሀ) ዘሩ በታጠበበት ወይም በተቀበረበት ቦታ ወይም ዉሃ ተኝቶበት በነበረበት ቦታ ብቅለት አይኖርም (ለ). የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

11 በተጨማሪም የተወሰነ የሰብል ቅሪት ማሳ ላይ መተው ዘሩ በጎርፍ እንዳይታጠብ ይረዳል። አረምንና በአፈር ውስጥ የሚገኙ ተባዮችን ለመቆጣጠር ማሳውን ቀደም ብሎ ማረስና ፀኃይ እንዲመታው ማድረግ ያስፈልጋል። አለበለዚያ ምስል 5. በእርሻና በዘር መሃል በቂ የጊዜ እርቀት ማሳው ከታረሰ በኋላ (ምስል 5) ወዲያውኑ በዘር ካሌለ አረም ከኬነዋው ቀድሞ ይበቅላል፡፡ መሸፈን አረሞች ቀድመው እንዲበቅሉና እንዲያድጉ ስለሚያደርግ በሰብሉ ላይ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት ይደርሳል። መሬቱ በጣም ጥብቅ ከሆነ በጥልቀት ማረስና የአፈር ለምነትን ሊጨምሩ የሚችሉ ተክሎችን ዘርቶ አበባ ከማውጣታቸው በፊት በመገልበጥ አፈሩ ልል እንዲሆን ማድረግ ይቻላል። ነገር ግን በዚህ ዘዴ በቀላሉ የሚታረስ ልል አፈር ለማግኘት ማሳውን ቀደም ብሎ በማረስ አፈር ውስጥ የተቀበረው ተክል በሚገባ መበስበስ አለበት።በሚገባ ባልታረሰና ጓል አፈር በበዛበት ማሳ (ምስል 6) ላይ የሚተከል የኬነዋ ዘር ውሃ ከሳበ በኋላ በቀላሉ ይደርቃል። ይህም የሚሆንበት ምክንያት ዘሩ ከአፈር ጋር የሚኖረው ንክኪ አነስተኛ ስለሆነ ነው። የኬነዋ ዘር መጠኑ ትንሽ በመሆኑ በደንብ የታረሰና ያልጠበቀ አፈር ከመፈለጉም በላይ ከተዘራ በኋላ አፈሩን በስሱ ደምደም በማድረግ በዘሩና በአፈሩ መካከል በቂ ንክኪ መፍጠር ያስፈልጋል። በመሆኑም በእርሻ ወቅት አንኳሮችን በሚገባ መሰባበርና ማድቀቅ ያስፈልጋል (ምስል 7) ። ከባድ (ሸክላማ) አፈር ላይ የላይኛው አፈር በመጠንከር መሃላቸው ጎድጎድ ያለ ቂጣ መሰል ክፍልፋዮችን መስራቱ የተለመደ ነው። እንዲህ ያለ ሁኔታን የም ንቆጣጠርበት አንደኛው መንገድ ዘሩከመብቀሉ በፊት ኩትኳቶ (ጭፍን ኩትኳቶ) በማድረግ ነው። ነገር ግን ይህ ዘዴሊተገበር የሚችለው ዘሩየተዘራው በመስመር ከሆነብቻ ነው። የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

12 ምስል 7. በሚገባ የታረሰና የመትከያ መስመሮቹ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ ማሳ 5.2. የዘር ወቅት በአጠቃላይ ኬነዋ እስከ አሁን በሃገራችን በተሞከረባቸው አካባቢዎች በሙሉ ተስማሚ የዘር ወቅት ሁኖ የተገኘው ጤፍ የሚዘራበት ወቅት ነው፡፡ የመዝሪያ ወቅትን መወሰንን በተመለከተ ቁልፉ ጉዳይ ኬነዋው ለምርት በሚደርስበት የወቅት የዝናብ ወቅት እንዳይሆን መጠንቀቅ ነው፡፡ 5.3. ዘር፣ የዘር መጠንና የአዘራር ዘዴ መሬቱ በሚገባ ከተዘጋጀ በኋላ ዘር ከመዘራቱ በፊት አንድ ዝናብ መጠበቅ አፈሩ እንዲረጋጋና ቦታ እንዲይዝ ያደርገዋል። እንዲህ በሚሆንበት ጊዜ በዝናብ ወቅት ዘሮች እንዳይገለጡ ወይም ቦታቸውን እንዳይለቁ ወይም ታጥበው እንዳይሄዱ ይረዳል። ይህም በተለይ አመራረቱ በመስመር በሚሆንበት ጊዜ የተክሎች አቀማመጥና ስርጭት እንዳይዛባ ያደርጋል። ዘሮች በተመሳሳይ ጊዜ እንዲበቅሉና በመጨረሻም እኩል ለምርት እንዲደርሱ በዘር ወቅት ዘሮቹ በተመሳሳይ ጥልቀት ላይ እንዲቀመጡ ማድረግ ያስፈልጋል። ከአዘራር ሁኔታ በተጨማሪ የእያንዳንዱ የዘር መጠን (ግዝፈት) ልዩነት በችግኞች አበቃቀልና አስተዳደግ ላይ ልዩነት ሊያስከትል ይችላል። የኬነዋ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

13 ዘሮች ከአንድ ሰብል ላይ ቢሰበሰቡም እንኳን ግዝፈታቸው ተመሳሳይ አይሆንም። በተለይ ሰብሉ ተራርቆ በሚበቅልበት ወቅት በጣም ቅርንጫፋማ ይሆናል፡፡ በዚህን ጊዜ ከየቅርጫፉ የሚገኙት ዘሮች ግዝፈት ስለሚለያይ የአበቃቀላቸውም ሁኔታ ይለያያል። በመሆኑም ዘሮችን በየመጠናቸው መከፋፈል ይህንን ችግር ለመቀነስ ይረዳል፡፡ በዘር ወቅት የአፈሩ ሁኔታ በጣም እርጥብ ወይም ደረቅ መሆን የለበትም። የአፈሩን የውሃ ይዘት መጠን ለማወቅ አንድ እፍኝ አፈር ዘግኖ መጨበጥና መልቀቅ፤ በሚጨበጥበት ወቅት ውሃ ወይም ቀጭን ጭቃ በጣቶች መሀከል ከወጣ የአፈሩ የውሃ ይዘት ከፍተኛ ነው ማለት ነው። ጭብጡ በሚለቀቅበት ወቅት አፈሩ ብትን ካለ የውሃ ይዘቱ አነስተኛ ነው ማለት ነው። ጭብጡ ሲለቀቅ አፈሩ እንደ በሶ ተያይዞ ከቀረ ትክክለኛ የውሃ ይዘት አለው ማለት ነው (ምስል 8)። ከተለያዩ ሃገራት የተገኙ መረጃዎች እንደሚያሳዩት እንደ አፈሩ አይነት፣ የእርጥበት ይዘትና እንደ ዝርያው አይነት በመትከያ መስመሮች መሃከል የሚኖረው ርቀት 20 እስከ 100 ሳ.ሜ ሊሆን ይችላል። በሃገራችን በተለያዩ የአፈር አይነቶች ላይ ከተገኘው የሁለት አመታት ልምድ በመነሳት፤ በመስመሮች መሃከል ከ 40 ሳ.ሜ እና በተክሎች መሃከል 10 ሳ.ሜ ርቀት መጠበቅ የአረም ተጽእኖ ለመቀነስና በማሳ ውስጥ እንደልብ እየተዘዋወሩ ለመስራት ያስችላል። ምስል 8. አፈሩ በእጅ ሲጨበጥ (ሀ) አንደበሶ ከተያያዘ (ለ) የአፈሩ እርጥበት ለተከላ ተስማሚ ነው የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

14 ነገር ግን ከሌሎች ሃገራት የተገኙ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ ተክሎች በተወሰነ ደረጃ ተጠጋግተው እንዲበቅሉ በማድረግ፤ ምርት ፈጥኖ እንዲደርስ፣ ከፍተኛ ምርት እንዲገኝና ተክሎች ቅርንጫፋማ እንዳይሆኑ ያደርጋል። በመሆኑም የተክሎችን ቁጥር በመጨመር ከሚገኘው የምርት ጭማሪ/ ፍጠነት እና የተክሎችን ቁጥር በመቀነስና ቅርንጫፋማ እንዲሆኑ በማድረግ ከሚገኘው የምርት ጭማሪ የትኛው ተመራጭ እንደሆነ ጥናት ሊደረግበት ይገባል። በመስመር በሚዘራበት ወቅት ለአንድ ሄክታር እስከ 10 ኪ.ግ በሚገባ የተጣራ ዘር ያስፈልጋል። ነገር ግን በዘር ወቅት አፈሩ በቂ እርጥበት ከሌለውና የግድ በደረቁ መዘራት ካለበት የሚያስፈልገው የዘር መጠን በእጥፍ ይጨምራል። ለዚህም ምክንያቱ በደረቅ አፈር ላይ ሲዘራ የተወሰነ የኬነዋ ዘር ሊሞት ስለሚችል ያንን ለማካካስ ነው። እንደ አፈሩ አይነትና የውሃ ይዘት ዘሩ አፈር ውስጥ ከ 3 ሳ.ሜ. በላይ መጥለቅ የለበትም። የኬነዋ ዘር ትንንሽ ስለሆነ ከላይ ከተመለከተው ጥልቀት በታች ወይም በላይ የሚቀመጥ ከሆነ በድርቀት ወይም በውሃ ብዛት ሊሞት ይችላል። በዘር አጣጣል ወቅት (ምስል 9) የተስተካከለ ስርጭት እንዲኖርና የዘር ብክነት ወይም መብዛትን ለማስወገድ አንድ እጅ ዘርን ከ 5- 8 እጅ ከሚሆን አሸዋ ጋር መቀላቀል ይቻላል (ምስል 10)። የዘሩና የአሸዋው ምጥጥን የሚወሰነው በአማካኝ የአሸዋው መጠን ሲሆን፤ የእያንዳንዱ አሸዋ መጠን ከእያንዳንዱ የዘር መጠን ጋር ተቀራራቢ ከሆነ የሚያስፈልገው የአሸዋ ብዛት አነስተኛ ከመሆኑም በላይ የተሻለ የዘር ስርጭት ማግኘት ይቻላል። የሚፈለገውን አይነት የዘር ስርጭት ለማግኘት ሌላው ዘዴ ደግሞ የፕላስቲክ ጠርሙስ በመጠቀም መዝራት ነው (ምስል 11) ። የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

15 ምስል 9. በባዶ እጅ ዘር ሲዘራ ምስል 10. ከአምስት እጅ አሸዋ ጋር የተቀላቀለ የኬነዋ ዘር በዚህ አዘራር ዘዴ ጥሩ ውጤት ለማግኘት ለዘር ማውጫ ተብሎ በክዳኑ ላይ የሚሰራው ቀዳዳ በጣምም እንዳይተልቅ በጣምም እንዳያንስ ያስፈልጋል። በተጨማሪም ቀዳዳው የሚሰራው በሚስማር በመብሳት ከሆነ የብሱ አቅጠጫ ከክዳኑ የውስጠኛው ክፍል ወደ ውጨኛው ክፍል መሆን አለበት። ዘሩ ከፈሰሰ በኋላ ውፍረቱ ከሁለት ሳ.ሜ በላይ ባልሆነ አፈር መሸፈን (ምስል 12) ፈጣንና ወጥ የሆነ የዘር ብቅለት እንዲኖር ያስችላል። ዘሩ አፈር ከተመለሰበት በኋላ በእጅ ወይም በእግር ጫን ጫን ማድረግ (ምስል 13) በዘሩና በአፈርመካከል የሚገኘውን አየር በማስወጣት ጥሩ ብቅለት እንዲኖር ከማስቻሉም በላይ ዘሩ በዝናብ ጠብታ እንዳይታጠብ ይረዳል። ምስል 11. ክዳኑ በተበሳ የፕላስቲክ የውሃ መያዣ እቃ ዘር ሲዘራ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

16 ምስል,12 ዘር ከተዘራ በኋላ በስሱ አፈር ሲለብስ ምስል 13, አፈር ከለበሰ በኋላ አፈሩን በመጠኑ ማጥበቅ ምርምር ወይም ለሰርቶ ማሳያ ካልሆነ በቀር ገመድ ወጥሮ ቀጥ ያሉ የመትከያ መስመሮችን መስራት አስፈላጊ ካለመሆኑም በላይ የሚተከለው መሬት በሰፋ መጠን ይህ አሰራር በቀላሉ ሊተገበር አይችልም። በመሆኑም አርሶ አደሮች ኬነዋን በመስመር ለመዝራት በእርሻ ወቅት የሚፈጠሩትን መስመሮች እንደመዝሪያ መስመር መጠቀም ይችላሉ (ም ስል 14) ። በመስመሮቹ መሃል የሚኖረው እርቀት እንደ ድግሩስፋት ይለያያል። ድግሩ ጠባብ ከሆነና በመስመሮች መሃከል የሚኖረው እርቀት ከ 25 ሳ.ሜ ካነሰ፤ አንድ አንድ መስመር እየዘለሉ መዝራት ይቻላል። ወይም ደግሞ በመስመሮች መሃከል የሚኖረው ርቀት በጣም ሰፊ ወይም በጣም ጠባብ በሚሆንበት ጊዜ በእያንዳንዱ መስመር ላይ የሚገኙትን የተክሎች መጠን በመቀነስ ወይም በመጨመር የሚፈለገውን የተክል ብዛት ማግኘት ይቻላል።በእርሻ ጊዜ በተከታታይ መስመሮች መሃል የሚኖረው ርቀት በጣም ጠባብ ወይም በጣም ሰፊ እንዳይሆን መጠንቀቅ ነው እንጂ የመስመሮች መጣመም አሳሳቢ አይደለም። ዘሩ የሚዘራው ቦዩ ላይ ሳይሆን ከፍ ብሎ ወገቡ ላይ መስመር ሰርቶ መስመሩን ተከትሎ በመዝራት ነው። የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

17 ምስል14. በእርሻ ወቅት የሚፈጠሩ መስመሮች ላይ አንድ አንድ እየተዘለለ ቢዘራ በመስመሮች መሃል የሚፈለገውን እርቀት ማግኘት ይቻላል 5.4. ማሳሳት ኬነዋ ዘሩ ከተዘራ በኋላ፣ አፈሩ በቂ እርጥበት ካለው ፣ በ 24 ሠዓታት ውስጥ የሚበቅል ሲሆን፤ ከ ሶስት እስከ አምስት ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ደግሞ ከአፈር ውስጥ ብቅ ይላል (ምስል 15) ። በመጀመሪያዎቹ ሁለትና ሶስት ሳም ንታት የኬነዋ እድገት በጣም አዝጋሚ ስለሆነ በአረም ወይም በእርስ በርስ ፉክክር በከፍተኛ ደረጃ ሊጠቃ ይችላል። ችግኝ የማሳሻ ወቅት የተክልን ቁመት፣ የም ርት መድረሻ ጊዜን፣ የእህል ም ርትንና ጠቅላላ ም ርትን የሚወስን ዋና ምክንያት ነው። ኬነዋ በተፈጥሮው ከብቅለት በኋላ ባሉት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ሳምንታት እድገቱ ዘግምተኛ ስለሆነ እርስ በእርሱም ሆነ በአረም ምክንያት የሚፈጠር ሽሚያን መቋቋም አይችልም። በመሆኑም ከብቅለት በኋላ ከስምንተኛው እስከ አስረኛው ቀናት ውስጥ ወይም ሁለት እውነተኛ ቅጠል ሲያወጡ ችግኞች በሚፈለገው መጠን መሳሳት አለባቸው (ምስል 16) ። የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

18 ምስል 15 ከበቀሉ 3 ቀናት የሆናቸው የኬነዋ ችግኞች በትከክለኛው የዘር መጠን(ሀ) ከሚገባውየዘር መጠን በላይ (ለ) ዝቅተኛ ከፍታ ባላቸውና የአየሩና የአፈሩ ሙቀት ከፍተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ችግኞች በፍጥነት ስለሚያድጉ ችግኝ የማሳሳቱ ስራ ከላይ ከተጠቀሱት ቀናት ቀደም ብሎ ሊተገበር ይገባል። ችግኞች በጣም ተጠጋግተው ከሆነ የበቀሉት፤ ከብቅለት በኋላ ባሉት ቀናት የውሃ እጦት ወይም እጥረት በሚከሰትበት ወቅት ትንንሽ የዘር እራስ በመስራትእድገታቸውን ያቋርጣሉ። በዚህን ወቅት ተክሎቹ ሊኖራቸው የሚችለው ቁመት ከ 30 ሳ.ሜ አይበልጥም (ምስል 17)። ሰብሉ ከዚያ በኋላ ማዳበሪያም ሆነ በቂ እርጥበት ቢያገኝ እንኳን ም ንም የም ርትም ሆነ የእድገት ለውጥ አያሳይም። ነገር ግን ችግኞች በተገቢው መጠን ከሳሱና የአረም ቁጥጥር ከተደረገ አፈር ውስጥ ያለውን እርጥበት ብቻ በመጠቀም ቁመታቸውም ሆነ ምርታቸው በሚፈለገው መጠን ይጨምራል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የእርጥበቱ መጠን ዝቅተኛ ቢሆንም እንኳን የኬነዋ ተክል ከፍተኛ ምርት ሊሰጥ የሚችል ትልቅ የዘር እራስ ይሰራል (ምስል 18) ። ምስል 16. ችግኝ ለማሳሳት የመጀመሪያእውነተኛ የቅጠል ደረጃተስማሚነው የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

19 ምስል. 17 በመጀመሪያዎቹ 3 ሳምንታት ከፍተኛ የምግብና ውሃ ምስል 18. በመጀመሪያዎቹ 3 ሳምንታት ውስጥ በጥሩ ሁኔታ አጥረት ስላጋጠመው ያለጊዜው ያፈራ የኬነዋ ተክል የተያዘ የኬነዋ ማሳ ከዚያ በኋላ የዉሃ እጥረት ቢኖርም እንኳን ምርቱ ብዙም አይቀንስም 5.5. ምስል19.ከብቅለት በኋላ ባሉት ቀናት ሰብሉን ከአረም ለመለየት እንዲቻል በመስመር መዝራት ያስፈልጋል የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀም ዘዴ ኬነዋ ለምነታቸው አነስተኛ በሆኑና ለሌሎች ሰብሎች አስቸጋሪ በሆኑ የአፈር አይነቶች ላይ የመብቀልና ምርት የመስጠት አቅም አለው። ምንም እንኳን ኬነዋ ያለ ማዳበሪያ ተቀባይነት ያለው ምርት መስጠት ቢችልም፤ የተለያዩ የጥናት ጽሁፎች አንደሚያሳዩት እንደ አፈሩ ሁኔታ ከ 40 እስከ 200 ኪ.ግ ናይትሮጅን በሄክታር ቢደረግበት ምርቱ በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል። ነገር ግን ኬነዋ ፎስፈረስ ማዳበሪያ ቢደረግበት ም ንም የም ርት ጭማሪ አያሳይም ። አሁን ባለው ሁኔታ በአገራችን በኬነዋ ላይ የተደረገ የማዳበሪያ ጥናት ስለሌለ ለጊዜው ከ 100 ኪ.ግ ናይትሮጅን በሄክታር እየተደረገ ነው ያለው። ይህም የተደረገበት ምክንያት ኬነዋ በዝቅተኛ ናይትሮጅንም ቢሆን የምርት ጭማሪ ስለሚያሳይና የአነስተኛ አርሶ አደሮችን ማዳበሪያ የመግዛት አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት ነው። የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

20 ማዳበሪያው የሚደረገው ሁለት እኩል ቦታ በመክፈል ነው፡፡ የመጀመሪያው ግማሽ ችግኞች ከሳሱ በኋላ የሚደረግ ሲሆን ሁለተኛው ግማሽ ደግሞ የመጀመሪያው ግማሽ ከተደረገ በኋላ ባሉት ከ 15 እስከ 21 ቀናት ውስጥ በቂ ዝናብ በሚጥልበት ጊዜ ዝናቡን ተከትሎ ማድረግ። የአደራረጉ ሁኔታ ደግሞ ሰብሉ ተክሎቹ ከሚገኙበት መስመር አምስት ሳንቲ ሜትር ራቅ ብሎ በመስመር ማድረግ ነው፡፡ 6. ሰብል ጥበቃ 6.1. አረም ቁጥጥር ገና የበቀሉ የኬነዋ ችግኞችን ከአረም ለመለየት ስለሚያስቸግር በመስመር መዝራት በአረም ወቅት የሚፈጠር ችግርን ያስቀራል (ምስል 19) ። በተለይ አመድማዶ የተባለው ከኬነዋ ጋር ዝምድና ያለው አረም ባለበት አካባቢ፤ ሁለቱም ተክሎች በችግኝ ወቅታቸው በጣም ተመሳሳይ ስለሆኑ (ምስል 20) ከብቅለት በኋላ ባሉት ሁለትና ሶስት ሳምንታት ውስጥ የሚደረግ አረም ቁጥጥር በጣም አስቸጋሪና ጥንቃቄን የሚፈልግ ነው። ከላይ እንደተገለጸው ኬነዋ በፍጥነት መብቀል የሚችል ቢሆንም በመጀመሪያዎቹ ሶስት ሳምንታት እድገቱ በጣም አዝጋሚ ስለሆነ በአረም በቀላሉ ይጠቃል። ስለዚህ ምንም እንኳን ኬነዋ ብዙ እንክብካቤ የማይፈልግ ሰብል ቢሆንም፣ በመጀመሪያው የእድገት ደረጃው ላይ በእጅ በመንቀል ወይም በኩትኳቶ ከአረም ነጻ መደረግ አለበት፡፡ አረም ን በበቂ ሁኔታ ለመቆጣጠር የመጀመሪያ እርምጃ መሆን ያለበት ከፍተኛ የአረም ችግር እንዳለበት የሚታወቅ ማሳ ላይ ያለመዝራት ነው፡፡ በተጨማሪም የማሳ ዝግጅት አስቸጋሪ አረሞችን ለመቀነስ በሚያስችል መልኩ ማለትም ቀደም ብሎና ደጋግሞ በማረስ መከናወን አለበት:: አለበለዚያ ግን አረሞች ከተክሉ እኩል ወይም በፈጠነ ሁኔታ ስለሚያድጉ ከፍተኛ ችግር ይፈጥራሉ (ምስል 21) ፡፡ ከበቀለ ከሶስት ሳምንት በኋላ ግን ኬነዋ በፍጥነት ማደግ ስለሚጀምር አረምን መጨቆን ከመቻሉም በላይ ከአፈር ውስጥ በትነት የሚጠፋው ውሃ ይቀንሳል፡፡ እዚህ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

21 ደረጃ እስኪደርስ ድረስ ግን ከሶስት እስከ አራት የሚደርስ አረማና ኩትኳቶ ዋናው የአረም መቆጣጠሪያ ዘዴ ነው፡፡ በተጨማሪም መጨረሻው ኩትኳቶ ወቅት አፈር ማስታቀፍ ሰብሉ ፍሬ በሚይዝበት ወቅት እንዳይወድቅ (እንዳይጋሽብ) ያደርጋል፡፡ ምስል. 20 ላምበስኳርተር (አመድማዶ) የሚባለው ምስል 21 .በሚገባና በወቅቱ ባለመዘጋጀቱ ምክንያት በሰብል ከኬነዋጋር ተመሳሳይነት ያለው አረም በችግኝና (ሀ) በፍሬ ቅሪት የተወረረ የኬነዋ ማሳ ደረጃ (ለ) 6.2. ነፍሳት ቁጥጥር እንደ ምግብ ሰብልነት ኬነዋ ለአለም አዲስ እንደመሆኑ መጠን ሰብሉን የሚያጠቁ ነፍሳትን በተመለከተ የተደረገው ጥናት አነስተኛ ነው፡፡ በመሆኑም አብዛኛው ኬነዋን የሚያጠቁ ነፍሳት በተመለከተ ያሉት መረጃዎች ከሰብሉ መገኛ (ከአንዲስ) አካባቢ የተገኙ ናቸው፡፡ ኬነዋ ከ 56 በላይ በሆኑ ቅጥል- በል ነፍሳት ይጠቃል፡፡ እነዚህ ነፍሳት በተክሉ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት በተባዩ አይነትና በተክሉና በተባዩ የእድገት ደረጃ ይወሰናል፡፡ በአጠቃላይ ተባዮች ኬነዋ ማሳ ላይ የሚከሰቱበት ድግግሞሽና ብርታት እንደ ሃገሩ ሁኔታ፣ በተባዩ የተፈጥሮ ጠላቶች መኖር ላይና በአካባቢያዊ ሁኔታዎች ላይ ይወሰናል፡፡ 7.2.1. እስከ አሁን ከተመዘገቡት ከ 56 በላይ የኬነዋ ተባዮች ሁለት የሄሊኮቨርፓ (Helicov- erpa species) አይነቶች በመከሰት መጠንም ሆነ በሚያስከትሉት ጉዳት ከፍተኛነት የታወቁ ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ የአፍሪካ ጓይ ትል (Helicoverpa armigera) በመባል የሚታወቀውና የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

22 ብዙ ሰብሎችን የሚመገበው ተባይ በኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄዱ አንዳንድ ሙከራዎችና የዘር ብዜት ማሳዎች ላይ ተከስቶ ጉዳት አድርሷል፡፡ የተባዩ መገለጫዎች የአፍሪካ ጓይ ትል ሙሉ የእድገት ደረጃን ማለትም እንቁላል፣ትል፣ዕጭና ሙሽራ የሚከተል ሲሆን፤እናት የአፍረካ ጓይ ትል የምትንቀሳቀሰው በማታ ጊዜ ሲሆን በተክል ላይ ምንም አይነት ጉዳት አታስከትልም፡፡ ሰውነቷ ፈርጣማ ሲሆን ከክንፎቿ ጫፍ እስከ ጫፍ ያለው እርዝመት 3.8 ሳ.ሜ ይደርሳል፡፡ የፊተኛው ክንፎቿ ከኋለኞቹ በመጠኑ ያነሱ ናቸው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ክንፎቿ ነጣያለ ቡናማ ቀለም ሲኖራቸው ዙሪያቸውን በጥቁር መስመር የተከበቡና የፊተኞቹ ክንፎች መሃል ላይ ጥቁር ነጥብ አለባቸው (ምስል22)፡፡ እናት የአፍሪካ ጓይ ትል ብዛት ያላቸው ነጭ እንቁላሎችን በለጋ ቅጠሎች ወይም እምቡጦች ላይ ትጥላለች፡፡ እንቁላሎቹ እንደ አየሩ ሙቀት ሁኔታ ከ3 እስከ 5 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚፈለፈሉ ሲሆን፤የመፈልፈያ ቀናቸው ሲቃረብ ይጠቁራሉ፡፡ የአፍሪካ ጓይ ትል ጸጉር አልባ ነው፡፡ገና የተፈለፈለ ትል ሰውነቱ ክሬም ወይም ነጭ ቀለም ሲኖረው የጭንቅላቱ ቀለም ግን ጥቁር ነው፡፡ትሉ ለመጀመሪያዎቹ አራት ቀናት ቁመቱ በየቀኑ በእጥፍ ይጨምራል፡፡የመጨራሻ እድገት ደረጃቸው ላይ የደረሱ ትሎች ቀለማቸው በጣም የተለያየና (ቢጫ፣ቡናማ፣አረንጓዴ ወይም ቀይ) (ምስል23) በጎን በኩል ከጫፍ እስከ ጫፍ የሚዘልቅ ነጣ ያለ መስመር ያለባቸው ናቸው፡፡የነዚህ ትሎች ጭንቅላት ጠቆር ያለ ቢጫ ወይም ብርቱካናማ ቀለም አለው፡፡ ትሉ እድገቱን ጨርሶ አፈር ውስጥ በመግባት ወደ ሙሽራነት ከመለወጡ በፊት ከ16 እስከ 17 ለሚሆኑ ቀናት ይመገባል፡፡ ከእንቁላል እስከ እናት ያለውን የእድገት ደረጃ ለማጠናቀቅ በሞቃታማ ወቅት ከ27 እስከ 35 ቀናት የሚፈጅበት ሲሆን በቀዝቃዛ ወቅት ይህ ቁጥር ሊጨምር ይችላል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

23 ምስል 22. የአፍሪካ ጓይ ትልበእናት ደረጃ ላይ ምስል 23 የአፍሪካ ጓይ ትል በትልነት ደረጃው ላይ የተለያየ መልክ አለው ተባዩ የሚመገባቸው ሰብሎችና የጥቃት ምልክቶች የአፍሪካ ጓይ ትል ብዛት ባላቸው የእህል፣ የጭረት፣ የቅባት፣ የመኖ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎች ላይ ጉዳት ያደረሳል፡፡ በምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ተባዩ 35 የምግብ ሰብሎችና 25 የጫካ ተክሎች ላይ እንደሚመገብ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ የተባዩ የጥቃት መጠን እንደ ሰብሉ አይነት፣ እንደ ስነ-ምህዳሩና እንደ አካባቢው ሁኔታ ይለያያል፡፡ በምስራቅ አፍሪካ በዚህ ተባይ ከሚጠቁ ሰብሎች ውስጥ ጥጥ፣ ቦለቄ፣ ኦክራ፣ አተር፣ ጥራጥሬዎች፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ሱፍ፣ ትንባሆ፣ ቲማቲም፣ ዱባ፣ ስንዴና አማራንተስ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ትሉ ቅጠሎች፣ እምቡጦች፣ ቀንበጦች፣ አበቦችና ፍሬዎች ላይ ይመገባል (ምስል 24- 27) ፡፡ በአበቦችና በፍሬዎች ላይ የሚከሰት ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል፡፡ በአበቦች ላይ የሚደርስ ጥቃት በቂ ፍሬ እንዳይመረት ስለሚያደርግ ምርትን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል፡፡ ይህ ተባይ በኬነዋ ቅጠል ላይ ሲመገብ የሚፈጥረው ሁነኛ ምልክት የቅጠሉን የላይኛውን ንጣፍ በመመገብ መስታወት የሚመስል የቅጠሉን ክፍል ሳይነካ ይተወዋል (ምስል 29 እስከ 31)፡፡ በፍሬዎች ውስጥ ተደብቆ የመመገቡ ሁኔታ ይህን ተባይ ለቁጥጥር አስቸጋሪ እንዲሆን ያደረገው ቢሆንም በኬነዋ ላይ ግን ሊደብቀው የሚችለው ፍሬ ስለሌለ ቁጥጥሩ አስቸጋሪ አይሆንም፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

24 ምስል 25 በአበባ እምቡጥ ላይ እየተመገበ ያለ የአሪካ ጓይ ምስል 24. በአፍሪካ ጓይ ትል የወደሙ ለጋ ቅጠሎችና ትል እምቦጦች ምስል 26. በአንድ የኬነዋ ራስ ላይ በርካታ የአፍሪካ ጓይ ምስል.27 የደረሰ ኬነዋ ራስን እየተመገበ ያለ የአፍሪካ ጓይ ትል ትሎች ምስል28. በአፍሪካ ጓይ ትል የተጠቁ የኬነዋ ተክሎች ምስል 29. በአፍሪካ ጓይ ትል የወደመ ቅጠል በቅርበት ሲታይ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

25 ምስል 30 በቅጠል ላይ እየተመገበ ያለ የአፍሪካ ጓይትል ቁጥጥር በማንኛውም ተባይ ቁጥጥር ውስጥ የተባይ አሰሳ የመጀመሪያው ስራ መሆን አለበት፡፡ ይህ ከሆነ ተባዩ ቁጥሩ ሳይበዛና ከፍተኛ ጉዳት ከማድረሱ በፊት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ያስችላል፡፡ ከሌሎች ሃገሮች በተገኘ መረጃ መሰረት በኬነዋ ሰብል ውስጥ በየጊዜው አሰሳ በማድረግ፤ አለፍ አለፍ እያሉ አስር ተክሎችን መርጦ በመመርመር በአማካይ ከአስሩ ተክሎች ላይ ከአንድ ተባይ በላይ ከተገኘ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን በተመረጡት አስር ተክሎች ላይ የተገኘው የተባይ አማካይ ቁጥር ከአንድ በታች ከሆነ ምንም እርምጃ መውሰድ አያስፈልግም፡፡ የማሳ ጽዳት ማለትም ከምርት ስብሰባ በኋላ ቅሪቶችን ማስወገድ፣ መሬትን አስቀድሞና በጥልቀት በማረስ የተባዩን ሙሽራ ለጸሃይና ለተፈጥሮ ጠላቶች ማጋለጥና ተባዩ ሊመገባቸው የሚችሉ አረሞችን ማስወገድ የአፍሪካ ጓይ ትልን ለመቆጣጠር ወይም ለመከላከል መወሰድ የሚገባቸው ሌሎች እርምጃዎች ናቸው፡፡ በተጨማሪም የተባዩ ቁጥር ከፍተኛ ካልሆነና በጊዜ መለየት ከተቻለ በእጅ እየለቀሙ በመግደል ተባዩን መቆጣጠር ይቻላል፡፡ እናት የአፍሪካ ጓይ ትል እንቁላሎቿን በአበባ ደረጃ ላይ ባሉ እንደ የእርግብ አተር፣ ሽንብራ፣ በቆሎ፣ ትንባሆ፣ ማሽላ ወይም የሱፍ ተክሎች ላይ መጣል ትመርጣለች፡፡ ስለዚህ እነዚህን የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

26 ሰብሎች ከኬነዋ ጋር አሰባጥሮ ወይም በኬነዋ ዙሪያ በመዝራትና ተባዩ ወደ እነዚህ ሰብሎች እንዲሳብ በማድረግ በኬነዋ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ይቻላል፡፡ እንደ መሳቢያነት የተመረጠው ሰብል የሚያብብበት ወቅት የኬነዋው ሰብል ከሚያብብበት ወቅት ጋር እንዲገጣጠም ማድረግ ለዚህ የቁጥጥር ዘዴ ውጤታማነት ወሳኝ ነው፡፡ ነገር ግን ተባዩ ከነዚህ ከላይ ከተዘረዘሩት ሰብሎች አንጻር ለኬነዋ ያለው ምርጫ ምን እንደሚመስል በጥናት መረጋገጥ አለበት፡፡ ይህ ሁሉ የቁጥጥር ዘዴ ከተተገበረ በኋላ ተባዩን ለመቆጣጠር ካልተቻለና ኬሚካል መርጨት አስፈላጊ ከሆነ፤ በአካባቢና በሌሎች ፍጥረታት ላይ ተጓዳኝ ጉዳት የማያደርሱ ኬሚካሎችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ረገድ በፋብሪካ የሚቀናበር የኒም ፍሬ ዘይትም ሆነ በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ የኒም ፍሬ የውሃ ብጥብጥ የአፍሪካ ጓይ ትልን ለመቆጣጠር ያስችላሉ:: በተጨማሪምቢቲ የተባለ የሚፈለገውን ተባይ ከመቆጣጠር ባለፈ በአካባቢ ላይ ጉዳት የማያደርስ የኬሚካል አይነት ስላለ ይህንን ተባይ ለመቆጣጠር መጠቀም ይቻላል፡፡ እነዚህ አካባቢ ላይ ጉዳት የማያስከትሉ ኬሚካሎች ካልተገኙ፤ በጥጥ፣ በቲማቲም፣ በአተርና በሌሎች ሰብሎች ላይ የአፍሪካ ጓይ ትልን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ በፋብሪካ የተቀነባበሩ ሰው ሰራሽ ኬሚካሎች ስላሉ እነሱን በኬነዋ ላይ ለመጠቀም ይቻላል፡፡ ነገር ግን ተባዪ ኬሚካሎችን በቀላሉ የመቋቋም ባህሪ ስላለው፤ አነዚህ ኬሚካሎች በጥቅም ላይ በሚውሉበት ጊዜ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡ 7.2.2. ክሽክሽ (ኤፊድ) የተባዪ መገለጫና የጥቃት ምልክት ክሽክሽ የተክል ቅማል በመባል የሚታወቅ መጠኑ አነስተኛ የሆነ ተባይ ነው፡፡ ሰውነቱ በጣም ለስላሳ ሲሆን፤ ከጠቅላላ የሰውነቱ መጠን ጋር ሲነጻጸር እረጅምና ቀጭን እግርና አንቴና አለው:: አንዳንድ ጌዜ የተባዩ ቁጥር በጣም ጨምሮ መተፋፈግ ሲከሰት፤ የተወሰኑ ክሽክሾች የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

27 ክንፍ ያወጡና ለመንቀሳቀስና ለመመገብ በቂ ቦታ ወዳለበት የማሳ ክፍል ወይም ወደ ሌላ ማሳ ይበራሉ፡፡ ምንም እንኳን ይህ ተባይ በማንኛው የተክል እድገት ደረጃ ላይ ሊከሰት ቢችልም በተለየ ሁኔታ ለጋ ቅጠሎችን፣ እንቡጦችንና ቀንበጦችን ያጠቃል፡፡ ነገር ግን የተባዩ ቁጥር በጣም ከፍ በሚልበት ጊዜ ከመሬት በላይ ባለ በማንኛውም የተክል ክፍል ላይ ሊመገብ ይችላል:: ከፍተኛ ጥቃት የደረሰባቸው ቅጠሎች በወስጣቸው የሚገኘው ፈሳሽ ንጥረ ነገር ስለሚሟጠጥ ተባዩ በሰፈረበት በኩል በመጠቅለል ተባዩን ይሸፍኑታል (ምስል 31 እና 32):: ተባዩ በሰብሉ የመጀመሪያ የእድገት ደረጃ ወቅት ከተከሰተ የቅጠል መጠውለግና አጠቃላይ የተክል መቀንጨርን ያስከትላል:: በዚህ ተባይ በጣም የተጠቁ ቅጠሎች በመጀመሪያ በቢጫ ነጠብጣብ ይሸፈኑና እንዚህ ነጠብጣቦች እየሰፉ ሄደው እርስ በእርስ ሲገናኙ ቅጠሉ ሙሉ በሙሉ ቢጫ ይሆንና ጠውልጎ ይረግፋል:: ክሽክሾች መጣጭ ተባዮች ስለሆኑ ከሚመገቡት ውስጥ ትርፍ የሆነውን ስኳር መልሰው ወደ ቅጠሉ የላይኛው ክፍል ላይ ያከማቻሉ (ያስወግዳሉ):: ይህ ትርፍ ስኳር ጥቁር ሻጋታ እንዲበቅል ስለሚያደርግ የቅጠሎችን ምግብ የማዘጋጀት ብቃት ይቀንሳል:: በተጫሪም ክሽክሾች በሚመገቡት ወቅት ከአንድ ተክል ወደ ሌላ ተክል የቫይረስ በሽታን ያስተላልፋሉ:: ይህ ቫይረስ በተክሉ የመጀመሪያ የእድገት ደረጃ ወቅት ከሆነ የተከሰተው፤ ሊገለው ወይም ምንም ምርት እንዳይሰጥ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ተባዩ ደረቅና ሞቃታማ ወቅትን ስለሚመርጥ በመስኖ በሚመረቱ ሰብሎች ላይ የበለጠ ጥቃት ያደርሳል፡፡ በዝናብ ወቅትም ቢሆን ከአስር እስከ አስራ አምስት ቀናት የሚቆይ ደረቅ ወቅት ከተፈጠረ ተባዩ ሊከሰት ይችላል:: የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

28 ምስል 31 በክሽክሽ ጥቃት ምክንያት የተጠቀለለ ቅጠል (ሀ),ክሽክሽ በቅጠል ላይ (ለ) ምስል 32. በክሽክሽ በከፍተኛ ደረጃ የተጠቃ የኬነዋ ተክል ቁጥጥር ለጋ ቅጠሎችን ቀንበጦችንና የአበባ እንቡጦችን አዘውትሮ መሰለል ተባዩ ከተከሰተ ወድያውኑ እርምጃ ለመውሰድ ይረዳል ፡፡ በተጨማሪም በውሃ የተሞሉ ቢጫ እቃዎችን በማሳው የተለያዩ ክፍሎች በማስቀመጥና ውሃው ውስጥ ገብተው የሚሞቱትን በራሪ ክሽክሾች በመቁጠር የተባዩ ቁጥር ማሳው ውስጥ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ይቻላል፡፡ በሚገባ እንክብካቤ የተደረገላቸውና ጤናማ ሰብሎች የተባይንና የበሽታን ጥቃት ለመቋቋም ይቻላቸዋል፡፡ ነገር ግን ከሚገባው በላይ የናይትሮጅን ማዳበሪያ የተደረገበት ማሳ በአጠቃላይ ተባዮችን ከመሳቡም በላይ እንደ ክሽክሽ አይነቶቹን መጣጭ ተባዮች እንቁላል የመጣል ወይም ልጅ የመውለድአቅም ከፍ በማድረግ የሚያደርሱትን ጉዳት ያባብሰዋል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ በሚገባ የተብላላ ብስባሽ ማድረግ የተክሎችን በሽታ ወይም ተባይ የመቋቋም አቅም ይጨምረዋል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

29 ክሽክሽን በበቂ ሁኔታ ሊቆጣጠሩ የሚችሉ የተፈጥሮ ጠላቶች አሉ፡፡ ነገር ግን ተባዩን ለመቆጣጠር ሰው ሰራሽ ኬሚካሎች በጥቅም ላይ በሚውሉበት ጊዜ እነዚህ የተፈጥሮ ጠላቶች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም የተባይ የተፈጥሮ ጠላቶች ከተክል ተባዮች የበለጠ በኬሚካል ስለሚጠቁ ነው፡፡ በዚህ አኳያ ለተባይ ቁጥጥር የሚውል ማንኛውም ኬሚካል መርጦ መግደል የሚችልና ከአካባቢው ቶሎ የሚጠፋ መሆን አለበት፡፡ ከአካባቢ ቶሎ የሚጠፉና በአካባቢ ላይ ጉዳት ከማያደርሱ ኬሚካሎች ውስጥ አይነተኛ ምሳሌ የሚሆነው ከኒም ዛፍ ፍሬ ዱቀት የሚዘጋጅ የውሃ ብጥብጥ ነው፡፡ ብጥብጡን ለማዘጋጀት ርጭቱ ከመከናወኑ ከአንድ ቀን በፊት ፍሬውእንዲደቅ ይደረግና በላስቲክ እቃውስጥ ከ 25 እስከ 50 ግራም የሚሆነው የደቀቀ ፍሬ በአንድ ሊትር ውሃ ውስጥ እንዲሟሟ ይደረጋል፡፡ በሚሟሟበት ወቅት የተያያዙ ጓጎላዎች እንዲፈርሱ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ በኋላ ብጥብጡ በጭለማ ውስጥ ከአስራ ሁለት ሰአት በላይ እንዲቀመጥ ይደረግና በመጨረሻ እየተጣራ ተስማሚ በሆነ ማሳሪያ ይረጫል፡፡ 7.2.3. የጎተራ ተባይ እስከ አሁን ድረስ በየትኛውም የአለም ክፍልም ንም አይነት የጎተራ ተባይ በኬነዋ ላይ አልታየም :: ይህም ሁኔታ ከጥራጥሬ ሰብሎች በተለየ መልኩ ኬነዋ አመቱን ሙሉ አማራጭ የፕሮቲን ም ንጭ ሆኖ እንዲያገለግል ያስችለዋል፡፡ ም ንም እንኳን ጥራጥሬዎች አነስተኛ ገቢ ላላቸው አርሶ አደሮች አይነተኛ የፕሮቲን ምንጭ በመሆን ቢያገለግሉም፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ መሉ በሙሉ የምርት ውድመትን ሊያስከትሉ በሚችሉ የተለያዩ አይነት የጎተራ ተባዮች ይጠቃሉ፡፡ ስለዚህ የስነ ም ህዳርና የምርት አቀማመጥ ሁኔታ ልዩነት ሳይወስነው ኬነዋ አስተማማኝ የሃይልና የንጥረ ነገር ምንጭ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

30 በሽታ አብዛኞቹ ኬነዋን የሚያጠቁ በሽታዎች በሻጋታ ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው፡፡ በባክቴሪያና በቫይረሶች የሚከሰቱ በሽታዎችና ኔማቶዶች የሚፈጥሩት ችግር አነስተኛ ነው፡፡ የበሽታ መከሰት ሁኔታና በሽታው የሚያደርሰው የጉዳት መጠን እንደ ተክሉ የእድገት መጠንና የአካባቢ ሁኔታዎች ይለያያል፡፡ በአለም ላይ በጣም የታወቀውና ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሰው የኬነዋ በሽታ “ዳውኒ ሚልዲው” (Downy mildew) የተባለው ነው፡፡ ነገር ግን አነስተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ እንደ ዳም ፒንግ ኦፍ፣ ግሪን ሞልድ፣ ሊፍ ስፖት፣ ብራውን ስቴም ሮት፣ አይስፖት፣ ባክቴሪያል ስፖት፣ በቫይረስ የሚከሰቱ በሽታዎችና ኔማቶዶች ያጠቁታል፡፡ 7.3.1. ዳውኒ ሚልዲው የበሽታው መገለጫና ተስማሚ አካባቢ ሁኔታዎች ተክሉ በእድገት ደረጃ ላይ እያለ ዳውኒ ሚልዲው የሚዛመተው ስፖር በሚባሉ ጥቃቅን ብናኞች ሲሆን፤ ተክሉ ከደረቀ በኋላ ወይም ማሳ ላይ ምንም ሰብል በማይኖርበት ጊዜ ግን በፍሬው ላይ በሚጣበቁ ወይም በተክል ቅሪት ውስጥ በሚደበቁ ኡኡስፖር በሚባሉ ክፍሎቹ አማካኝነት ይዛመታል፡፡ በመሆኑም በአጭር እርቀት ውስጥ በስፖር አማካይነት ሲዛመት በረጅም እረቀት ግን በኡኡስፓር አማካይነት ይዛመታል፡፡ አሁን ባለው ከፍተኛ የኬነዋ ፍላጎት የተነሳ በሃገራትና በአህጉራት መካከል ከፍተኛ የኬነዋ ዘር ልውውጥ አለ፡፡ ይህም የዘር ልውውጥ የበሽታ ስርጭትን ለመግታት ሲባል የተዘረጉ ስርአቶችን ሁልጊዜ ጠብቆ ስለማያልፍ በበሽታ የተበከሉ ዘሮች ከአገር ወደ አገር የመተላለፍ እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም ኬነዋ በሚገኝበት ቦታ ሁሉ ዳውኒ ሚልዲው ይገኛል ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ የዚህ በሽታ ክስተቱና(incidence) ብርታቱ (severity) በሰብሉ ዝርያ አይነት፣ የአካባቢ ሁኔታና የሰብል እንክብካቤ አይነት ይወሰናል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

31 ሚልዲው የሚያስከትለው የምርት ውድመት በሽታው በተከሰተበት ወቅት ሰብሉ በሚገኝበት የእድገት ደረጃና በተክሉ በሽታውን የመቋቋም አቅም ይወሰናል፡፡ የሚመረተው የኬነዋ ዝርያ በሽታውን የመቋቋም አቅሙ አነስተኛ ከሆነና የአካባቢ ሁኔታዎች ለበሽታው መከሰት ተስማሚ ከሆኑ በተለይ የአየሩ እርጥበት ከፍተኛ ከሆነ፤ በሽታው የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ይሆናል:: በሽታው በሰብሉ የመጀመሪያ እድገት ላይ ከተከሰተ ሰብሉ ሙሉ በሙሉ ሊወድም ይችላል (ምስል 33) ፡፡ ምስል 33. ከችግኝ ደረጃ ጀምሮ በሚልዲው የተጠቃ የኬነዋ ሰብል (ግራ) እና የዘር እራስ ካወጣ በኋላ በሚሊዲው የተጠቃ ሰብል (ቀኝ) አመቺ አካባቢያዊ ሁኔታዎች የሚባሉት ውስጥ ከፍተኛ የአየር እርጥበት(ከ 80% በላይ) እና ከ 18 እስከ 22 ዲ.ሴ የሚደርስ ሙቀት፤ የሻጋታ እድገትንና የስፖር መፈጠርን በማፋጠን ለሚልዲው በሽታ በከፍተኛ ደረጃ መከሰት አይነተኛ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህ ሁኔታ ማለትም የሻጋታ እድገትና የስፖር መፈጠር የተራዘመ ጸሃያማና ደረቅ ወቅት በሚኖርበት ጊዜ ይቋረጣል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ምስል 34. በጤዛ የተሸፈነ የኬነዋ ቅጠል ጠዋት ጠዋት ቅጠሎችን የሚሸፍኑት ትናንሽ የጤዛ ጠብታዎች (ምስል 34) የበሽታውን አምጪ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

32 ተዋህስ እንዲያድግለማድረግ በቂ ናቸው፡፡ ዝናብ የሌለበት ደመናማ ወቅትም ለበሽታው መከሰት ተስማሚ ሊሆን ይችላል፡፡ እርጥበት እስካለ ድረስ በሽታው ከ 0 እስከ 25 ዲ.ሴ በሆነ የአየር ሙቀት ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡ ከፍተኛ የዝናብ መጠን ባለባቸው አካባቢዎች ይህ በሽታ ኬነዋን ለማምረት አይነተኛ ማነቆ ነው፡፡ በመሆኑም እንደ ቦሊቪያ ባሉ ዋና ኬነዋ አምራች ሃገሮች ለውጭ ሃገር ገበያ የሚመረት ኬነዋ ዝቅተኛ የዝናብ መጠን (200- 250 ሚ.ሜ) ባላቸው አካባቢዎች ብቻየተወሰነ ነው፡፡ የበሽታው ምልክቶች ምንም እንኳን የበሽታው ምልክት በግንድ፣ በቅርንጫፍ በአበባና በፍሬ ላይ የሚታይ ቢሆንም በሽታው በዋነኛነት የሚያጠቃው ቅጠልን ነው፡፡ እንደ ተክሉ ዝርያ አይነት ቢጫ፣ ሃምራዊ፣ ቀይ፣ ብርቱካናማ ወይም ግራጫ ቀለምያላቸው ትንንሽና ቅርፅ የሌላቸው ነጠብጣቦች መፈጠር በቅጠሎች ላይ የሚታይ የበሽታው የመጀመሪያ ምልክት ነው (ምስል 35)፡፡ በሽታው እየበረታ ሲሄድ እነዚህ ነጠብጣቦች ይገጥሙና ቅጠሉ ወይቦ ይረግፋል፡፡ ሁኔታዎች ለበሽታው አመቺ ከሆኑ (ከፍተኛ የአየር እርጥበት፣ ደመናማና ዝናባማ ቀን) ሁሉም የተክሉ ቅጠሎች ታመው ሊረግፉና ማንኛውም አይነት የተክል እድገት ሊቆም ይችላል፡፡ ምስል 35. ቀለማቸው እንደ ኬነዋው ሰብል ዝርያ የሚለያይ በሚልዲው ምክንያት በቅጠሎች ላይ የሚታዩ የበሽታ ምልክቶች የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

33 ሻጋታው ስፖሮችን በበሽታው በተበከለው ቅጠል ስር የሚሰራ ሲሆን የስፖሩ ስርጭት መጠንም እንደ ዝርያው በሽታውን የመቋቋም አቅም ይወሰናል (ምስል 36)፡፡ በሽታው በሚጠቃ ዝርያ ላይ ከፍተኛ የሆነ የስፖር መፈጠር ቅጠሎችን ግራጫማ ቀለም እንዲይዙ ያደርጋቸዋል (ምስል 37 ሀ እና ለ)፡፡ ነገር ግን በሽታውን በሚቋቋም ዝርያ ላይ ፈንገሱ ሊታይም ላይታይም ይችላል:: በሽታው ተክሉ የአበባ ወይም የዘር ጭንቅላት በሚያወጣበት ወቅት ከተከሰተ፤ የጭንቅላቱ እድገት ይገታል፣ ጭንቅላቱ የሚይዘው የዘር መጠን ከመቀነሱም በላይ የእያንዳንዱ ዘር መጠንም አነስተኛ ይሆናል፡፡ የኬነዋው ፍሬ በለጋ ደረጃ ላይ ሲደርስ የአካባቢው ሁኔታ ለበሽታው አመቺ ከሆነ የሚፈጠሩት ፍሬዎች ይጠቁራሉ፡፡ በሽታውን በሚቋቋሙ ነባር ዝርያዎች ላይ ግን ሚሊዲው የዘር መጠን ላይ ተጽእኖ አያስከትልም፡፡ ምስል 36.ሚሊዲውን የሚቋቋም ዝርያ (ግራ) በቀላሉ የሚጠቃ ዝርያ በበሽታው እንደተያዘ (መካከለኛ) በመጨረሻ ቅጠሉ በበሽታው ሲረግፍ (ቀኝ) ምስል 37. ግራጫማ ስፖሮች በቅጠል የስረኛው ገጽ ላይ (ሀ); ቀይ ቀለም ባላቸው የኬነዋ ዝርያዎች ላይ በታችኛውና በላይኛው የቅጠል ገጾች ላይ የስፖር አፈጣጠር (ለ) የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

34 በሽታ ቁጥጥር የተለያዩ የአመራረት ዘዴዎችንና የበሽታ መከላከያ ዘዴዎችን አሰባጥሮበመጠቀም ዳውን ሚሊዲውን ለመቆጣጠር ይቻላል፡፡ ከነዚህም ዘዴዎች ውስጥ፡ • በሽታውን የሚቋቋሙ ዝርያዎችን መጠቀም፤ • የዘር ጥራትን መጠበቅ ማለትም በሚገባ የታከመ ዘር መጠቀም፤ • አፈር ላይ የተብላላ ብስባሽ ወይም ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ መጠቀምና ማሳን በሚገባ ማዘጋጀት ተክሎች ግዙፍና ጤናማ እንዲሆኑ ማድረግ፤ • ከሁለት የቅጠል ደረጃ ጀምሮ እስከ አበባ ወይም የፍሬ ጭንቅላት ማውጣት ያለው የእድገት ደረጃ የኬነዋ ተክል ለዚህ በሽታ በጣም የሚጋለጥበት ወቅት ስለሆነ፤ የተከላ ጊዜን በማስተካከል ከፍተኛ ዝናብ የሚኖርበት ወቅት ከዚህ የእድገት ደረጃ ጋር እንዳይገጣጠም ማድረግ፤ • ለአካባቢው ሁኔታ ተስማሚ የሆነ የተክል ቁጥር መጠቀም፡፡ ለምሳሌ ከፍተኛ የአየር እርጥበት ባለበት ቦታ በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር በመስመሮች መካከል ከ 0.5 ሜትርና በተክሎች መካከል ከ0.15 ሜትር ያላነሰ እርቀት እንዲኖር ማድረግ፤ • በማሳ ውስጥ የሚፈጠር ትርፍ ውሃን በወቅቱ እንዲንጣፈፍ ማድረግና፤ • አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ ተገቢውንአይነት ጸረ-ፈንገስኬሚካል መጠቀም፤ ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡ 7. የምርት አሰብሰብና ድህረ ምርት አያያዝ እንደ ዝርያው አይነትና እንደ አካባቢው ልዩ ሁኔታ በአንዲስ አካባቢ የሚገኘው የኬነዋ ምርት በሄክታር ከ 400 እስከ 1200 ኪ.ግ ይደርሳል፡፡ ነገር ግን የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የኬነዋ የምርት አቅም በሄክታር እስከ 11 ቶን ይደርሳል፡፡ በሃገራችን የማስተዋወቅ ስራዎች በተሰሩባቸው የአማራና የኦሮሚያ ክልል በሄክታር በአማካኝ እስከ 20 ኩንታል የተገኘ ሲሆን ከፍተኛ ተብሎ የተመዘገበው 45 ኩንታል ነው፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

35 7.1. ምርት የመድረሱ ምልክቶች የኬነዋ ተክል እድሜ በጨመረ ቁጥር የዘሩ ራስ አይነተኛ ወደ ሆነውና የምርት መድረስን ወደ ሚያበስረው ቢጫ ቀለም ከመቀየሩ በፊት ቅጠሉ ጠቆር ያለ አረንጓዴ ይሆናል (ምስል 38-2):: ለምርት በሚደርስበት ወቅት ተክሉ ከላይ ወደታች ቢጫ እየሆነ ይሄዳል ፡፡ ስለሆነም ፍሬው ለመሰብሰብ ደርሶ ሳለ ቅጠሎቹ አረንጓዴ ሆነው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ የዘሩ ራስና ቅጠሎቹ ጠቆር ያለ አረንጓዴ ከሆኑ ጀምሮ እስከ 15 ቀናት በሚሆን ጊዜ የአንዳንድ ተክሎች የዘር ጭንቅላት ወደ ቢጫነት መቀየር ይጀምራል (ምስል 38-3)፡፡ የአንዳንድ ተክሎች የዘር እራስ ቢጫ መሆን ከጀመረ በኋላ እስከ ስምንት ቀናት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተክሎች የዘር ጭንቅላት ቢጫ ይሆናል (ምስል 38-4 ):: ከዚያም የያንዳንዱ ተክል የዘር እራስ ሙሉ በሙሉ ቢጫ ከሆነ በኋላ በዘሩ እራስ ውስጥ ያሉት ቅጠሎች ወደ ቢጫነት መቀየር ይጀምራሉ (ምስል 38-5 እና 6 ):: የዘር ቅጠሎችን ቢጫ መሆን ተከትሎ ቀሪውም ቅጠል ወደ ቢጫነት መቀየር ትክክለኛውን የምርት መሰብሰቢያ ደረጃን ያመለክታል (ምስል 39-1 )፡፡ ቅጠሎች በሙሉ ቢጫ ከሆኑ በኋላ አዝመራው ሳይሰበሰብ ከቀር፤ ቅጠሎች በሙሉ ይረግፉና ፍሬዎች በንክኪም ሆነ በንፋስ መርገፍ ይጀምራሉ (ምስል 39- 2)፡፡ የዘሩን ጭንቅላት መልክ ለውጥ ከማስተዋል በተጨማሪ፤ ሰብሉ ለመሰብሰብ መድረሱን ለማረጋገጥ የዘር ጭንቅላቱን ጭብጥ አድርጎ መያዝና መልቀቅ፡፡በሚለቀቅበት ወቅት በመዳፍ ውስጥ ዘር ከረገፈና ይህ የረገፈው ዘር በፊት ጥርስ ሲነከስ የመሰበር ድምጽ ካሰማ አዝመራው ለመሰብሰብ ደርሷል ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ምርቱን ሰብስቦ በነፋሻማ ቦታ ማስጣት ያስፈልጋል፡፡ እንደ አማራጭ ደግሞ ፍሬውን በሌባ ጣትና በአውራ ጣት ጥፍር መካከል ጫን ተደርጎ ሲያዝ የማይሰረጉድ ከሆነ ለመሰብሰብ ደርሷል ማለት ነው፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

36 ምርት አሰባሰብና አወቃቅ 7.2. በተለያዩ ምክንያቶች ምርት ከመሰብሰቡ በፊት ቅጠሎች ሙሉ በሙሉ ከረገፉ፤ ምርት ለመሰብሰብ ተስማሚው ጊዜ ጠዋት ነው፡፡ ምክንያቱም የፍሬው እራስ ሌሊቱን ውሃ ስለሚስብ በምርት ስብሰባ ወቅት ዘሩ አይረግፍም፡፡ የኬነዋ ምርት ለመሰብሰብ በደረሰበት ወቅት የሚኖረውን የአየር ሁኔታ በንቃት መከታተል ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ለመሰብሰብ የደረሰ ኬነዋ ዝናብ ከነካው ዘሩ እተክሉ ጭንቅላት ላይ እያለ ሊበቅል ይችላል፡፡ በምርት ማጓጓዝ ጊዜ እንዳያስቸግርና በማስጣጣት ወቅት ብዙ ቦታ እንዳይወስድ፤ ምርቱ ሲሰበሰብ የዘሩን ጭንቅላት ከስሩ ቢቆረጥ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን እስከ አሁን በሃገራችን ባለው ሁኔታ፤ በምርት ስብሰባ ወቅት ሰብሉን ከስሩ በማጭድ ወይም በገጀራ መቁረጥ የተለመደ ነው (ምስል 40) ፡፡ ምርቱ ከተሰበሰበ በኋላ በላስቲክ ኬንዳ (ምስል 41) ወይም በሚገባ የለሰለሰ ቦታ ላይ ተሰጥቶ እንዲደርቅ ይደረጋል፡፡በሚገባ ከደረቀ በኋላ በተሰጣበት ኬንዳ ላይ በዱላ በመደብደብ ይወቃል (ምስል 42 )፡፡ እንደ አማራጭ፤ በውቂያ ወቅት የሚከሰተውን የምርት ብክነት ለመቀነስ ጭንቅላቱን በከረጢት ውስጥ ከቶ በዱላ መምታት ይቻላል፡፡ ምርት ስብሰባው የተከናወነው ተክሉ ሙሉ በሙሉ ከደረቀ በኋላ ከሆነ ወዲያውኑ እንደተሰበሰበ መውቃት ይቻላል፡፡ በመጨረሻም የተወቃው እህል ከተጣራ በኋላ ከተቻለ እርጥበት በማያሳልፍ እቃ ውስጥ መቀመጥ አለበት (ምስል 43) ፡፡ ካልተቻለ ደግሞ በተገኘው እቃ አስገብቶ እርጥበት የማያገኘው ቦታ ማስቀመጥ፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

37 12 34 56 ምስል 38. (1) ኬነዋ ፍሬ ከመያዙ በፊት ብሩህ አረንጓዴ ቀለም አለው (2) ጠቆር ያለ አረንጓዴ ቀለም ያለው ኬነዋ (3) አልፎ አልፎ የዘር ጭንቅላት ቢጫ የሆነበት ማሳ (4) ከግማሽ በላይ ቢጫ የሆነማሳ (5) በዘር እራስ ላይ ያሉ ወደ ቢጫነት የተቀየሩ ቅጠሎች (6) እነዚህ ቅጠሎች በቅርበት ሲታዩ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

38 ምስል 39. (ግራ) ሙሉ በሙሉ ቢጫ የሆነና ለመሰብሰብ የደረሰ የኬነዋ አዝመራ (ቀኝ) ከሚገባው በላይ የደረቀና ቅጠሉ የረገፈ የኬነዋ ማሳ ምስል40. የኬነዋ ምርት በማጭድ (ግራ) ወይም በገጀራ በመቁረጥ ሲሰበሰብ ምስል 41 ምርቱ ከተሰበሰበ በኋላ በተስማሚ እቃ ወይም ቦታ ምስል 42 ኬነዋው ሲደርቅ በተሰጣበት ቦታ ወይም ዕቃ ላይ ተሰጥቶ እንዲደርቅ ይደረጋል ላይ ይወቃል፡፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

39 ምስል 43. በመጨረሻ የተጣራው እህል ዉሃ በማያስገባ እቃ መቀመጥ አለበት 8. ኬነዋን በመስኖ የማምረት ዘዴ ኬነዋ የመስኖ ዉሃ ባለበት አካባቢ ከሌሎች ሰብሎች ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ በሆነ የዉሃ ፍጆታ ሊመረት ይችላል፡፡ ኬነዋን በመስኖ ለማምረት፤ በመጀመሪያ የሚመረትበትን ቦታ አርሶ በሚገባ ማለስለስ ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ በመቀጠል የዉሃ ማጠጫ ቦዮች በየአርባ ሳንቲ ሜትር ርቀት ይሰራሉ፡፡ የዉሃ ማጠጫ ቦዮቹ ርዝመት እንደ መሬቱ ወጣ-ገባነት ይወሰናል፡፡ መሬቱ እምብዛም ወጣ-ገባ ባልሆነበት ቦታ የቦዮችን ርዝመት እስከ አስር ሜትር ድረስ ማስረዘም ይቻላል፡፡ ነገር ግን መሬቱ በጣም ወጣ-ገባ ከሆነ ቦዮች እስከ አምስት ሜትር ድረስ ሊያጥሩ ይችላል፡፡ ቦይ ከተዘጋጀ በኋላ ትክክለኛ የመዝሪያ መስመሮችን ለመወሰንና ቦዮችን ለማስተካከል እንዲረዳ ዘር ከማፍሰሳችን በፊት ማሳውን ዉሃ ማጠጣት ያስፈልጋል፡፡ ዉሃ በሚጠጣበት ወቅት ዉሃው በጣም የሚንደረደር ከሆነ፤ ዉሃ መግቢያ አካባቢ ያሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች ዝቅ እንዲሉ መደረግ አለበት፡፡ ዉሃው ወደ ኋላ ለመመለስ የሚሞክር ከሆነ ደግሞ በቦዩ እርዝመት መሃል ላይ ወይም የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

40 መጨረሻ አካባቢ ያሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች ዝቅ እንዲሉ መደረግ አለበት፡፡ ማሳው ከጠጣ በማግስቱ በሚገባ ጠፈፍ ካለ በኋላ በየቦዩ ውስጥ ዉሃው ደርሶ የነበረበትን ከፍታ ተከትሎ መስመር በመስራት ዘሮችን ማንጠባጠብና በእርጥብ ነገር ግን በሚፈረፈር አፈር ማልበስ፡፡ ከዚህ በኋላ ኬነዋው በቅሎ ሙሉ በሙሉ ከአፈር ውስጥ እስኪወጣ ድረስ ማሳው ዉሃ አይሰጠውም፡፡ ከዚያ በኋላ ችግኞች አንድ ጥንድ እውነተኛ ቅጠል እስከሚያወጡ ድረስ፤ በዉሃ እንዳይታጠቡ በየሶስት ቀኑ ቀለል ያለ (ቦዮችን ለማርጠብ ያህል ብቻ) መስኖ እንዲሰጣቸው ይደረጋል:: የመጀመሪያውን ጥንድ ቅጠል ካወጡ በኋላ፤ ቅጠሎች ጠዋት ወይም ወደ ማታ ላይ የሚያሳዩትን የመጠውለግ ምልክት እያስተዋሉ ዉሃ መስጠት::: ችግኞች ሁለት ጥንድ እውነተኛ ቅጠል ሲያወጡ (ምስል 44)፤ በአንድ ቦታ ሁለት ሁለት ችግኞችን በመተው በየአስር ሳንቲ ሜትር እርቀት ማሳሳት:: ከዚያም ችግኞች አራት ጥንድ ቅጠል ሲያወጡ፤ ከሁለቱ የተሻለውን በማስቀረት ሌላኛውን መንቀል ያስፈልጋል፡፡ በማሳሳትም ሆነ በነቀላ ወቅት ቀሪዎቹ ችግኞች እንዳይነቀሉ ወይም ስራቸው እንዳይናጋ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ዘር በምናፈስበት ወቅት ተጠጋግተው የሚወድቁ ዘሮች የሚያበቅሉት ስር እርስ በርሱ የተጠላለፈ ሊሆን ስለሚችል ነው፡፡ በመስኖ የሚመረት ኬነዋ የሚፈልገው የማዳበሪያ መጠንም ሆነ የማድረጊያው ወቅት በዝናብ ከሚመረት ኬነዋ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ማዳበሪያ ከተደረገ በኋላ ማዳበሪያ በዉሃ እንዳይጠረግ ከማዳበሪያ በኋላ የሚደረግ መስኖ ቀለል ያለ መሆን አለበት፡፡ ማሳው በሚሳሳበት ወቅት፣ ማዳበሪያ በሚደረግበት ወቅትና በአረም ወቅት ኬነዋውን አፈር ማስታቀፍ፤ በምርት የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

41 ወቅት ተክሎች እንዳይወድቁ ያደርጋል፡፡ አጠቃላይ የኬነዋው ማሳ ቢጫ መሆን ከጀመረ በኋላ ዉሃ መስጠት ማቋረጥ ያስፈልጋል፡፡ 9. ዘር በማምረት ወቅት የሚደረጉ ጥንቃቄዎች ምንም እንኳን ኬነዋ ራስ በራስ የብናኝ ዘር ልውውጥ የሚራባ ቢሆንም እስከ 15 ከመቶ የሚደርስ ተሻጋሪ የብናኝ ዘር ልውውጥ ያካሂዳል፡፡ ስለዚህ የተለያዩ ዝርያዎች ተጠጋግተው ከተዘሩ እርስ በእርስ ሊዳቀሉና መሰረታዊ ባህሪያቸውን ሊያጡ ይችላሉ፡፡ ኬነዋ በጣም ትንንሽና ቀላል ክብደት ያለቸው ብናኝ ዘር ስለሚያመርት ብናኝ ዘሮቹ በንፋስ አማካይነት እረጅም ርቀት ይጓዛሉ፡፡ በመሆኑም በዝርያዎች መካከል ያልተፈለገ መዳቀል እንዳይኖር በዝርያዎች መካከል ከሶስት እስከ ስምንት ኪ.ሜ ርቀት መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም እንደ ዳውኒ ሚልዲው ያሉ በሽታዎች በዘር ላይ በመጣበቅ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላው ከአንድ የምርት ዘመን ወደ ቀጣዩ ይተላለፋሉ፡፡ በመሆኑም በዚህ በሽታ መጠቃቱ ከታወቀ ማሳ ላይ የሚገኝዘርን ለተከላ አለመጠቀም ወይም ከመጠቀማችን በፊት ዘሩን በማከም የበሽታውን አምጪ ተዋህስ ማስወገድ ያስፈልጋል፡ የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል